TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#19_ዓመት ?

የ14 ዓመቷን ልጅ የደፈረው እና ሕይወቷ እንዲያልፍ ያደረገው ግለሰብ በ19 ዓመት መቀጣቱ ተሰምቷል።

ተከሳሹ አላዩ ሞገስ ደሳለኝ ይባላል።

ጥር 29 ቀን 2015 ዓ / ም ከጠዋቱ በግምት 1፡30 ሲሆን በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 02 ሽሮ ሜዳ አዲስ ተስፋ ትምህርት ቤት አካባቢ የ14 ዓመት የሆነችውን የግል ተበዳይ የምትኖርበት መኖሪያ ቤት ይገባል።

ከዛም በጥፊ በመምታት ፣ እንዳትጮህ በአፏ ውስጥ ጨርቅ በመጠቅጠቅ እና አንገቷን በሁለት እጁ አንቆ በመያዝ በኃይል የግብረ-ስጋ ግንኙነት ይፈጽምባታል።

በአፏ ውስጥ #ጨርቅ_በመጠቅጠቁ እና አንገቷን በማነቁ ምክንያት ትንፋሽ አጥሯት ሕይወቷ ሊያልፍ ችሏል።

ጉዳዩም በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ 11ኛ ወንጀል ችሎት ሲታይ ቆይቷል።

የዐቃቤ ሕግ ማስረጃ ከተሰማ በኋላ ተከሳሹ ክሱን እንዲከላከል ብይን ተሰጥቶ የመከላከያ ምስክሮችን ያሰማ ቢሆንም የቀረበበትን ክስ ግን ሊከላከል አልቻለም።

ፍ/ቤቱ በተከሳሽ ላይ የጥፋተኛነት ፍርድ በመስጠት " በ19 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ " ሲል ውሳኔ ሰጥቷል፡፡

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከፍትህ ሚኒስቴር ነው ያገኘው።

@tikvahethiopia