TIKVAH-ETHIOPIA
#Update አሰልጣኝ ገመዶ ደደፎ፣ የኢትዮጵያ ፕሬዜዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በተገኙበት ከኢትዮጵያ መንግሥት የተበረከተላቸውን የ2 ሚሊዮን ብር ሽልማት " አልቀበልም " ብለው መልሰው ከመድረክ መውረዳቸው ይታወሳል። የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር " ገንዘቡ ወደ መንግስት ካዝና ተመላሽ ይሆናል። ምክንያቱም ስጦታ በግድ ውሰዱ ስለማይባል " ሲል ለኤፍ ኤም 97.1 ተናግሯል። አሰልጣኝ ገመዶ ደደፎ ፤ ለሙያውና…
#GemedoDedefo
ከፕሬዜዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ እጅ የተሰጣቸውን የ2 ሚሊዮን ብር ሽልማት " የኛ የአሰልጣኞችን ልፋት አመጥንም " ብለው ሳይቀበሉ የቀሩትና በኃላም " እዛ ቦታ ላይ ያን ማድረግ አልነበረብኝ ፤ ተሳስቻለሁ " በማለት ህዝቡን እና ፕሬዜዳንቷን በይፋ ይቅርታ የጠየቁት አሰልጣኝ ገመዶ ደደፎ ዛሬ " ታስረዋል " ከሰዓታት በኃላ ደግሞ " ከእስር ተፈተው ወደ ቤት ገብተዋል " የሚሉ መረጃዎች ሲሰራጩባቸው ነበር።
እሳቸው ግን " እኔ አልታሰርኩም ፤ እስር ቤትም አልነበርኩም " ሲሉ ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ዙሪያ ታማኝ ነው የሚባለው ጋዜጠኛ ኤቢሳ ነገሰ አሰልጣኙን በስልክ እንዳገኛቸውና " ጉዳዩም እንደሚባለው እንዳልሆነ " ገልጿል።
እሳቸው አሰልጣኝ ገመዶም እስር ቤት እንዳልነበሩ ቃላቸውን እንደሰጡት አመልክቷል።
" እኔ አልታሰርኩም " ማለታቸውን ጋዜጠኛው አሳውቋል።
በሌላ በኩል አሰልጣኙ በራሳቸው የፌስቡክ ገጽ መታሰራቸው " ውሸት ሀሰተኛ ዜና " እንደሆነ እና ቤታቸው እንደሚገኙ ገልጸው ወዲያው ደግሞ አጥፍተውታል።
ጉዳዩን ከሚያውቁ ሌሎች አካላት በተገኘው መረጃ ግን አሰልጣኙ ታስረው እንደነበር ፤ ምሽት ላይ ግን መፈታታቸው ተሰምቷል።
የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አሰልጣኙ " አልወስድም " ያሉት ገንዘብ ወደ መንግስት ካዝና ተመላሽ እንደሚሆን ማሰወቁ ይታወሳል። " ስጦታ በግድ ውሰዱ አይባልም " ነው ያለው።
@tikvahethiopia