TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update በሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ዳግም ያገረሸውን የእሳት ቃጠሎ በማስነሳት የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አንድ የአካባቢው ባለስልጣን ተናገሩ። ካለፈው ሰኞ አመሻሽ ጀምሮ እንደገና የተነሳው እሳት በፓርኩ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ነው ተብሏል።

በአማራ ክልል የደባርቅ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ምርኩዝ ዋሴ ለዶይቼ ቬለ እንደተናገሩት በፓርኩ ላይ “ሆን ብለው እሳቱን ለኩሰዋል” የተባሉ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል። ስለ ተጠርጣሪዎቹ ብዛትም ሆነ እንዴት ቃጠሎው እንደተነሳ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት የተቆጠቡት የወረዳው አስተዳዳሪ በአሁኑ ወቅት በፓርኩ ውስጥ “እሳቱ በከፍተኛ ሁኔታ እየተቀጣጠለ” እንዳለ አስረድተዋል።

የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የህብረተሰብ እና ቱሪዝም ሀብት ኃላፊ አቶ ታደሰ ይግዛው ቃጠሎው እንዴት ተነሳ የሚለውን ለማወቅ “አሁን ጊዜው ገና ነው” ብለዋል፡፡ ቃጠሎው በንፋስ ታግዞ ከፍተኛ ውድመት እያደረሰ እንዳለ እና እሳቱን ለማጥፋት በመረባረብ ላይ እንደሆኑም ገልጸዋል።

ባለፈው መጋቢት 19 ቀን 2011 ዓ.ም በፓርኩ የተነሳው እሳት ለሳምንት ያህል ቆይቶ መጥፋቱ አይዘነጋም። በወቅቱም ከ342 ሄክታር በላይ የፓርኩ ክፍል ተቃጥሏል፡፡ ባለፈው ሰኞ መጋቢት 30 አመሻሽ ላይ እንደገና ያገረሸው የእሳት ቃጠሎ ምን ያህል ውድመት እንዳደረሰ እስካሁን እንደማይታወቅ ኃላፊው አመልክተዋል፡፡

Via #ዶቼ_ቨለ
@tsegabwolde @tikvahethiopia