#ፋይዳ #National_ID
" እያንዳንዱ ሰው መታወቅ አለበት " - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ባለፉት 2 እና 3 ዓመታት በተሰራው ስራ ከ15 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ለፋይዳ / ብሔራዊ መታወቂያ መመዝገባቸውን ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
ይህን የገለጹት " ቴክ-ቶክ " ከተሰኘ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ነው።
ባለፉት 2 እና 3 ዓመታት በተሰራው ስራ አሁን ላይ ከ15 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የፋይዳ / ብሔራዊ መታወቂያ እንዳወጡ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) እስከ መጪው መስከረም ወር ድረስ 20 ሚሊዮን ይጠጋል ተብሎ እንደሚታሰብ ተናግረዋል።
በሚቀጥለው ዓመት ፋይዳ መታወቂያ ያላቸው ዜጎችን ቁጥር ወደ 60 እና 70 ሚሊዮን ለማድረስ እንደሚታሰብ ጠቁመዋል።
" በቀጣይ 2 እና 3 ዓመታት ውስጥ እያንዳንዱ ሰው የሚታወቅ ከሆነ እንደ ሀገር ለብዙ ነገር ለፕላኒንግ፣ ለገቢ፣ ለንግድ ፣ ለመተማመን ያግዛል " ብለዋል።
" ፋይዳ ፋይዳው የጎላ ነው " ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፋይዳ ፦
- የሚፈጸሙ ህገወጥ ንግዶችን ለመከላከል
- መጭበርበሮችን ለመቀነስ
- ያልተስተካከለውን የንግድ ስርዓት ለማሻሻል
- ለኢኮኖሚው
- መተማመንን ለመገንባት
- ለአጠቃላይ የንግድ ስርዓቱ
- ለሰላም እና ደህንነቱ
- ወጥቶ ለመግባቱ
- አገልግሎት ለማግኘቱ ... በአጠቃላይ በሁሉም መስክ ያለው ሚና ከፍተኛ እንደሆነ አስረድተዋል።
ፋይዳ ብዙ ሴክተሮችን የሚነካ መሆኑን በመጠቆም " እያንዳንዱ ዜጋ ሊኖረው የሚግባ ነገር ነው " ሲሉ ገልጸዋል።
እያንዳንዱ ሰው መታወቅ እንዳለበትም አስገንዘበዋል።
" ፋይዳን የተገበሩ ሀገራት ተጠቅመዋል የተዘናጉ ሀገራት ደግሞ የደረሰባቸው ጉዳት አለ " ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) " አፍሪካ ውስጥ የሞከሩ ሀገራት አሉ በትክክል ግን በእኛ በዲጂታል አይዲ መልክ አይደለም የሞከሩት እኛ የጀመርነውን ዲጂታል አይዲ ለመማር ብዙ የአፍሪካ ሀገራት በገንዘብ ውልም ጭምር ጥያቄ እያቀረቡ ነው ያሉት ፤ እኛም የሚሳካልን ለሌሎችም ትምህርት የሚሆን ስራ እንደምንሰራ ተስፋ አደርጋለሁ ጥቅሙም ከፍተኛ ነው " ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
#Digital_ID #National_ID #Ethiopia
@tikvahethiopia

😡1.94K❤671👏151😭90🤔64🕊40🙏38💔35😱23😢12🥰6