#ADWA124
የአዲስ አበባ ም/ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ 124ኛውን የዓድዋ በአል አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
ም/ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ “ከ124 አመታት በፊት በሩቁ፣ በአሻጋሪ ተመልክተው በጨለማ የምንኖር ደካሞች አድርገው ለቆጠሩን በኅብረት፣ በእውቀት ብርሃን የምንኖር ፅኑ መሆናችንን በአድዋ አስተምረናል” ብለዋል።
ዓድዋ የፍቅር ፣ የመተባበር ፣ በጋራ የማደግ፣ የለጋስነት ፣ ጎረቤትን እንደራስ የመውደድ ትምህርት ኢትዮጵያውያን ሁሌም የሚያስተምሩት የእውነት መንገድ መሆኑንም ነው ም/ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ የገለፁት።
ም/ከንቲባው “የሀሰት፣ የትዕቢት፣ የመጠቃት ደንገርጋራ መንገድን ኢትዮጵያውያን እንጠላለን፣ ጠልተንም በአድዋ መንገድ እንድንፃረረው ሆነን አድገናል” ማለታቸውን የከንቲባ ፅ/ቤት አስታውቋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

በፓን አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ ዲዛይን ላይ ያተኮረ ውይይት በአድዋ ከተማ ተካሄደ። በውይይቱ የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤልን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች እና የዩኒቨርሲቲው ግንባታ ጉዳይ የሚመለከታተሉ አካላት ተገኝተው ነበር።
በተመሳሳይ ዛሬ ማለዳ የዓድዋ ድል ቀን ምክንያት በማድረግ የዓድዋ ከተማ በተካሄደ የፓናል ውይይት የፓን አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ እስካሁን ድረስ ወደተግባር ሊገባ አለመቻሉና አሁንም ድረስ በዲዛይኑ ላይ ውይይት መደረጉ ትኩረት እንዳልተሰጠው ያመላክታል ተብሏል።
የፌደራል መንግስትን ጨምሮ በሌሎች አካላት ቃል የተገባው ገንዘብ እስካሁን የት እንደደረሰ የተመለከቱ ጥያቄዎችም በተሳታፊዎች ዘንድ ተነስተዋል። በዚህም መንግስት አሁንም ቢሆን ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንዳለበት ተመላክቷል።
#ትግራይኮሚኒኬሽን #ትግራይቲቪ

የኢፌዴሪ ፕሬዝደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ 124ኛውን የአድዋ ድል በዓል ለማክበር አድዋ ከተማ ይገኛሉ። ፕሬዝደንቷ በስፍራው ሲደርሱ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ፣ የትግራይ ክልል ምክትል ርዕስ መስተዳድር ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤልና የአፍሪካ ህብረት ተወካዮችም በበዓሉ ለመታደብ በሰፍራው ይገኛሉ።
አምባሳደሮች፣ የከተማዋ ነዋሪዎችና ከተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎች የተወከሉ ከ200 በላይ የማህበረሰብ ክፍሎች አድዋ ተገኝተዋል።
PHOTO : FBC