TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
የ2017 ዓ/ም የመውጫ ፈተና ውጤት እካሁን ይፋ አልተደረገም። ትምህርት ሚኒስቴር የፈተናውን ውጤት ይፋ ማድረጉን ሲያሳውቅ እና የውጤት መመልከቻው አገልግሎት ሲሰጥ ተከታትለን የምናሳውቃችሁ ይሆናል። #TikvahEthiopia @tikvahethiopia
#ExitExamResult

" የፈተናው ውጤት ተለቆ ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ተልኳል " - የትምህርት ሚኒስቴር አመራር

🔴" የፈተና ውጤት ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ጋር መጥቷል " -  የኢትዮጵያ ተማሪዎች ኅብረት

የሀገር አቀፍ መውጫ ፈተና ውጤት ለዩኒቨርሲቲዎች መላኩን የትምህርት ሚኒስቴር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት አጭር ቃል ፥ " ፈተናው ተለቆ ለዩኒቨርሲቲዎች ተልኳል " ብለዋል።

" በነገራችን ላይ ለዩኒቨርሲቲዎች ነው የሚላከው ሊንኩም ይላክላቸዋል። ውጤት ሁሉም ዩኒቨርሲቲ ጋር ደርሷል " ሲሉ ገልጸዋል።

ምን ያክል ተማሪ አለፈ ? ለሚለው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ " ውጤቱ አሁን ስለተለቀቀና ለተቋማት ስለተላከ አጠቃላይ ዳታውን የምናየው ነገ ነው " ብለዋል።

የኢትዮጵያ ተማሪዎች ኅብረት ቡኩሉ፣  " ውጤቱ ተለቋል። የሁሉም ዩኒቨርሲቲ መጥቷል " ሲል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

ውጤት መመልከቻ ሊንኩ ደርሷችኋል ? ስንል ላቀረብንለት ጥያቄ በሰጠን ምላሽ ደግሞ፣ " ዝም ብሎ ውጤቱ ነው የመጣው " የሚል አጭር ምላሽ ሰጥቷል።

ውጤቱ ለየዩኒቨርሲቲዎች ሬጅስትራር መላኩን የገለጸው ኅብረቱ ተፈታኞች ውጤታቸውን በየዩኒቨርሲቲያቸው / ካምፓሳቸው
#ከነገ ጀምሮ ማየት እንደሚችሉ ገልጿል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የፈተናው ውጤት በኦንላይ የሚታይበት መንገድ ካላ ጠይቆ ያቀርባል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ExitExamResult " የፈተናው ውጤት ተለቆ ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ተልኳል " - የትምህርት ሚኒስቴር አመራር 🔴" የፈተና ውጤት ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ጋር መጥቷል " -  የኢትዮጵያ ተማሪዎች ኅብረት የሀገር አቀፍ መውጫ ፈተና ውጤት ለዩኒቨርሲቲዎች መላኩን የትምህርት ሚኒስቴር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል። የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት አጭር ቃል ፥ " ፈተናው…
#UPDATE #ExitExamResult

“ ከዲሲፒሊን ጋር በተገናኘ 540 ተማሪዎች ተለይተዋል። ከዚህኛው ውጤት እስከ መሰረዝ፣ የሚቀጥለውንም ድጋሚ ያለመፈተንና እንቅፋታቸው ትልልቅ የሆኑም እስከነጨረሻውም የሚይፈተኑበት ጊዜ ሊኖር ይችላል ” - ትምህርት ሚኒስቴር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ

ሃገር አቀፉን የመውጫ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ውጤት ከሰዓታት በፊት መለቀቁን ትምትርት ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ተማሪዎች ኅብረት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጻቸውን ነግረናችኋል።

በወቅቱም የፈተናው ውጤት የሚታይበት ሊንክ ስንጠይቅ “ ለዩኒቨርሲቲዎች ተልኳል ” በመባሉ የተለዬ መመልከቻ ካለ እንደምናጋራችሁ ቃል ገብተንላችሁ ነበር።

በዚህም፣ የውጤት መመልከቻው ሊንክ የትኛው ነው ? ስንል የጠየቅናቸው አንድ የትምህርት ሚኒስቴር አመራር በሰጡን ቃል፣ “ ውጤት የሚታይበት ሊንክ ኖርማሊ ለዩኒቨርሲቲዎች ተልኳል። ከተወሰኑ ዩኒቨርሲቲዎች ውጪ ሁሉም ማዬት እንዲችሉ ተነግሯቸዋል ” የሚል ምላሽ ሰጥተውናል።

“ ሊንኩ፦ ባለፈው ኦንላይን ሳፓርቲንግ የምንጠቀምበት ፔጅ ነበረ፤ እዛ ፔጅ ላይ ተለቋል። ያውቁታል እነሱ ፤ ከዚህ በፊት የተለቀቀ ሊንክ ነው ለኤግዚት ኤግዛም የተመዘገቡበት ሊንክ ላይ ውጤት ማየት ይችላሉ ” ሲሉ አስረድተዋል።

ስንት ተማሪዎች እንዳለፉና እንደወደቁ ጠይቀናቸው ገና እንዳልታወቀ በገለጹበት አውድ፣ “ አናላይስሱ አልተሰራም። አንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች ቅዳሜ እለት ስለሚያስመርቁ ለእነሱ ተብሎ ነው በችኮላ የተለቀቀው ” ብለዋል።

በሌላ በኩል፣ የዲሲፒሊን ጉድለት የታየባቸው ዩኒቨርሲቲዎች ላይ የፈተና ውጤት አለመለቀቁንም እኝሁ አካል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

“ የዲሲፒሊን ግድፈት ጎልቶ የታየባቸው ዩኒቨርሲቲዎች ላይ ውጤት አልተለቀቀም፤ ወደ 6 በሚሆኑ ዩኒቨርሲቲዎች። ከዛ ውጪ ተለቋል። ስለዚህ አናላይሲሱ የ6ቱም ተጨምሮ ሲያልቅ ይሰራል ” ሲሉ ነግረውናል።

ስለዚህ የፈተናው ውጤት በተመረጡ ዩኒቨርሲቲዎች ነው የተላከው ማለት ነው ? ስንል ላቀረብንላቸው ጥያቄ ፣ “ የፈተና ኮራፕሽኑ፤ ስርቆቱ የጎላባቸው 6 ዩኒቨርሲቲዎች ብቻ ላይ ነው እንጂ ያልተለቀቀው ሁሉም ላይ ተለቋል ” የሚል ምላሽ ነው የሰጡን።

በፈተናው ወቅት የተፈጠረ ችግር ነበር ወይስ በሰላም ተጠናቋል ? ለሚለው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ የአመራሩ ምላሽ፣ “ በዚህኛው ፈተናችን በሰላም ነው የተጠናቀቀው። የጎላ ቸግር አልነበረም ” የሚል ነው።

አክለው ደግሞ፣ “ የተለመዱ የዲሲፒሊን ችግሮች ናቸው የነበሩት፣ የተማሪዎች ከስርቆት ጋር በተገናኘ ያልተፈቀዱ እንደ ሞባይል ያሉ ኤሌክትሮኒክ ዲቫይሶችን ለመጠቀም ሙከራ ማድረግ፣ ወጣ ያለ ደግሞ ከዚህ በፊት የተፈተኑ ተማሪዎች ገብተው ለመፈተን ሙከራ ማድረግ፣ ናቸው እንጂ በጣም የጎላ ችግር አልታዬም ” ነው ያሉት።

ከዲሲፒሊን ግድፈት ጋር በተያያዘ ስንት ተማሪዎች ተገኝተዋል ? ለሚለው ጥያቄ በሰጡን ምላሽ፣ “ ከዲሲፒሊን ጋር በተገናኘ እስካሁን ድረስ ወደ 540 ተማሪዎች ተለይተዋል። የዚህኛው ራውንድ ውጤት እስከ መሰረዝ፣ የሚቀጥለውንም ድጋሚ ያለመፈተንና እንቅፋታቸው ትልልቅ የሆኑ እስከነጨረሻውም የማይፈተኑበት ጊዜ ሊኖር ይችላል ” ብለዋል።

“ እስካሁን ግን አልተወሰነም። ለጊዜው ግን የዚህኛው ውጤት ዲስኳሊፋይድ እንደሚደረግ ነው 54ዐ ተማሪዎች የተለዩት። ቁጥሩ ሊበልጥ ይችላል፤ ለጊዜው ግን ወደ 540 ተማሪዎች ተለይተዋል ” ሲሉም አክለዋል።

(ስንት ተፈታኞች እንዳለፉና እንዳላለፉ ውጤቱን ተከታትለን በቀጣይ የምናሳውቃችሁ ይሆናል)

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia