TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
214 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#DAWA : በሶማሊ ክልል ዳዋ ዞን (የቦረና አጎራባች) በተከሰተ ድርቅ 25,000 ገደማ የቁም እንስሳት ማሞታቸውን የሶማሊ ክልል አደጋ መከላከል እና ዝግጁነት ቢሮ አስታውቋል።

የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ሳዲቅ አብዱቃድር ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ፥ በድርቁ የተነሳ ግመሎች እና የቀንድ ከብቶች መሞታቸውን ተናግረዋል።

አስቸኳይ ድጋፍ ካልተገኘ አሁን ከሞቱት በላይ እንስሳት ሊሞቱ ይችላሉ ብለዋል።

እስካሁን ፦

- 1,360 ግመሎች ሞተዋል።
- 21,148 ፍየሎች ሞተዋል።
- 1098 ከብቶች ሞተዋል።

አሁንም ከዚህ በላይ ቁጥር ያላቸው የሞት አደጋ ውስጥ ናቸው።

አሁን ላይ ድጋፍ እንዲደረግ የተለያየ እንቅስቃሴ መኖሩን ያሳወቁት አቶ ሳዲቅ በወረዳ ደረጃ ውሃ እንዲዳረስ ለማድረግ እና የእስሳት መኖ ከሸበሌ እና ከጅግጅጋ እንዲመጣ ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል።

በሌላ በኩል ከ83 ሺህ በላይ ነዋሪዎች አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው አቶ ሳዲቅ አሳውቀዋል።

ድጋፍ ፈላጊዎቹ ከተለያየ ቦታ ተፈናቅለው ካምፕ ውስጥ የሚገኙ ዜጎች (በቁጥር ከ33 ሺ በላይ) እንዲሁም የዛው የዳዋ ዞን ነዋሪዎች (በቁጥር ከ50 ሺ በላይ) መሆናቸውን ጠቁመዋል።

የምግብ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች እስካሁን ድጋፍ መቅረብ እንዳልጀመረ ገልፀው ከፌዴራል መንግስት ድጋፍ እንዲደረግ ጥያቄ መቅረቡን ተናግረዋል፤ ክልሉ ከሰብዓዊ ድርጅቶችም ጋር በመነጋገር ድጋፍ እንዲደረግ ለማስደረግ እየሰራ መሆኑንም ለሬድዮ ጣቢያው ጠቁመዋል።

@tikvhahethiopia
#Borana #Dawa

የIOM WASH ቡድን በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን እና ሶማሊ ክልል ዳዋ ዞን የተከሰተውን ድርቅ ለመከላከል ይረዳ ዘንድ ለህብረተሰቡ የውሃ ማጓጓዝ ስራ መስራት መጀመሩን ገልጿል።

IOM በዚህ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት በከባድ ድርቅ ለተጎዱ እና አስተማማኝ የውሃ ምንጭ ለሌላቸው ማህበረሰቦች ውሃ የማድረስ ስራ እየሰራ መሆኑን አመልክቷል።

ይህንን ተግባር ለማከናወን የጀርመን የፌደራል የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ልግስና ድጋፍ ማድረጉ ተገልጿል።

በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን እና በሶማሊ ክልል በዳዋ ዞን በከፋ ድርቅ ምክንያት በሺዎች የሚቆጠሩ እንስሳት መሞታቸው ሰዎችም በውሃ እጥረት ለከፋ ችግር መጋለጣቸው መገለፁ ይታወቃል።

@tikvahethiopia