#Democracy👏
" የህዝቤን ውሳኔ አከብራለሁ " - በምርጫ የተሸነፉት ባውሚያ
አፍሪካ ውስጥ የተረጋጋ ምርጫና የስልጣን ሽግግር ከሚደረግባቸው ሀገራት አንዷ ጋና ናት።
ሀገሪቱ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ አካሂዳለች።
ለውድድር የቀረቡትም ተቃዋሚው የናሽናል ዴሞክራቲክ ኮንግረስ ፓርቲው የቀድሞ ፕሬዝዳንት ጆን ድራማኒ ማሃማ እና የአሁን የገዢው ኒው ፓትርዮቲክ ፓርቲ ዕጩና የሀገሪቱ ምክትል ፕሬዝዳንት መሃሙዱ ባውሚያ ናቸው።
ውጤት ?
የቀድሞው ፕሬዝዳንት ጆን ማሃማ የገዢውን ፓርቲና የአሁኑ ምክትል ፕሬዜዳንት ባውሚያን አሸንፈዋቸዋል።
በምርጫው የተሸነፉት የገዢው ፓርቲ ዕጩ ለተፎካካሪያቸው " እንኳን ደስ አልዎት ! " ብለዋቸዋል።
ምርጫውን የተሸነፉት የገዢው ዕጩ ባውሚያ ህዝባቸውን / ጋናውያንን ለለውጥ የሰጡትን ድምጽ እና ውሳኔ እንደሚያከብሩ ተናግረዋል።
" የጋና ፕሬዜዳንት ሆነው ለተመረጡት የተከበሩ ጆን ማሃማ ስልክ ደውዬ እንኳን ደስ አለህ ብዬዋለሁ " ሲሉም ገልጸዋል።
ተመራጩ ፕሬዜዳንት ምርጫውን በማሸነፋቸው ደስታ እንደተሰማቸው ገልጸው በሀገሪቱ ያሉትን ችግሮች ለመፍታት እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል።
ተመራጩ ፕሬዜዳንት ከዚህ ቀደም እ.ኤ አ. ከሃምሌ 2012 እስከ ጥር 2017 ሀገሪቱን መርተዋል።
የምርጫው ውጤት ለሁለት ስልጣን ዘመን የቆየው የፕሬዜዳንት ናና አኩፎ ኦዶ ገዢ ፓርቲ ማብቂያ ሆኗል።
ባለፉት የስልጣን ዘመናት ጋና አይታ የማይታውቀው የኢኮኖሚ ቀውስ እንዳጋጠማት ፣ ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት እንዲሁም ከፍተኛ ዕዳ ጉድለት እንደተመዘገበ ተገልጿል።
ህዝቡም በተለይ ለተሻለ የኢኮኖሚ ለውጥ ፤ ያለው የከፋ የኢኮኖሚ ቀውስ መፍትሄ እንዲያገኝ በማሰብ የገዢውን ፓርቲ ዕጩ በድምጹ በመቅጣት ተቀናቃኙን የቀድሞውን ፕሬዜዳንት ወደ ቢሮ ለመመለስ እንደወሰነ ተመላክቷል።
የሀገሪቱ ምርጫ ትልቁ ማጠንጠኛ ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች እንደነበሩ ተሰምቷል።
አጠቃላይ የምርጫው ውጤት ግፋ ቢል ማክሰኞ ይፋ ይደረጋል።
ተሰናባቹ ፕሬዜዳንት ናና አኩፎ ኦዶ ለምን ምርጫ አልተወዳደሩም ?
በጋና የፕሬዜዳንቱ ስልጣን ገደብ አለው።
ሁለት የስልጣን ዘመን አሸንፎ ሀገር ከመራ ለሌላ የስልጣን ዘመን " ልወዳደር " ቢል አይፈቀድለትም።
በዚህም ሀገር ለመምራት የሚፈቀድላቸው የስልጣን ዘመን ገደቡ ላይ ስለደረሰና መወዳደር ስለማይችሉ ምክትል ፕሬዜዳንቱ ነው የተወዳደሩት።
ተሰናባቹ ፕሬዜዳንት ወንበሩን ለሌላ የሀገራቸው ልጅ ያስረክባሉ።
#Ghana
#Democracy #Election
#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia