TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሀገረ አቀፍ ፈተናዎች . . .

እንደ ትምህርት ሚኒስቴር እና ሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መረጃ :

የሬሜዲያል ፈተና ፦

- በልዩ ሁኔታ የሬሜዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ የሆኑ ተማሪዎች ፈተና ዛሬ ሰኔ 30/ 2015 ዓ/ም ተጠናቋል።

(አሁን ላይ ያልተፈተኑ የግል ተማሪዎች ወደፊት በሚገለፅ ጊዜ በመስከረም 2016 ዓ/ም እንደሚፈቱ የትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል)

- በ2016 ዓ/ም ፍሬሽማን ፕሮግራም ለመከታተል ብቁ ሆነው የሚገኙ በተቋማት የውስጥ ፈተና 30 ከመቶ፣ በማዕከል የተዘጋጀው ፈተና 70 ከመቶ ተደምሮ በድምሩ 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ ይሆናሉ።

ለመጀመሪያ ጊዜ ለመንግስት እና ለግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመራቂ ተማሪዎች የሚሰጠው የመውጫ ፈተና ፦

- መውጫ ፈተና ከሐምሌ 3 እስከ ሐምሌ 8 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ይሰጣል። ውጤት ሐምሌ 10 ይገለፃል። (የጤና ተማሪዎች መውጫ ፈተና ዛሬ ተካሂዷል)

- በዘንድሮው ዓመት 169 ሺህ በላይ ተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና ይወስዳሉ።

- ለ208 የመመረቂያ ፕሮግራሞች የሚውሉ የፈተና ዓይነቶች ተዘጋጅቷል።

- ሃምሳ (50) በመቶና በላይ ያመጡ ተማሪዎች ያልፋሉ።

- ፈተናውን ያላለፉ ተማሪዎች መልሰው መላልሰው የሚወስዱበት ዕድል አለ። የመጀመሪያው ዙር ፈተና መንግሥት በራሱ መንገድ የሚያስኬደው ሲሆን ከዛ በኃላ ግን ልክ የ12ኛ ክፍል ፈተናን በግል እንደሚፈተኑት መውጫ ፈተና ላይም ተፈታኞች ዝግጁ ነን በሚሉ ሰዓት / በተዘጋጁ እና ይሄን ፈተና አልፋለሁ ብለው እራሳቸውን አብቅተው በሚመጡበት ሰዓት መፈተን ይችላሉ። ተፈትነው ሲያልፉ #ዲግሪያቸውን የሚወስዱበት አሰራር አለ።

- የመውጫ ፈተና ሙሉ በሙሉ #በኦንላይን ይሰጣል።

- የተፈታኝ ተመራቂ የተማሪዎች ስም ዝርዝር ተልኮ ወደ ዳታ ማዕከል ገብቷል።

- ለተማሪዎች ለፈተና የሚሆን ልዩ የመታወቂያ ቁጥር ይሰጣቸዋል ፤ በተሰጣቸው ቁጥር መሠረት በኦንላይን መፈተን እንዲችሉ የሚረዳ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ ተከናውኖ ፤ የሞዴል ፈተና እየወሰዱ ነው።

ለ2ኛ ጊዜ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ፦

- ብሔራዊ ፈተናው ከሐምሌ 19 እስከ 30 ቀን 2015 ዓ/ም ድረሰ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ይሰጣል።

- ለብሔራዊ ፈተናው የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ከሐምሌ 16 ቀን ጀምሮ ለዚሁ ሥራ ብቻ ዝግጁ ይሆናሉ።

- የ2015 ዓ.ም ብሔራዊ የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ለመውሰድ ከ869 ሺህ በላይ ተፈታኞች በኦንላይን መመዝገባቸውን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል፡፡

- ፈተናው ለመውሰድ 869 ሺህ 765 ተፈታኞች በኦንላይን ተመዝግበዋል።

- ለፈተናው የተመዘገቡት 503,812 የሶሻል ሳይንስ እንዲሁም 365,954 የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች ናቸው።

- የፈተና አስፈጻሚዎች፣ ሱፐርቫይዘሮች እና የፈተና ጣቢያ ኃላፊዎች ምልመላ ቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ተከናውኗል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia