TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#AtoGelesaDilbo

በኢህአዴግ የሽግግር ወቅት የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ሊቀ መንበር የነበሩትና በአሁኑ ወቅት የፓርላማ አባሉ አቶ ገላሳ ዲልቦ በድንገተኛ ህመም ከዚህ ዓለም በሞት መለያታቸውን ቤተሰቦቻቸው ገልፀዋል።

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር አንዱ መስራች የሆኑት አቶ ገላሳ ዲልቦ ባለፈው ዓመት በነበረው ምርጫ የምሥራቅ ሐረርጌ ዞን ጎላኦዳ ቁምቢ መልካ በሎ ወረዳዎችን በመወከል በግል ተወዳድረው በማሸነፍ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ነበሩ።

አቶ ገላሳ ዲልቦ ፤ ለረጅም ዓመታት በስደት ኑሯቸውን በለንደን አድርገው የነበሩ ሲሆን ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ በውጭ አገራት የነበሩ ተቃዋሚ ኃይሎች ጥሪ ማድረጋቸውን ተከትሎ ወደ አገር ቤት ከተመለሱ አንጋፋ ፖለቲከኞች መካከል አንዱ ነበሩ።

አቶ ገላሳ ፤ የተወለዱት ምሥራቅ ወለጋ ነቀምቴ ከተማ ሲሆን አንደኛ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን እዚያው ነበር የተከታሉት።

በአውሮፓውያኑ 1974 አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የገቡ ቢሆንም የመጀመሪያ ዓመት ትምህርታቸውን ሳይጨርሱ ደርግ ሥልጣን መቆጣጠሩን ተከትሎ ለትግል ወደ ሶማሊያ መሄዳቸውን በወቅቱ ተናግረው ነበር።

ሆኖም የሶማሊያ መንግስት ወደ ሀገር ስለመለሳቸው በአገር ቤት የነበረውን የትጥቅ ትግል መቀላቀላቸውንና የትግል ሕይወታቸውም በዚያው እንደተጠነሰሰ በአንድ ወቅት ለቢቢሲ ተናግረዋል።

በሽግግሩ ወቅት የኦነግ ሊቀ መንበር የነበሩት አቶ ገለሳ ፤ ከኦነግ ፓርቲ የወጡት በአውሮፓውያኑ 1998 የኦነግ መከፋፈልን ተከትሎ ሲሆን፣ "አባኦ ቃማ ጨኡምሳ" የሚባል ሌላኛውን የኦነግ ፓርቲን መስርተው በሊቀ መንበርነት ለረጅም ዓመታት ማገልግለላቸውን ቢቢሲ አስታውሷል።

አቶ ገለሳ ትላንት ለሊት በድንገተኛ ህመም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

@tikvahethiopia