TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ፍትህ_ለመአዛ

በተስፋ ነዳ

እናቴ….እናቴ…ሰውየው ይታሰር! ሰውየው ይታሰር!

እንዲህ አይነት ሰቆቃ የሰማሁበት ቀን በህይወቴ ትዝ አይለኝም፡፡ በጆሮዬ የሰማሁትን ይህንኑ መዓት ለራሴ እንከዋን ደግሜ ላስበው ባልፈልግም ይህ ህመም ነገ በኔ፣ በአንተ፣ በአንቺ ጓዳ ሊፈጠር እንደማይችል ማረጋገጫ የለኝምና እያመመኝም ቢሆን ልዝለቀው፡፡

መአዛ ካሳ በመንግስት መስርያ ቤት ውስጥ በፋይናንስ ኦፊሰርነት ተቀጥራ ስትሰራ የነበረች በስነምግባሯ የተመሰገነች ሴት ነበረች፡፡ ከባለቤቷ ጋር መፋታቷ ሳያግዳት ሁለት ልጆቿን እያሳደገች የ75 ዓመት አዛውንት የሆኑት እናቷንም የምትረዳ ታታሪም ነበረች፡፡ እህቷ እንዲህ አለችኝ ‹ እኛ እኮ ለራሳችንም መሆን አቅቶናል…እሷ ግን የመንግስት ስራ እየሰራች በትርፍ ጊዜዋ ደግሞ በስልክ ድለለላ እየሰራች እየተሯሯጠች እናታችንንም የምትረዳ ነበረች፡፡›

ታድያ በዚህች ሴት ላይ አንድ ክፉ አይን አረፈ፡፡ መኩሪያ (ለጊዜው ስሙ የተቀየረ) በቅርቡ በተቀጠረችበት መስርያ ቤት ውስጥ በካሸሪነት ሲሰራ 90000 ብር ጎድሎበት ታግዶ… በኋላም ወደ ሌላ መደብ ተቀይሮ ነበረ፡፡ የመአዛን ቅጥር ተከትሎ ይህ ሰው አይኑን አሳረፈባት፡፡ ሁለት ልጆች እያሏት የ3 ወር ፅንስ እንዳላት እያወቀ አፈቀርኩሽ ይል ጀመር፡፡ ጥርጣሬ አደረብኝ! ምነነቱ ለጊዜው ሊገለፅ የማይፈልግ በስራዋ አካባቢ የሚያውቃት ሰውም ጉዳዩ የፍቅር ሳይሆን መኩሪያ እሷን ሊጠቀምባት ፈልጎ እንደነበረ…የተወሳሰቡ የፋይናንስ ኬዞችም እንደነበሩ ገለፀልኝ፡፡ ለእህቷም ይሄንነኑ አነሳሁባት ‹አዎ እሱኮ አፈቀርኩሽ ያላት ገና በገባች የመጀመርያው ቀን ነው፡፡ ልጆቿን ይዛ ስትሄድ ብስኩት ጋባዥ ይሆናል.. እኔ ራሱ ሄጄ በአንድ ቀን ነው የተግባባኝ እነደውም ግብዣ ሲያበዛብኝ ገርሞኝ ነበረ› ትላለች፡፡ እንግዲህ ይህ ያልታወቀ ተልዕኮ ያነገበ የሚመስለው የፍቅር ጥያቄ በሷም ዘንድ ተቀባይነት አላገኘም፡፡ በተደጋጋሚም እንደማትፈልገው ነግራዋለች፡፡

ጥር 1 ለእህትየው ደውሎ ነገ ነይ እስቲ እንጨዋወት ቢላትም እህትየው ግን መደወሉ እየገረማት እንደማይመቻት ትነግረዋለች፡፡ ጥር 2 መአዛ ቤቷ እንግዶች ጠርታ ስለነበረ ለመውጣት እየተቻኮለች እያለ ቢሮዋ ሆኖ አስር ጊዜ እግሩን እየዘረጋ ሊያደናቅፋት ይሞክራል፡፡ ጉዳዩ ያልገባት መአዛም ከቀልድ ቆጥራው ትቆጣዋለች፡፡ ሎከሯን ከዘጋች በኋላ ውሃዋን ልትጠጣ ስታነሳ ከለሩን ቀይሯል፡፡ ይሄ የኔ ውሃ አይደለም ተቀይሮብኛል ስትል ‹ ምን ይቀየርብሻል ከጠረጵዛ ላይ ያነሳሁልሽ የራስሽ ነው › ይላታል፡፡ መልሶ ሌላ ውሃም ያመጣላታል.. ይሄም የኔ አይደለም! ስትለው ማበድ ይጀምራል፡፡ ‹ውሃዬን ቀየርክብኝ ብላ ስሜን አጠፋች › ብሎ ይጮሃል፡፡ እንደምንም ጉዳዩ በርዶ ልትወጣ ስትል ከኋላዋ ይነካታል፡፡ ‹መአዚ እንኪ › ይላታል፡፡ ዘውር ስትል የያዘውን ጩቤ ሆዷ ውስጥ ይሰካዋል፡፡ መሰካቱም ሳያንስ ከጨጓራዋ ወደታች 15 ሲንቲሜትር ይሸነትረዋል..‹ ውስጡን አማሰለው፡፡› ትላለች እህቷ፡፡ ይሄኔ መአዛ በደመነፍስ ጩቤውን ከሆዷ አውጥታ ትይዘዋለች፡፡ እህቷ እነደነገረችኝ መአዛ በጊዜው ‹ ልሰካበት እችል እኮ ነበረ..ግን የልጆች አባት ነው…እንዴት እሱ ተሳሳተ ብዬ ልሳሳት › ብላለች፡፡ ከዚህ በኋላ ጩቤውን ወንበር ስር ወርውራ አምልጣ ብትወጣም ሰዎች ዕያዩ ..በቪድዮ እየተቀረፀ.. ሴቶች በመሆናቸው ማስጣል እቅቷቸው… በተደጋጋሚ ጀርባዋን በጩቤው ወጋት፡፡ በመጨረሻም ሰው መጥቶ አስጣላት፡፡

ከዚህ በኋላ ወደ ሆስፒታል ሄደች.. በተዐምር ተረፈች… የደሟ አይነት ጠፍቶ ለሰአታት ቆየች… ውስብስብ ህክመናን ቀዶ ህክምናን ጨምሮ አካሄደች (ብዙ ዝርዝር ጉዳዮች ስላሉት እዚ መፃፍ አስፈላጊ አይደለም፡፡) ጨጓራዋ በመቀደዱ አሲዱ ወጥቶ ሰውነቷን ጨረሰው..በፊስቱላ ተይዛ በአፏ የገባው ሁሉ በአንጀቷ ይወጣል፡፡ ይቺ ምስኪን ሴት ላይ ይሄን ጨምሮ ብ ሰቆቃ ደረሰ.. ሃኪሞች የቻሉትን ሁሉ ጥረት አደረጉ…
በዚህ ሁሉ ጊዜ የተጠርጣሪው እህት ፣ አክስት ና ሁለት ጎረምሶች ሆስፒታሉ ውስጥ ያንዣብባሉ፡፡ ከዛ አልፎም ለእህቷ የእናሳክምልሽ ጥያቄ አቀረቡ እህቷም ማንነታቸውን ባለማወቅ የመስርያ ቤት ሰው ነን ስለለዋት ‹እስካሁን የት ነበራችሁ › የሚል ወቀሳ ከማቅረብ ውጪ ጥያቄያቸውን አልገፋችም ነበር፡፡ መአዛ ግን ‹ ሊገሉኝ ውሃዬን ሊቀይሩብኝ መጡ › ብላ አበደች፡፡ በሌላኛው ቀን ተጠርጣሪው ከየት እነደሆነ ባይታወቅም በእህቱ ስልክ ደውሎ ‹ ደህና ነች በሉልኝና በዋስ ልውጣ ..ከዛ አሳክማታለሁ› አለ፡፡ እህተዋ ጥያቄውን አልተቀበለችውም፡፡

ብዙ ታሪክ ሆነ… እህትየው ትላለች.. ‹ለአንድ ለአምስት ቀን አንድ ጉዳይ ስለነበረኝ..እስራሁለት ቀን ያለ እንቅልፍ ካስታመምኳት በኋላ..ሰው ተክቼ ወጣሁ ..ደህና ነበረች..ትበላ ነበረ…ታወራ ነበረ… በሁለተኛው ቀን ነይ ተባልኩ.. ያለኔ ስለማይሆንላቸው ነው ብዬ ነበረ ያሰብኩት ግን ሲርየስ ኬዝ ነው ሲሉኝ በላዳ ስበር ሄድኩ…› እነዲህም ሆነ ያቺ ምስኪን ሴት በምን እነደሆነ ባለታወቀ ምልኩ በድንገት አብዳለች…ማንንም አታቅም..ጥቁር ሆናለች.. ትጮሃለች …ከአማኑዔል ሆስፒታል መድሃኒት መጣ..መዋጥ ስለማትችል በመርፌ ተሰጣት.. በቀጣይ ቀናትም ይኸው ህይወት ቀጠለ፡፡

ከሶስት ቀን በፊት እነቷ እጅ ላይ እነደተኛች አሸለበች፡፡ እነትየው ተከራከሩ ‹ ልጄን አትነኳት ከተነሳች ትጮሃለች.. ማነሽ አንቺ አላቅሽም ትለኛለች ካለችኝ ቀድምያት ሞታለሁ!› ግን አልፋ ነበረ፡፡

‹ገደሉኝ ..መጡ..በር ዝጉ..ውሃዬን ይቀይሩታል.. ብላ እነደጮኸች በር በሩን እነዳየች መአዛ አለፈች፡፡ ሁለት ልጆቿን ቻው እንኳን ሳትል አለፈች፡፡

የሰባት አመት የመጀመርያ ልጇ ልቅሶ ቤት ውስጥ እየዞረች ‹እናቴ የት ሄደች..የትኛው አፈር ውስጥ ነው ያለችው ትላለች፡፡› ጡት ያልጣለው ሁለተኛ ልጇ ነገር አለሙ ሳይገባው ጣቱን ይጠባል፡፡
እስከአሁን ቤተሰቦቿ ፍርድቤት ቀርበው አያቁም.. ሄደው ተከልክለው ተመልሰዋል…በስሚ ስሚ ከሚሰሙት ውጪ የክሱ ሂደት ምን ደረጃ ላይ እነዳለ አያቁም.. እበካችሁን የህግ ባለሙያዎች ድረሱ!

ሁለቱ ልጆች በቃጣይ ሊያድጉ የሚችሉት እያታቸው ዘንድ ቢሆንም አያትየውም የመኣዛን እጅ ጠብቀው አዳሪ ነበሩና ምንም ማድረግ የማይችሉ ናቸው፡፡ እባካችሁን እንድረስላቸው!
የእናቷ የባንክ አካውንት በፎቶ እስካሳውቃችሁ ድረስ ይሄን ፖስት ለወገኖቻችን በሙሉ በማድረስ ተባበሩኝ!

ለመረጃ፦
ሜሽ 0979491370
ተስፋ 0924410897 መሄድ ለምትፈልጉ አድራሻቸው ..ሳሪስ ወርቁ ሰፈር!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update #ፍትህ_ለመአዛ

"...ተጠርጣሪው አምልጧል!.."
የተበዳይዋ የመአዛ እህት ደወለችልኝ።

''ተስፋ እባክህን የምትችለውን አርግልን... ተጠርጣሪው አምልጧል። የቤቷን የልጆቿን አድራሻ ያውቃል። 'የህግ ያለህ' ብለህ ጩህልን። "

ከዚ በላይ መቀጠል አልቻለችም።

መአዛ በህክምና ላይ ሆና ስትሰቃይ ቤተሰቦቿ የህጉን ሂደት መከታተል አልቻሉም። ፖሊስም 'እየተጣራ ነው' ከማለት ውጭ ምንም መረጃ አልሰጣቸውም።

በመሀል የት ሆኖ እንደደወለ ባይታወቅም ደውሎ ' መአዛ ደህና ናት ብላችሁ አስፈቱኝ' ብሏል።

እህትየው ዛሬ ለመርማሪው ስትደውልለት ስልክ አያነሣም። በሌላ ሰው ሲደወልለት ደግሞ 'ሀኪም ቤት ስንወስደው አምልጦናል' ብሏል።

ምን አቅም አለኝ? ምን ላርግላት?
ማድረግ የምችለው ጩኸታቸውን መጮህ ነው።

እባካችሁን አጋሩልኝ
ለመረጃ 0924410897

@tsegabwolde @tikvahethiopia