TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ETHIOPIA

በነገራችን ላይ ትላንት በቫይረሱ ተይዟል ከተባለው ጃፓናዊ ጋር ንክኪ የነበራቸው ግለሰቦች ከ45 በላይ ደርሰዋል። ሁሉም የጤና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል። እስካሁን ድረስም ምልክቱን ያሳየ ሰው የለም።

#DrEbaAbate
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የበሽታውን ምልክቶች ይወቁ!

- የኮሮና በሽታ ምልክቶች እጅግ ቀላል ናቸው፤ ብዙ ጊዜም አብረውን የቆዩ በሽታዎች የሚያሳዩት ምልክት ነውና ያንን መለየት አስፈላጊ ነው።

- ጉንፋን የሚያሳየው ምልክት በኮሮና ቫይረስ ላይም እንደምልክትነት ይከሰታል። ትኩሳት፣ ደረቅ ሳል፣ የመተንፈስ ችግር ይገጥማል፣ የንፍጥ መዝረክረክ ይኖራል።

- ከላይ የተጠቀሱት ምልክቶችን የሚያሳይ ከበሽታው የተጠቁ ሀገራት የመጣ ከሆነ፣ ወይም ደግሞ በቅርቡ ከሱ ጋር ንክኪ ያላቸው ሰዎች እንዳሉ ካወቀ ጥንቃቄ መውሰድ ይኖርበታል።

#DrEbaAbate
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
መደረግ ያለባቸው ጥንቃቄዎች!

ህብረተሰቡ ጥንቃቄ ማድረጉ ተገቢ መሆኑ ቢታመንም፤ የሚደረገው ጥንቃቄ ልኬትም ሊኖረው ይገባል። አሁን ባለው የኢትዮጵያ ሁኔታ ከቫይረሱ ስርጭት ስጋት ጋር በመነጨ ትራንስፖርት መቆም አለበት የሚል ደረጃ ላይ አልተደረሰም።

ትራንስፖርት በምንጠቀምበት ወቅት ግን ጥንቃቄዎች እንዳይለዩን ይመከራል። የእጃችንን ንፅህና መጠበቅ፣ አልኮል ነክ በሆኑ ነገሮች እጃችንን ማፅዳት፣ ያህንን የማናገኝ ከሆነ በንፁህ ውሃና ሳሙና እጃችንን በአግባቡ መታጠብ ይኖርብናል።

ከማያስነጥሱ፣ ከሚያስሉ ሰዎች በሁለት ሜትር መራቅ፤ እኛ ላይ ደግሞ መሰል ምልክቶች ሲታዩ ህዝብ የሚሰበሰብበት ቦታ አለመሄድ፣ አላስፈላጊ የሆና ትልልቅ ስብሰባዎችን መመጠን አስፈላጊ ነው።

#DrEbaAbate

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia