TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
56.9K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ‹‹ሰላም #ዋናው ትኩረታችን ነው፡፡›› ሲሉ የሽግግር አካል ኦነግ ሊቀመንበር አቶ #ገላሳ_ዲልቦ አስታወቁ፡፡ ለውጡ በመልካም መንገድ ላይ ነው የሚል እምነት እንዳላቸውም ገለጹ፡፡ ሊቀመንበሩ አቶ ገላሳ ዲልቦ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤በሀገሪቱ ችግሮች ቢስተዋሉም፤ የሚታይ ለውጥም አለ፡፡ ችግሩን ደግሞ ታግሎ መፍታት ይቻላል፡፡ ‹‹ህዝቡ ምን ይዛችሁ መጣችሁ የሚለን ከሆነ የህዝቡ ጥያቄ እንዳለ ሆኖ አንዱ ዋና ትኩረታችን ሰላም መሆኑን እገልጻለሁ፡፡ ሲሉ ሊቀመንበሩ አስታውቀዋል፡፡

via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የተባበረው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር እና የሽግግር ኦሮሞ ነፃነት ግንባር ለመዋሃድ የሚያስችላቸውን ስምምነት #ተፈራረሙ። ፓርቲዎቹ ዛሬ በመሪዎቻቸው በኩል ስምምነቱን ተፈራርመዋል። የተባበረው የኦሮሞ ነፃነት ግንባርን በመወከል አቶ #ገላሳ_ዲልቦ እና የሽግግር ኦሮሞ ነፃነት ግንባርን በመወከል ደግሞ #አባነጋ_ጃራ ስምምነቱን ተፈራርመዋል። እንደ ኤፍ ቢ ሲ ዘገባ ፓርቲዎቹ ለህዝቡ ሰላም እና አንድነት በጋራ ለመስራትም በማስብ መዋሃደችውን ነው ያመለከቱት። መላው የኦሮሞ ህዝብ እና ለኦሮሞ ህዝብ የሚታገሉ ሀይሎች የመጣውን ለውጥ ወደፊት ለማስኬድ ድጋፍ እንዲያደርጉ ብሎም በጋራ ተሰባስበው እንዲሰሩ ጥሪ አቅበዋል።

Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia