TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.7K photos
1.61K videos
216 files
4.36K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
እንኳን ደስ አለን!!

ለበርካታ ወራት ተቋርጦ የነበረው የTIKVAH-ETH የቋንቋ ትምህርት ከነሃሴ 1 ጀምሮ ይቀጥላል!!

#አፋን_ኦሮሞ
#ትግርኛ
#ግዕዝ.... በቀጣይ የሚካተቱት ቋንቋዎች እንደተጠበቁ ናቸው። ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል!

ኢትዮጵያን መውደድ ማለት~ቋንቋዋን፣ ባህሏን፣ ህዝቦችን መውደድ ነው!!

@Tikvahethedu በድጋሚ እንኳን ደስ አለን!

https://t.iss.one/joinchat/AAAAAEWA_-Jt2zIM5COJqw
#ግዕዝ_ባንክ

ግዕዝ ባንክ ከብሔራዊ ባንክ የሚጠበቅበትን ግማሽ ቢልዮን ብር በ1 ወር ውስጥ ለመሰብሰብ ማቀዱን ገለጸ።

ግእዝ ባንክ ከመጋቢት 2012 ዓ.ም ጀምሮ ለምስረታ ሂደት የሚያበቃውን የአክሲዮን ሽያጭ ማከናወን ቢጀምርም "በሀገሪቱ በተፈጠረው ወቅታዊ ችግር ምክንያት እንቅስቃሴው ተገትቶ ቆይቷል" ብሏል።

በዛሬው ዕለትም የተፈጠረውን መረጋጋት ከግምት ውስጥ በማስገባት ዳግም የአክስዮን ሽያጭ መጀመሩን በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።

ዳግም ሽያጭ መጀመሩንም አስመልክቶ የባንኩ መስራች የመሆን ፍላጎት ላላቸው ግለሰቦችና ድርጅቶች ከአሁን ጀምሮ በስራ ላይ ባሉ ባንኮች በተከፈተው የዝግ እና የአግልግሎት ሂሳብ ቁጥሮች የመመስረቻ አክስዮን መግዛት ይቻላል ብሏል።

ባንኩ እንዳስታወቀው፥ የአንድ አክስዮን መጠን 1000 ብር ሲሆን፤ አባል ለመሆን 5,000 ብር ክፍያ ይኖረዋል። መስራች አባል ለመሆን 50 አክስዮኖችን እና ከዚያ በላይ መግዛት ወይንም ደግሞ ከ50,000 ብር በላይ መክፈል ይጠበቃልም ተብሏል።

ባንኩ ከብሔራዊ ባንክ የሚጠበቅበትን ግማሽ ቢልዮን ብር በአንድ ወር ውስጥ ለመሰብሰብ ማቀዱን አሳውቋል።

አክስዮኑንም ሙሉ ክፍያ በመፈጸም ወይም 25 በመቶውን በቅድሚያ ከፍሎ ቀሪውን 75 በመቶውን ደግሞ ቀስ እያሉ ጠቅላላ ጉባኤ እስከሚጠራ ድረስ በመክፈል መግዛት እንደሚቻል ተጠቁሟል።

ዲያስፖራን በተመለከተ ባሉበት ሀገር መገበያያ ገንዘብ የሚገዙ ሲሆን አክሲዮኖችን ሲገዙ 5℅ የአገልግሎት ክፍያ እንዳለውም አስታውቋል።

በአጭር ጊዜ ሽያጩን ጨርሶ ወደ ስራ ለመግባት እንደሚሰራ ያሳወቀ ባንኩ፤ አክስዮን ሽያጩ ተቋርጦ በነበረበት ወቅት መስራች አባላትና ደንበኞቹ ላሳዩት ትእግስት ምስጋናውን አቅርቧል።

@tikvahethiopia
👍79275👎68😢10🙏9😱6🕊3🥰2
#ግዕዝ

ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በግዕዝ ጥናት መስክ በዶክትሬት ዲግሪ ፕሮግራም ሰልጣኞችን መቀበል ሊጀምር ነው።

ዩኒቨርሲቲው ሰልጣኞችን ተቀብሎ ለማስተማር የሚያስችለውን ስርዓተ ትምህርት እንዳዘጋጀ አሳውቋል።

ዩኒቨርሲቲው የፍላጎት ዳሰሳ ጥናት በማድረግና ስርዓተ ትምህርት በመቅረፅ ዝግጅት ሲያደረግ መቆየቱን፥ ትምህርቱን ለመጀመር በተዘጋጀ የምክክር አውደ ጥናት ላይ ተገልጿል።

የግዕዝ ቋንቋ ትምህርት በሰርተፊኬት እና በመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም ከሚሰጡ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል፦
- ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ፣
- ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ፣
- ወሎ ዩኒቨርሲቲ፣
- ጎንደር ዩኒቨርሲቲ እና ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ይጠቀሳሉ።

Via
@tikvahuniversity
163.03K👏588🙏200😡133🥰51🤔36🕊36💔32😭18😱11😢8