TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.7K photos
1.6K videos
216 files
4.36K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update አዲስ አበባ⬆️

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 በተለምዶ ዘይት መጭመቂያ ተብሎ በሚጠራው ቦታ ጤፍን ከባዕድ ነገሮች ጋር በመቀላቀል እንጀራ በሚሸጡ ግለሰቦች ላይ በህብረተሰቡ #ጥቆማ በቁጥጥር
ስር ውሏል፡፡

ወ/ሪት ወርቄና ትዕግስት አዳነ እንጀራ በመጋገር ለአንድ ወር ሰርተዋል፡፡

በቆይታቸውም 45 ኪሎ ግራም ጤፍን 100 ኪሎግራም ጀሶ ጋር በመቀላቀል ለባለሱቆች ያከፋፍላሉ፡፡

የማይሸጥና የተበላሸ እንጀራን #ጀሶ ከተቀላቀለበት ጤፍ ጋር እንደገና
በመቀላቀል ለጥቅም እንደሚውል የታዘቡትን ያስረዳሉ፡፡

በህብረተሰቡ ላይ ብዠታ የሚፈጥሩ ነገሮችን ለፖሊስና ጉዳዩ ለሚመለከታቸው አካላት ጥቆማ መስጠት እንደሚገባ ለዳት ሳጅን ተክሌ በቀለ ጠቁመዋል፡፡

የቦሌ ክፍለ ከተማ የምግብና መድሀኒትና ጤና እንክብካቤ አስተዳደር ቁጥጥር ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ በሐይሉ ዘለቀ በተገኘው ጥቆማ መሰረት ወደ ቦታው ከባለድርሻ አካላት ጋር ወደ ቦታው በመሄድ እንጀራ ጋጋሪዎች የንግድ ፍቃድና የብቃት ማረጋገጫ የሌላቸው መሆኑን ጠቅሰው ለእንጀራ የሚውል ሶስት ኩንታል #ባዕድ ነገር ማግኘታቸውን ተናግረዋል፡፡

ጤፍን ከባዕድ ነገር ጋር ቀላቅለው በሚሸጡ ግለሰቦች ላይ የማያዳግም እርምጃ እንደሚወሰድ አስታውቀዋል፡፡

ምንጭ: የክ/ከተማውን ኮምኒኬሽን ቢሮ
@Ttsegabwolde @tikvahethiopia