TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.7K photos
1.61K videos
216 files
4.36K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ኢትዮጵያን አታዋርዷት‼️

#የዩኒቨርሲቲ_ተማሪዎች እናተ ከሌላው የተሻላችሁ ናችሁ፤ ቦታው ይገባችኃላ ተብላችሁ ነው አሁን ያላችሁበት ቦታ የሄዳችሁት። ዩኒቨርሲቲ የገባችሁት ተምሮ ሀገር ለመቀየር እንጂ እርስ በርስ እየተከፋፈላችሁ እንድትጣሉ አይደለም። ዱላ፣ መሰዳደብ፣ መበሻሸቅ፣ መጠላላት ለማን ይጠቅማል?? ነገ የተሻለ ህይወት እንዲኖራችሁ አትመኙም?? ነገ የድሀውን ቤተሰባችሁን ኑሮ መቀየር አትመኙም?? ነገ ያሻችሁ አማርጣችሁ በልታችሁ፤ ያሻችሁን ገዝታችሁ ለብሳችሁ ዘንጣችሁ መኖር አትፈልጉም?? ልክ እንደ ውጪዎቹ በወጣትነታችሁ መኪና መያዝ፤ ሀገር ማገልገል፤ መሸለም፤ በህዝብ ዘንድ መወደድ አትፈልጉም??

እባካችሁ ፌሮውን፣ ዱላውን #ጣሉት! ይህ ዘመን ችግሮቻችን #በንግግር መፍታት የምንችልበት ነው።

በፈጣሪ እስከመቼ ወደኃላ እንጓዛለን?? ቢያንስ ለትንንሾቹ ልጆች አርአያ ሁኑ እንጂ!

ኢትዮጵያን በአለም ህዝብ ፊት አታዋርዷት!
ዱላውን፣ ፌሮውን ጥላችሁ እስክርቢቶ እና ወረቀት አንሱ፤ ሀገር የሚቀይር ሀሳብ አፍልቁ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia