TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.4K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Telegram

የቴሌግራም መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ ፓቨል ዱሮቭ ፈረንሳይ ውስጥ ታሰረ።

በፈረንሳይ የሩስያ ኤምባሲ የዱሮቭን ሁኔታ በቅርብ እየተከታተለ ነው።

ዱሮቭ ዛሬ ፍርድ ቤት ይቀርባል።

ብሎገሮች በፈረንሳይ ኤምባሲዎች የተቃውሞ ሰልፍ እየጠሩ ናቸው።


የቴሌግራም መተግበሪያ መስራቹና ዋና ስራ አስኪያጁ ፓቨል ዱሮቭ ትላንት ቅዳሜ ምሽት ፈረንሳይ ፣ በፈረንሳይ ከፓሪስ ወጣ ብሎ በሚገኘው ቡርጌት ኤርፖርት በቁጥጥር ስር ውሏል።

ዱሮቭ በግል ጄቱ ተሳፍሮ ሊጓዝ ሲል ነው የታሰረው።

ለእረፍት ካቀናበት አዘርባጃን ተነስቶ በፈረንሳይ አድርጎ ሊጓዝ በኤርፖርቱ ባረፈበት ወቅት ነው መያዙ የታወቀው።

በፈረንሳይ የመጀመሪያ ደረጃ የፖሊስ ምርመራ አካል በሆነ የእስር ማዘዣ እንደተያዘም ነው የተነገረው።

ምርመራው ያተኮረው በቴሌግራም ሞደሬት / ቁጥጥር የማድረግ ክፍተት ላይ ነው። የፈረንሳይ ፖሊስ " ቴሌግራም የወንጀል ድርጊቶች፣ የአደገኛ እፅ ዝውውር፣ ሽብር፣ መኒ ላውንደሪንግ፣ ማጭበርበር ያለገደብ የሚተለለፉበት ሆኗል " በሚል ምርመራ ያደርጋል ነው የተባለው።

ዱሮቭ ዛሬ ፍርድ ቤት ይቀርባል ተብሏል።

ቴሌግራም በጉዳዩ ላይ እስካሁን ያለው ነገር የለም። የፈረንሳይ የውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ፖሊስም በጉዳዩ ላይ ምንም አላሉም።

የሩስያ ምክትል የዱማ አፈ-ጉባዔ ቭላዲላቭ ዳቫንኮቭ ዱሮቭ እንዲፈታ የሚጠይቅ መልዕክት ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ፅፈዋል።

እስራቱ በፖለቲካዊ ተነሳሽነት ያለውና የቴሌግራም ተጠቃሚዎችን ግላዊ መረጃ ለማግኘት መሳሪያ ሊሆን ይችላል ነው ያሉት።

በፈረንሳይ የሩስያ ኤምባሲ ጉዳዩን በቅርብ እየተከታተለ ነው።

ብሎገሮች በፈረንሳይ ኤምባሲዎች ተቃውሞ እየጠሩ ናቸው።

በርካቶች ቴሌግራም ላይ ያነጣጠረው የሃሳብ ነጻነትን መንፈግ ነው ብለዋል።

ቴሌግራም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተጠቃሚዎች እጅ በጣም መጨመራቸው ይታወቃል።

በተለይ በሩስያ፣ ዩክሬን አካባቢ እጅግ በርካታ ተጠቃሚዎች ያሉት ሲሆን በመላው ዓለም ተጠቃሚዎቹ 1 ቢሊዮን ደርሰዋል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በበርካታ የዓለም ሀገራት መሪዎች እና ባለስልጣናት ዋነኛ ተመራጭ የመልዕክት ማስተላለፊያ መድረክ ሆኗል።

ዱሮቭ የሩስያ-ፈረንሳይ ዜግነት አለው።

#TF1TV #BFM

@tikvahethiopia