TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
214 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Urgent🚨 በአማራ ክልል፣ በሰሜን ጎንደር ዞን ፣ ጠለምት ወረዳ በተከሰተ የመሬት መንሸራተት የበርካታ ወገኖቻችን ህይወት አልፏል። በርካቶችም ችግር ላይ ወድቀዋል፤ ተፈናቅለዋል። ለተፈናቃዮቹ አስቸኳይ ድጋፍ ያስፈልጋል። ደጋግ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ድጋፍ እንዲያደርጉ ወረዳው በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ጥሪ አቅርቧል። የወረዳው አስተዳደሪ አቶ ጋሻው እንግዳው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡት ቃል ፦ “…
#ጠለምት🚨

“ ናዳው ቀጥሏል፡፡  አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 25 ነው ” - ወረዳው

የመሬት መንሸራተት አደጋው መቀጠሉ የተነገረለት ሰሜን ጎንደር ዞን በተለይ ጠለምት ወረዳ የሟቾች ቁጥር መጨመሩን ወረዳው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎች የተከተው ይሄው አደጋ የብዙዎችን ሕይወት መቀጠፉ የሚታወስ ሲሆን፣ በተለይ በጠለምት ወረዳ አብና ቀበሌ ከመሬት መንሸራተቱ በተጨማሪ በሌሎች ቀበሌዎችም “ የህድሞ ” ቤት ናዳ አደጋ መከሰቱን ወረዳው ከሳምንት በፊት ገልጾልን ነበር፡፡

ይህ በእንዲህ እያለ፣ እስከ ነሐሴ 29 ቀን 2016 ዓ/ም ደግሞ የሟቾች ቁጥር በ15 መጨመሩን የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ጋሻው እንግዳው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

“ ናዳው ቀጥሏል፡፡ በጠለምት ወረዳ የሟቾች ቁጠር 25 ደርሷል ” ነው ያሉት፡፡

አስተዳዳሪው በዝርዝር ምን አሉ ?

“ በወረዳው በሚገኙ ቀበሌዎች በናዳና የጎርፍ አደጋ ምክንያት በሰዎችና በንብረት ላይ ጉዳት እየደረሰ ነው፡፡

ከነሐሴ 18 ቀን 2016 ዓ/ም እስከ ነሐሴ 29 ቀን 2016 ዓ/ም ድረስ ብቻ አራት ወንዶች፣ 11 ሴቶች በአጠቃላይ 15 ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል፡፡

ሁለት ወንዶችና ሁለት ሴቶች በድምሩ አራት ሰዎች ደግሞ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡

አደጋው ከተከሰተበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ነሐሴ 29 ቀን ድረስ በአጠቃላይ በወረዳው የሞቱ ሰዎች ብዛት 25 ደርሷል፡፡

የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ብዛት ደግሞ 10 ደርሷል፡፡ 456 ሰዎች የእርሻ መሬት ተጎድቶባቸዋል፡፡ 476.5 ሄክታር ሰብል ተጎድቷል፡፡

2911 እንስሳት ሞተዋል፡፡ 28 መኖሪያ ቤቶችና 236 የንብ ቀፎዎች ወድመዋል”
ብለዋል፡፡

የተለያዩ ተቋማት የተለያዩ ድጋፎችን እንዳደረጉ የገለጸው ወረዳው፣ አደጋውና መፈናቀሉ ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ በመሆኑ የተጀመረው ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርቧል፡፡

አደጋው የተከሰተው በዞኑ የተለያዩ ወረዳዎች ሲሆን፣ በተለይም ጠለምት ወረዳ አብና ቀበሌ የተከሰተው የመሬት መንሸራተት መቆም እንዳልቻለ መገለጹ ይታወሳል፡፡

በዞኑ በሚገኙ ሌሎች ወረዳዎች አደጋው በምን ደረጃ እንደሚገኝ በቀጣይ መረጃ የምናደርሳችሁ ይሆናል፡፡

ፎቶ ፦ ፋይል

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia