TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#EliasMelka

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በታዋቂው የሙዚቃ ሰው ኤልያስ መልካ ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁ፦

"ዝነኛው የሙዚቃ አቀናባሪ #ኤልያስ_መልካ ከዚህ አለም በሞት በመለየቱ የተሰማኝን ጥልቅ ሀዘን ለመግለጽ እወዳለሁ። ኤልያስ ትውልዳችን በኩራት ስማቸውን ከሚያነሳቸው፤ ለጥበብ ህይወታቸውን ሰጥተው ድንቅ ስራዎቻቸውን ለታሪክ ካስቀሩልን ከያኒያን መሀል ከፊት የሚሰለፍ የጥበብ ሰው ነበር። ፈጣሪ ነፍሱን በገነት ያኑርልን! ለመላው ቤተሰቦቹ እና ለስራው አፍቃሪዎች መጽናናትን እመኛለሁ።" ኢንጂነር ታከለ ኡማ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#EliasMelka

የሙዚቃ ሰው ኤልያስ መልካ የቀብር ስነ ስርዓት ሰኞ፣ መስከረም 26 ቀን 2012 ዓ/ም ከቀኑ 9:00 ሰዓት በጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤተ ክርስቲያን ወዳጅ ዘመድና አድናቂዎቹ በተገኙበት ይፈፀማል።

ዛሬ ከሰዓት በፋና ኤፍ ኤም 98.1 የከሀ እስከ ፐ ፕሮግራም ላይ በቀጥታ ቆይታ ያደረጉት ሙዚቀኛ ዳዊት ይፍሩ እና ሰርፀ ፍሬስብሃት እንዳስታወቁት፣ ከቀብር ስነ-ስርዓቱ አስቀድሞ ሙዚቃን በተማረበት ያሬድ የሙዚቃ ት/ቤት አሊያም በሚሊንየም አዳራሽ አሸኛኘት ይደረግለታል። ይህን የሚያስፈጽም ኮሚቴ ተዋቅሮም በስራ ላይ ይገኛል።

ምንጭ፦ ከሀ እስከ ፐ የሬድዮ ፕሮግራም
@tsegabwolde @tikvahethiopia