TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#CapitalMarket #Ethiopia በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪዎች ፈቃድ አሰጣጥና ቁጥጥር መመሪያ ቁጥር 980/2016 ስራ ላይ ውሎ ይገኛል። በዚህ መሰረት የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ከፊታችን #ሰኞ ጀምሮ ለካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪነት ፈቃድ ማመልከቻዎችን መቀበል እንደሚጀምር አሳውቋል። በዘርፉ ለመሰማራት ፍላጎት ያላቸው አካላት በመመሪያው የተቀመጡትን የፈቃድ መስፈርቶችን…
የኢንቨስትመንት ባንክ ምንድነው ? ከሌሎች ባንኮች በምን ይለያል ?

የንግድ ባንኮች የሚባሉት ፦ በብሔራዊ ባንክ ስር የሚተዳደሩ ፤ ከብሔራዊ ባንክ ፍቃድ ተሰጥቷቸው የሚተዳደሩ ናቸው።

ኢንቨስትመንት ባንክ ፦ በካፒታል ገበያ አዋጅ መሰረት የሚቋቋም፣ በካፒታል ገበያ ባለስልጣን ፍቃድ የሚሰጠው ነው። ከግለሰቦች ተቀማጭ የሚወስድ ከሆነ የኢንቨስትመንት ባንክ መሆን አይችልም።

የኢንቨስትመንት ባንኪግ ስራ ምንድነው ?

ዋና ስራው ወደ ካፒታል ገበያ የሚመጡትን ኩባንያዎች፣ ድርጅቶች ፣ መንግስት ፣ ከተሞች ሊሆኑ ይችላሉ ቦንድ መሸጥ ሲፈልጉ ፣ አክሲዮን መሸጥ ሲፈልጉ ፦
* አክሲዮኑ ምን ይመስላል ?
* አክሲዮኑ በምን ያህል ዋጋ ይሸጥ ?
* መቼና ለማን ይሸጥ ? የሚለውን የፋይናንስ ስትራተጂ ላይ የምክር አገልግሎት የሚሰጡና የሚያገናኙ በካፒታል ገበያ ውስጥ ትልቁን ድርሻ የሚጫወቱ ናቸው።

ለምሳሌ ፦ አንድ በግል የተያዘ ድርጅት ፤ ወደ ህዝብ ድርጅት ነው መቀየር የምፈልገው ፣ የሼር ኩባንያ ነው መሆን የምፈልገው ብሎ ሼሩን የካፒታል ማርኬት ላይ መሸጥ ቢፈልግ ድርጅቱ ምን ያህል ነው ዋጋው ? ለአብነት ወደ 2000 ሼር ቀይሬ 2 ሺህ ሼር ለገበያው ሸጣለሁ ቢል እያንዳንዱ ሼር ዋጋው ምን ያህል ነው የሚለውን አጠቃላይ ስራ የሚሰራው ኢንቨስትመንት ባንክ ነው።

በተጨማሪ ኢንቨስትመንት ባንክ ፦

* price discovery / ገበያው ላይ ኩባንያዎች ያላቸው እውነተኛ ዋጋቸው ምንድነው የሚለውን ያጣራል።
* የካፒታል ገበያ ላይ የሚሳተፉ አካላትን ያማክራል።
* የካፒታል ብክነት እንዳይኖርና ካፒታል ወደአስፈላጊው ቦታ እንዲሄድ ያደርጋል።

ኢንቨስትመንት ባንኮች እንደ ሌሎች የንግድ ባንኮች ከሰዎች ላይ ተቀማጭ ገንዘብ / deposit አይወስዱም።

የኢንቨስትመንት ባንኮች የማማከር ስራን የሚሰሩ ሲሆን አንዳንድ ኩባንያዎች የኢትዮጵያ ሰነደ መዋዕለ ነዋይ ገበያ ለመግባት ሲወስኑ ኩባንያውን ማዛጋጀት፣ ሼሩ ምን ያህል ነው የሚለውን መለየት ፣ ምን ያህል ሼር ለምን ያህል ሰው የሚለውን መለየት ስራዎችን ይሰራሉ።

የካፒታል ገበያውን የሚቆጣጠረው አካል ፤ በካፒታል ገበያው ለሚሳተፉ አካላት ፍቃድ ከመስጠት እና ሂደቱን ከመቆጣጠር ባለፈ ኢንቬስተሮች በየትኛው ዘርፍ መሳተፍ አለባቸው የሚለውን አይወስንም ሃሳብም አይሰጥም ፤ ይህን የሚያደርጉት የአዋጭነት ትንተናዎችን በመስራት የኢንቨስትመንት ባንኮች ናቸው።

ማማከር፣ ኢንቬስተሮችን እና ተፈላጊ የፋይናንስ ሃብት ማገናኘት የኢንቨስትመንት ባንኮች ስራ ይሆናል። የካፒታል ገበያ ላይ የሚሳተፉ ድርጅቶችን ወክለው ከሰነደ መዋዕለ ነዋይ ገበያው ሆነ ከተቆጣጣሪ መ/ቤቱ ጋር በመሆን ብዙ ስራዎች ይሰራሉ።

ለኢንቨስትመንት ባንክ መስረታ የሚጠየቀው ካፒታል ለንግድ ባንኮች ከሚጠየቀው #ያነሰ ነው።

የንግድ ባንኮች በዚህ ላይ መሳተፍ ይችላሉ ?

አሁን በኢትዮጵያ ስራ ላይ ያሉ የንግድ ባንኮች ጎን ለጎን የኢንቨስትመንት ባንክ ተሳትፎ የሚያደርጉበት እድል አላቸው።

እንደ ኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን መረጃ ከመጪው ሰኞ ጀምሮ መስፈርቱን ለሚያሟሉ የኢንቨስትመንት ባንክ ፍቃድ መስጠት የሚጀምር ሲሆን በአጭር ጊዜ ውስጥ በኢትዮጵያ ያሉና ከኢትዮጵያ ውጭ ያሉ ባንኮችም የኢንቨስትመንት ባንክ ፍቃድ ይወስዳሉ ተብሎ እንደሚጠብቅ ተስፋ ተደርጓል።

Credit ፦
#DrBirukTaye (ECMA Director)
#SirakSolomon (ECMA Senior Legal Advisor)
#YohanessArega (ECMA Senior Advisor)
#WuberstTessema (Journalist , FBC)

ዝግጅት ፦ #TikvahEthiopia

@tikvahethiopia