TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.7K photos
1.61K videos
216 files
4.36K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ዜና እረፍት‼️

ሁለት ታዋቂ የኪነ ጥበብ ባለሞያዎች ትናንት ምሽት ከዚህ አለም በሞት ተለዩ፡፡ ትናንት ምሽት በሞት የተለዩት የኪነ ጥበብ ባለሞያዎቹ #ጌታቸው_ደባልቄ እና #አሚር_ዳውድ ናቸው፡፡

አቶ ጌታቸው ደባልቄ ለረጅም ዓመታት በጸሐፊ ተውኔት እና በአዘጋጅነት ሰርተዋል፡፡ በ83 አመታቸው ያረፉት የአንጋፋው የኪነ ጥበብ ባለሞያ የቀብር ስነ ስርአት ነገ ይፈጸማል ተብሏል፡፡

በትግርኛ ዘፈኖቹ የሚታወቀው አርቲስት አሚር ዳውድ ትናንት ምሽት በመቐለ አይደር ሆስፒታል ነው ያረፈው፡፡ አርቲስቱ የግጥምና የዜማ ደራሲ ሲሆን፥ በተለይም አይሞቱም ጀጋኑና በሚለው ሙዚቃው ይታወቃል። በአርቲስቱ ህልፈት የትግራይ ክልል መንግስት የተሰማውን ሐዘን ገልጿል።

Via fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia