TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia ዛሬ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ ፥ በፓሪስ ኦሎምፒክ በወንዶች ማራቶን ለኢትዮጵያ ብቸኛውን የወርቅ ሜዳሊያ ያስገኘው ጀግናው አትሌት ታምራት ቶላ 7 ሚሊዮን ብር እና የወርቅ ኒሻን ሽልማት አበርክተዋል። ለሀገራቸው የብር ሜዳልያ ላመጡት አትሌት ትግስት አሰፋ፣ አትሌት በሪሁን አረጋዊ እና አትሌት ፅጌ ዱጉማ ለእያንዳንዳቸው የ 4 ሚሊዮን ብር ሽልማት ተበርክቷል፡፡ የታምራት…
#Ethiopia
" መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ይቅርታ አድርጉልኝ ፤ ፕሬዜዳንታችንንም እዛው ሊወጡ ሲሉ ይቅርታ ጠይቂያለሁ አሁንም ይቅርታ ደግሜ ደጋግሜ ጠይቃለሁ !! " - አሰልጣኝ ገመዶ ደደፎ
አሰልጣኝ ገመዶ ደደፎ ምን አሉ ?
" የብር ጉዳይ አይደለም።
ለእኛ (ለአሰልጣኞች) እየተሰጠን ያለው Value የተለያየ ነው።
እኔ አስተማሪ ነበርኩ ፤ በአስተማሪነት ለ9 ዓመት አገልግያለሁ የጠላሁት ማንም ለሙያው ቦታ የሚሰጥ ሰው የለም።
በሀገራችን ላይ ለሙያ የሚሰጠው ክብር በጣም የሞተ ነው።
ይሄ መሆን የለበትም ሞያውን እንዴት እናሳድገው ፣ አትሌቲክሱ ወደቀ ውጤታችን ጠፋ ይባላል እዚህ ጋር ደግሞ አሰልጣኝ ይጠፋል። አትሌትን ያደረሱ አሰልጣኞች ይጠፋሉ። ስንቶቹን አሰልጣኞች እያጣን ነው።
እዚህ ጋር የሚሰጠው value ቅር ያሰኘኝ። እኔ ለታምራት የሰጡትን ኒሻን ሸልመንሃል ቢሉኝ ይሻል ነበር።
ለኔ ስሙ ይሻለልኛል። መኪና ሰጠንህ ብለው ህዝብ መሃል ተናግረው ቁልፍ እዛ ጋር ሰጥተው መኪናውን ባይሰጡኝ እና ሁለት ሚሊዮኑን ቢሰጡን ደስተኛ ነኝ።
አሁን እያልን ያለነው ለኛ የሚሰጠው value ፣ ሞራል ከገንዘቡ ይበልጣል ነው።
የገንዘብ ጉዳይ አይደለም። እኔ እኮ ከካምፓኒዎች ጋር ሰራለሁ፣ በአትሌቶች ማናጀርነት ሰራለሁ እኔ ገንዘቡ ችግሬ አይደለም። ድህነንትንም አውቀዋለሁ በድህነቴም እኖራለሁ።
የታምራት 7 ሚሊዮን ሽልማት ለኔ ይሰጠኝ እያልኩ አይደለም። ግን እኔ ከታምራት እኩል መልፋቴን፣ ከታምራት እኩል መድከሜን Value መሰጠት አለበት ነው።
እንደ ገና ልዩ ተሸላሚ ተብሎ መሸለም ያለበት ሲሳይ ለማ እንዴት አልተሸለመም ? እኔ እንዴት አድርጌ ሲሳይን አሳምኜ ፣ ታምራትን አሳምኜ ደክመን በስንት መከራ ነው ውጤቱ የመጣው። ይሄ ውጤት በስንት መከራ እንደመጣ እናውቃለን።
እኔ ጥዋት ኤርፖርት ስደርስ በጣም ነው የተሰማኝ። ሁሉም እዛ የነበረው የሚጠራው ሜዳሊያ ያመጡትን ልጆች ብቻ ነው። ሁሉም የሚጠራው ገመዶን ብቻ ነው።
' ና ገመዶ እዚህ ጋር ተቀመጥ ' ከኔ በፊት እኮ ትላንት ያኮራን ሁሴን ሽቦ አለ ፣ ትላንት በሜዳሊያ ያስደሰተን ሀጂ አዲሎ አለ፣ ትላንት ሜዳሊያ የሰጠችን አማኔ አለች። እዛ ጋር የትዕግስት ብር የአማኔ ትግል ነው። እነሱን ለይተው በጣም ነው ያስለቀሰኝ። ለነሱ በተሰጠው ክብር እምባዬን ነው የለቀኩት።
እኔን ብቻ ነው ሲጠሩ የነበረው ለምን እኔን ብቻ ይጠሩኛል ?
ይሄ ለአሰልጣኝ እየተሰጠ ያለው ክብር ከሚገባው በላይ ያንሳል። አትሌቶችም ይረሳሉ።
እኛ እያለን ያለው የሚሰጠው value ካልተስተካከለ አትሌቲክሱን ይገለዋል። ይስተካከል ነው።
እኔ የገለጽኩበት አይነት ስህተት ነው። አዎ ! እዛ መሆን አልነበረበትም። ግን አንዳንዴ ጊዜ unconscious ሆነህ እንዲህ ታደርጋለህ። ሰው ልትመታም ትችላለህ፣ ልታብድም ትችላለህ።
እኔ በውስጤ የተንጸባረቀው በፊት የነበሩ ችግሮች በሙሉ ጭንቅላቴ ውስጥ አንጸባርቀው ነው።
ያ ግን ቤተመንግስት መሆኑና ህዝቡን በማስቀየሜ የኢትዮጵያን ህዝብ በሙሉ በጣም ይቅርታ ጠይቃለሁ። ፕሬዜዳንታችንንም እዛው ሊወጡ ሲሉ ይቅርታ ጠይቂያለሁ አሁንም ይቅርታ ደግሜ ደጋግሜ ጠይቃለሁ።
የሞያ ጓደኞቼንም ይቅርታ ጠይቃለሁ።
ሰው ይሳሳታል ፤ ከስህተቱም ይታረማል።
ህዝቡ ለሙያ ክብር እንዲሰጥ መደገፍ አለበት። እኔ አስተማሪ በነበረኩ ሰዓት በጣም ያመኝ ነበር አስተምረህ ፣ የሆነ ቦታ አድርሰህ ዶክተር ይሆናል አንተ እዛው ነው ያለኸው ገጠር ነው ያለኸው የትምህርት እድል የለው፣ ከስራ ከወጣ የሚኖርበት የለውም በቃ እዛው ተገሎ ሙያው ተረግጦ ይሄዳል ይሄ መሆን የለበትም።
ገንዘቡን አሁንም ቢሆን አልቀበልም ፤ ካስተካከሉት እቀበላለሁ።
እኔ ሀገሬ ደመወዝ ከፍላኝ አታውቅም ፣ ደመወዝ ተከፍሎኝ አያውቅም። አሁን ለመጀመሪያ ጊዜ ኦሎምፒክ የሁለት ወር ደመወዝ ከፍሎናል። እኛ የምንሰራው በራሳችን ለሀገራችን ነው የምንሰራው፤ በፍጹም አይከፋንም።
ለባለሙያ የሚሰጠው ክብር እኔ አፈረጥኩት እንጂ መፍረጡ አይቀርም ነበር። ከኔ በፊት የተሸለሙትም እኮ ውስጣቸው ቅጥል ብሏል። በውስጣቸው ይዘውት ነው።
ቀጥሎ በማሰልጠኑ እቀጥልበታለሁ። "
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህ የአሰልጣኙ ቃል ለሸገር ኤፍ ኤም ስፖርት የተሰጠ መሆኑን ይገልጻል።
#CoachGemedoDedefo #Ethiopia
@tikvahethiopia