TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.8K photos
1.61K videos
216 files
4.36K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ብላክማርኬት #ኤምባሲዎች " ነገር እንዳናበላሽ ነው የታገስናቸው ስራቸው ብላክ ማርኬት ማሯሯጥ የሆኑ ኤምባሲዎች አሉ " - ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በስም ያልጠቀሷቸው ኤምባሲዎች የኢትዮጵያን ሃብት በመዝረፍ እና የውጭ ምንዛሬ ቢዝነስ ላይ የተሰማሩ እንዳሉ ጠቁመዋል። " አንዳንድ ኤምባሲዎች ቀጥ ብለው የኢትዮጵያን ሃብት የመዝረፍ እና የውጭ ምንዛሬ ቢዝነስ የሚሰሩ…
#ብላክማርኬት #ፍራንኮቫሉታ

የተለያዩ ኩባንያዎች በኩባንያ ስም ፣ በፍራንኮ ቫሉታ ስም ፣ በወርቅ ንግድ ስም የኢትዮጵያን ገበያ የሚያዛቡ ግለሰቦች መኖራቸውን ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ተናግረዋል።

" ሹፌሮች ፣ ትናንሽ ስራ የሚሰሩ ሳይቀሩ የኢትዮጵያ ብላክ ማርኬት ዶላር ወደ አንዳንድ ሀገራት በባቡርና በቅጥቅጥ መኪና ይወጣል " ሲሉ ገልጸዋል።

" ከሀገር ወርቅ ይወጣል ፣ ዶላር ይወጣል ይሄን ዘረፋ መከላከል ያስፈልጋል። ህገወጥነት ፣ ኮንትሮባንድ ዘራፊዎች በውስጣችን ያሉ ሰዎች ተጨምረውበት የሚደረግ ማንኛውም ህግ ያልተከተለ ዘረፋ መከላከል አለብን " ብለዋል።

" አንዳንድ ሀገራት በዚህ መንገድ ኢትዮጵያን መዝረፍ መብት እንደሆነ አድርገው የሚያስቡ አሉ ኢትዮጵያ ግን ከብሔራዊ ጥቅሟ አንጻር ጥያቄ ስታነሳ እንደ ግስላ የሚሆኑ እኛን መዝረፍና የኛን ብሔራዊ ጥቅም አለማክበር ተገቢ አይደለም " ብለዋል።

" ከእኛ መውሰድ አስፈላጊ እንደሆነ ሁሉ ለመስጠት ዝግጁ መሆን ያስፈልጋል " ሲሉም አክለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ እነዚህ ሀገራት እነማን እንደሆኑ ግን በስም አልገለጹም።

በሌላ በኩል ፥ ጠቅላይ ሚኒስትሩ " ፍራንኮ ቫሉታ " እርማት እንደሚያስፈልገው ገልጸዋል።

" ፍራንኮ ቫሉታ አላማውን ስቶ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ሃብት ማሸሻ እየሆነ ስላለ ለሱ እርማት ማድረግ ያስፈልጋል " ብለዋል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
😡550256👏73🙏34😢22😭18🤔17🕊14🥰13😱12
#ፍራንኮቫሉታ

የጉሙሩክ ኮሚሽን በፍራንኮ ቫሉታ ግዢ የተፈፀመባቸው ሽቀጦች ከአንድ ወር ባነሰ ጊዜ ዉስጥ ወደ ሃገር እንዲገቡ ትዕዛዝ ሰጥቷል።

በፍራንኮ ቫሉታ ከውጭ የሚገቡ መሰረታዊ የፍጆታ ሸቀጦች በመደበኛ የንግድ ባንኮች የመተማመኛ ሰነድ /LC/ አማካኝነት እንዲገቡ መወሰኑን የገንዘብ ሚኒስትር ማስታወቁ ይታወሳል።

የጉምሩክ ኮሚሽን ህዳር 17 ቀን 2017 ዓ.ም. በፃፈዉ ደብዳቤ በፍራንኮ ቫሉታ ግዢ የተፈፀመባቸው ሸቀጦች በአንድ ወራት ባነሰ ጊዜ ዉስጥ ብቻ ወደ ሃገር ዉስጥ መግባት እንዳለባቸው አሳስቧል።

ኮሚሽኑ ይህን ያስተላለፈው የገንዘብ ሚኒስቴርን ዉሳኔ ተከትሎ መሆኑን ያስታወቀ ሲሆን ለሁሉም ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቶች እንዲያዉቁት አድርጓል።

መንግስት በመሰረታዊ የንግድ ሸቀጦች ላይ የምርት እጥረት እንዳይከሰት በማሰብ ለግል ባለሀብቶች ፍራንኮ ቫሉታ መፍቀዱ ይታወሳል፡፡

የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ህዳር 4 ቀን 2017 ዓ.ም. በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት ፍራንኮ ቫሉታ መሰረታዊ ሸቀጦችን ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት የምርት እጥረት እንዳይከሰት የተወሰነ እገዛ አድርጓል፡፡

ይሁን እንጂ የፍራንኮ ቫሉታ ባልተገባ መንገድ ለጥቁር ገበያ በመጋለጡ በውጭ ምንዛሬ ላይ ጫና በማሳደር ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ አመዝኗል ሲሉም ሚኒስትሩ ተናግረዋል ።

መሰረታዊ የፍጆታ ሸቀጦችን በፍራንኮ ቫሉታ ወደ ሀገር ውስጥ የማስገባት ውሳኔ ሙሉ በሙሉ እንዲቆም መደረጉንም የገለፁት አቶ አህመድ ሽዴ " በሂደት ላይ ያሉ ከውጭ የሚገቡ ሸቀጦች በሁለት ሳምንታት ውስጥ እንዲገቡ እንደሚደረግም " ተናግረው ነበር።

የጉምሩክ ኮሚሽን ከ ከጥቅም 28 ቀን 2017 ዓ.ም. በፊት የንግድ ሸቀጦች በፍራንኮቫሉታ ግዢ የተፈፀመባቸውን ሰነዶች በቅርንጫፍ ጽ/ቤት ያስመዘገቡ እና በዋና መስሪያቤት በኩል የተረጋገጡ አስመጪዎች በአንድ ወር ዉስጥ የንግድ ሸቀጣቸዉን አጠቃለዉ ወደ አገር ዉስጥ እንዲያስገቡ ነዉ ማሳሰቢያ የሰጠዉ።

መረጃው የካፒታል ጋዜጣ ነው።

@tikvahethiopia
319🙏82🕊33🥰29😡28🤔27😭18😢16👏15😱4