TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.1K photos
1.5K videos
211 files
4.09K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#DrTazebachew

የዶ/ር ታዘባቸው ውዴ ጉዳይ ዛሬም ድረስ መፍትሄ ሳያገኝ፤ ዩኒቨርሲቲውም አንዳች ነገር ሳይል ቀጥሏል።

ዶ/ር ታዘባቸው ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በህክምና ተመርቆ ይርጋለም ሆስፒታል ለ2 ዓመት አገልግሎ ለማህፀንና ፅንስ ስፔሻላይዜሽን ትምህርት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (ጥቁር አንበሳ) ተቀላቅሎ ትምህርቱን ሲከታተል ነበር።

ዶ/ር ታዘባቸው ከልጅነቱ ጀምሮ በአንድ አይኑ ላይ የመሸዋረር ችግር ያለበት ሲሆን ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሲመረቅ ሆነ ወደ አ/አ ጥቁር አንበሳ ሲቀላቀል አንድም ቀን ስለአይኑ ጉዳይ ተነስቶም፤ ተጠይቆ አያውቅም።

ጥቁር አንበሳን ሲቀላቀልም በቃል እና በፁሁፍ ፈተና ተፈትኖ ብቃቱን አስመስክሮ ተቋሙ ገብተህ መማር ትችላለህ ብሎት ነው።

ነገር ግን 4 ዓመት እጅግ ከፍተኛ ድካምና ጥረት የሚጠይቀውን የስፔሻላይዜሽን ትምህርቱን ቀንና ሌት እንቅልፍ አጥቶ ተምሮ ሊመረቅ ጥቂት ቀናት ሲቀረው ድንገት የዓይን ምርመራ አድርግ ይባላልና ብቁ አይደለህም ተብሎ ወደሌላ ዲፓርትመንት ገብቶ (ኒውሮሎጂ) ከአንደኛ አመት እንዲጀምር ተደርጓል።

ዶ/ር ታዘባቸው ከዚህ ቀደም እንዲህ አይነት ነገር ሰምቶ እንደማያውቅ ተናግሮ እሱ ብቻውን ከሌሎች በተለየ የአይን ምርመራ እንዲያደርግ ታዞ ምርመራ ካደረገ በኃላ በአጭር ፅሁፍ ትምህርቱን መቀጠል እንደማይችል እና አንደማይመረቅ እንደተነገረው ያስረዳል።

የአይኑ መንሸዋረር አንድም ቀን ለስራው ፣ለትምህርቱ እንቅፋት ሆኖበትና በዚህ ምክንያት በርካታ የቀዶ ጥገና ስራ ሲሰራ ችግር ተፈጥሮ እንደማያውቅም ይገልፃል።

4 ዓመት ከለፋበት ትምህርት ወጥቶ ወደሌላ ዲፓርትመንት እንዲገባ የተደረገው ዶ/ር ታዘባቸው ዩኒቨርሲቲው ውሳኔውን ዳግም እንዲያጤነው ካልሆነ መብቱን ለማስከበር ወደህግ እንደሚወስደው ከጠበቃው ጋር አሳውቋል።

@tikvahethiopia