TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ሹመታቸው የፀደቀላቸው የካቢኔ አባላት በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ ፈፅመዋል። አዲስ የተሾሙት ሚኒስትሮች ዝርዝር ፦ 1. አቶ ደመቀ መኮንን - የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር 2. ዶ/ር አብርሃም በላይ - የሃገር መከላከያ ሚኒስትር 3. አቶ አህመድ ሽዴ - የገንዘብ ሚኒስትር 4. ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል - የስራና ክህሎት ሚኒስትር 5. አቶ ኡመር…
#DrEngSeleshiBekele
" በቀጣይ አገሬ በምትፈልገኝ አገልግሎት የምሰማራ ይሆናል " - ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ
የቀድሞው የኢትዮጵያ ውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ ለአዳዲሶቹ ሚኒስትሮች ለኢ/ር አይሻ መሀመድ እና ለዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢቲፋ የመልካም ምኞት መልዕክት አስተላለፉ።
ዶክተር ኢ/ር ስለሺ በይፋዊ ትዊተር ገፃቸው ፤ ኢንጂነር አይሻ መሀመድ የመስኖ እና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ሚ/ር እና ዶ/ር ኢ/ር ሃብታሙ ኢተፋ የውሃና ኢነርጂ ሚ/ር ሆነው በመሾማቸው "እንኳን ደስ አላችሁ" ብለዋል።
አክለው ፤ " ላለፉት 5 አመታት ስመራው የነበረው የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚ/ር ዛሬ በጸደቀው የአስፈጻሚ መ/ቤቶች አደረጃጀት መሰረት በመሾማችሁ በጣም ደስ በሎኛል" ሲሉ ፅፈዋል።
" ሁለቱም ዘርፎች ለአገራችን ማደግ እና መለውጥ ወሳኝ ተቋማት ናቸው " ያሉት ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ ፤ "በውጤታማነት እንደምትመሩ ባለሙሉ እምነት ነኝ፡፡ የበኩሌ ድጋፍም ሁሌም አይለያችሁም" ሲሉ ገልፀዋል።
"ያደረግሁት አስተዋጽኦ በፈታኞቹ ወቅቶችና ሰአታት አገሬን ቀና አድርጓታል ብዬ አምናለሁ፡፡ በቀጣይ አገሬ በምትፈልገኝ አገልግሎት የምሰማራ ይሆናል፤ ለነበረኝ ትልቅ ሃላፊነትና ለተደረገልኝ ትብብር አመሰግናለሁ" ሲሉም ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
በመጨረሻም ፥ "አገራችን ኢትዮጵያን ፈጣሪ ይጠብቃት፡፡ ኢትዮጵያችን እንደ ገናና ታሪኳ ሁሉ ጸንታ ትኖራለች" ሲሉ ሀሳባቸውን አጠቃለዋል።
@tikvahethiopia

👍1
TIKVAH-ETHIOPIA
#DrEngSeleshiBekele " በቀጣይ አገሬ በምትፈልገኝ አገልግሎት የምሰማራ ይሆናል " - ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ የቀድሞው የኢትዮጵያ ውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ ለአዳዲሶቹ ሚኒስትሮች ለኢ/ር አይሻ መሀመድ እና ለዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢቲፋ የመልካም ምኞት መልዕክት አስተላለፉ። ዶክተር ኢ/ር ስለሺ በይፋዊ ትዊተር ገፃቸው ፤ ኢንጂነር አይሻ መሀመድ የመስኖ እና…
#DrEngSeleshiBekele
የቀድሞ የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር የነበሩት ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ በሚኒስትር ማዕረግ የድንበር ተሻጋሪ ወንዞችና የህዳሴ ግድብ ዋና ተደራዳሪና አማካሪ ሆነው በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ተሹመዋል።
@tikvahethiopia
የቀድሞ የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር የነበሩት ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ በሚኒስትር ማዕረግ የድንበር ተሻጋሪ ወንዞችና የህዳሴ ግድብ ዋና ተደራዳሪና አማካሪ ሆነው በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ተሹመዋል።
@tikvahethiopia
👍1
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በቅርቡ የተሾሙ አምባሳደሮች የተመደቡባቸው ሀገራት ዝርዝር ይፋ አድርጓል። አምባሳደሮቹ የተመደቡባቸውን ሀገራት ፦ 1. አምባሳደር ተፈራ ደርበው —ጃፓን 2. አምባሳደር ደሴ ዳልኬ—ደቡብ ኮሪያ 3. አምባሳደር ዶ/ር ስለሺ በቀለ—አሜሪካ 4. አምባሳደር ባጫ ደበሌ — ኬንያ 5. አምባሳደር ሀሰን ኢብራሂም–ግብፅ 6. አምባሳደር ዳባ ደበሌ –ሩዋንዳ 7. አምባሳደር ጀማል…
#DrEngSeleshiBekele
ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ ቃለመሃላ ፈፀሙ።
በቅርቡ በአሜሪካ ሀገር የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው የተሾሙት ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ ዛሬ ከፕሬዜዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በመቀበል ቃለመሃላ መፈፀማቸውን ገልፀዋል።
ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በተረጋገጠ የትዊተር ገፃቸው ላይ ፥ " ዛሬ በአሜሪካን አገር የኢትዮጵያ ልዩ መልእክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ለመሆን ከክ/ት ፕ/ት ሣሕለወርቅ ዘውዴ በመቀበል ቃለመሐላ ፈፅሜያለሁ " ብለዋል።
አክለው ፥ " ለመልካም ግኑኝነት፣ የአገሬን ፍላጎት፣ ክብር እና ጥቅም ለማስጠበቅ እተጋለሁ " ሲሉ ገልፀዋል።
ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር (በቀድሞ) በነበሩ ሰዓት በተለይም በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ በዓለም መድረክ የኢትዮጵያን እውነት ይዘው በመሟገት እና ጥቅሟ እንዳይነካ በመታገል እንዲሁም በተመደቡበት ቦታ ሀገራቸውን በትጋት በማገልገል ይታወቃሉ።

👍974❤117👏43🥰28👎17😱9😢9