TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.9K photos
1.5K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ሾኔ ከ500 በላይ የሾኔ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሠራተኞች የሥራ ማቆም አድማ ላይ እንደሚገኙ ተሰማ። በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፤ ሐዲያ ዞን ሾኔ ከተማ ፣ ላለፉት 3 ወራት የተቋረጠባቸው ደመወዝ እንዲከፈላቸው ያቀረቡት ተደጋጋሚ ጥያቄ ምላሽ አለማግኘቱን የገለጹ የሾኔ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሠራተኞች በሥራ ማቆም አድማ ላይ እንደሚገኙ ቪኦኤ አማርኛ ዘግቧል። በጊዜያዊ ውል የተቀጠሩትን ጨምሮ…
#Update

🔹 " የፌዴራሉ መንግሥት ያለንበትን ሁኔታ አይቶ መፍትሄ እንዲሰጠን እንፈልጋለን፤ ... ጥያቄያችንን በወከልናቸው ሰዎች ለማቅረብም ወደ አዲስ አበባ ለመሄድ ዝግጅት እያደረግን ነው " - ነዋሪዎች

🔹" ሳንበላ ማከም አንችልም " - የጤና ባለሞያዎች

▪️ ባለስልጣናት ስለጉዳዩ አስተያየት እንዲሰጡ ሲደወልላቸው ስልክ አያነሱም አንዳንዶቹ ስልካቸው ዝግ ነው።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፣ ሃዲያ ዞን ፣ የምስረቅ ባድዋቾ ወረዳ ነዋሪዎች የህክምና እና የትምህርት አገልግሎት በመቋረጡ መቸገራቸውን እየገለፁ ይገኛሉ።

ምንም እንኳን የሰራተኞች የወራት ደመወዝ  ባለመከፈሉ የህክምና እና የትምህርት አገልግሎት ከተቋረጠ ቀናት ቢያልፉም እስከአሁን መፍትሄ እንዳልተገኘ ከነዋሪዎች ተሰምቷል።

የመንግሥት ሠራተኞች የጀመሩት የሥራ ማቆም አድማ ዛሬ ሰኞ ሁለተኛ ሳምንቱን ያስቆጠረ ሲሆን ሠራተኞቹ የሥራ ማቆም አድማውን ማካሄድ የጀመሩት  ካለፈው ሐምሌ ጀምሮ ያለው ደሞዛቸው እንዲከፈላቸው በመጠይቅ ነው።

ነዋሪዎቹ ምን አሉ ?

(በዶቼ ቨለ ሬድዮ)

- የወረዳው ሀኪሞችና መምህራን ደሞዝ አልተከፈለንም በሚል ሥራ ካቆሙ ሁለት ሳምንት አስቆጥረዋል። በዚህ ምክንያት ልጆቻችን ቤት ለመዋል ተገደዋል፤ የታመሙ ሰዎችም ህክምና ለማግኘት ተቸግረዋል።

- በሠራተኞቹ አድማ የተነሳ በወረዳው የሚገኙ መንግሥታዊ ተቋማት አሁን ድረስ አገልግሎታቸው እንደተስተጓጎለ ነው።

- የሾኔ ሆስፒታልን ጨምሮ የህክምና ተቋማትና ትምህርትት ቤቶች ሙሉ በሙሉ በመዘጋታቸው ለከፍተኛ ችግር ተደራገናል።

- በሠራተኞች ደሞዝ አለመከፍል ምክንያት የተቋረጡ የአገልግሎት መስጫ ተቋማትን ለማስቀጠል በአካባቢው ባለሥልጣናት በኩል የሚደረግ ጥረት የለም።

- ችግሩ ከወረዳ፣ ከዞኑና ከክልሉ አቅም በላይ የሆነ ይመስላል። የፌዴራሉ መንግሥት ያለንበትን ሁኔታ አይቶ መፍትሄ እንዲሰጠን እንፈልጋለን። ጥያቄያችንን ለማቅረብም በወከልናቸው ሰዎች አማካኝነት ወደ አዲስ አበባ ለመሄድ ዝግጅት እያደረግን ነው።

የመንግሥት ባለልስጣናት ምን ምላሽ ሰጡ ?

ሬድዮ ጣቢያው የምሥራቅ ባድዋቾ ወረዳ አስተዳደር፣ የሃድያ ዞን የሰው ሀብት ልማትና የመንግሥት አገልግሎት መምሪያ እና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የፋይናንስ ቢሮ ሃላፊዎችን ለማነጋገር ጥረት ቢያሰርግም ባለሥልጣናቱ " ስብሰባ ላይ ስለሆንን ቆይታችሁ ደውሉ " የሚል ምላሽ ከሰጡ በኃላ በተባለው ሰዓት ሲደወልላቸው አንዳንዶች ጭራሽ ጥሪ አይመልሱም፤ የተቀሩት ደግሞ ሥልካቸው ተዘግቷል።

በሌላ በኩል ፤ የአካባቢው ባለሥልጣናት ትናንት እሑድ የሾኔ ሆስፒታል ሠራተኞችን ያነጋገሩ ቢሆንም ከስምምነት ሳይደርሱ መቅረታቸውን አንድ የሆስፒታሉ ሠራተኛ አሳውቀዋል።

ሠራተኛው ስብሰባውን ለጠሩት የወረዳው አመራሮች " ሳንበላ ማከም አንችልም " የሚል ምላሽ መሰጠቱን የጠቀሱት እኝሁ አስተያየት ሰጪ " መጀመሪያ ደሞዛችንን አስገቡልንና ወደ ሥራ እንመለሳለን የሚል ምላሽ ከሠራተኛው በኩል ተነስቷል ፤ መፍትሄው መክፈል ብቻ ነው ከዚህ ውጭ አማራጭ የለም በሚል ከአመራሮቹ ጋር ከስምምነት ሳንደርስ ቀርተናል " ብለዋል።

ቁጥራቸው ከሁለት ሺህ በላይ የሚሆኑት በሃድያ ዞን የምሥራቅ ባድዋቾ ወረዳ መንግሥት ሠራተኞች " የሠራንበት የሦስት ወር ደሞዝ ይከፈልን " በሚል ከሁለት ሳምንት በፊት ጀምሮ በሥራ ማቆም አድማ ላይ ናቸው።

ለሠራተኞቹ ደሞዝ መክፈል ያልተቻለው የቀድሞው የደቡብ ክልል ለወሰደው የአፈር ማዳበሪያ ብድር የወረዳውን ባጀት በዋስትና በማስያዙ እንደሆነ ከዚህ በፊት የወረዳው ባለሥልጣናት መግለፃቸውን ዶቼ ቨለ ሬድዮ በዘገባው አስታውሷል።

Credit - #DeutscheWelleRadio

@tikvahethiopia