TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
Audio
AudioLab

ያዳምጡ⬆️

ልዩ መረጃ ከኤልያስ ጋር
በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8


#FactCheck

የAvoxx Travel Agency ጉዳይ!

- በመጀመርያ እንደ ጋዜጠኛ ሳይሆን እንደ አንድ አገልግሎት ፈላጊ በመሆን የሄድኩት ቄራ ወደሚገኘው የኤጀንሲው ቢሮ ነበር። በቢሮው ሰራተኞች እንደተነገረኝ ውጭ ሀገር (በተለይ ካናዳ እና አሜሪካ) ለትምህርት እና ለስራ ለሚሄዱ ሰዎች ድርጅቱ ዩኒቨርሲቲዎችን እና አሰሪዎችን መፈለግ፣ ከዛ Apply ማድረግ በመጨረሻም የኤምባሲ ማማከር ስራ ይሰራል። ለዚህም ገንዘብ ይቀበላል፣ ካናዳ እና አሜሪካ ከሆነ ቅድመ ክፍያው 10,000 ብር ሲሆን ስራው ወይም ትምህርቱ ከተሳካ ደግሞ ቀሪው 120,000 ብር ይከፈላቸዋል።
.
.
ከላይ ባለው የድምፅ ፋይል ሙሉውን ያዳምጡ!

ልዩ መረጃ ከኤልያስ ጋር
በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FactCheck

በዓለም አቀፉ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት...

EBC ከጠዋት ጀምሮ በዘገባዎቹ ዛሬ ወደ ጠፈር የተላከውን ሳተላይት "የኮሚኒኬሽን" አገልግሎት እንዳለው እየገለፀ ነው። ይህ ቢሆን ሳተላይቱ የቴሌቭዥን፣ ሬድዮ እና ሌሎች ዌቮችን ያስተላልፋል ማለት ነው።

ነገር ግን ETRSS-1 የ "መሬት ምልከታ" ሳተላይት ነች። ለእርሻ፣ የአየር ሁኔታ እንዲሁም አካባቢ ጥበቃ የሚውሉ ምስሎችን የመላክ አቅም ግን አላት።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩና የአፈ ጉባኤው ፎቶ...

[በጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት #FactCheck]

ፎርቹን ጋዜጣ ዛሬ ይዞ በወጣው እትም ላይ ያለውን ፎቶ ተንተርሶ "አቶ ደመቀ መኮንን ስብሰባ ረግጠው ወጡ" የሚሉ በርካታ ፅሁፎች ብዙ ሺህ ተከታይ ባላቸው ገፆች ጭምር ሼር እየተደረጉ ነው።

የፎርቹን ፅሁፍ ግን "አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ ከምክትል ጠ/ሚ ደመቀ መኮንን'ን በጨዋታ መልክ ሲጎትቱ (playfully tugs)" ይላል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot