TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.7K photos
1.61K videos
216 files
4.36K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አስደሳች ዜና⬆️

በአስቸጋሪ ሁኔታ በዶሮ ቤት ዉስጥ ትኖር የነበረችዉ ታዳጊ #ያብስራ_ማሬ ቃል የተገባላትን ቤት ተረከበች፡፡

ከሳምንታት በፊት በተለይ በኢቢሲ በዶሮ ቤት ዉስጥ የምትኖረዉን የታዳጊ ያብስራ ማሬን ታሪክ የተመለከቱ አቶ ሚካኤል ገብሩ የተባሉ ባለሀብት በአንድ ሚሊዮን ብር በጀት ቤት እንደሚገዙላትና ሙሉ የትምህርት ወጪዋንም እስከ ዩኒቨርስቲ እንደሚችሉ ተናግረዉ ነበር፡፡

ቃላቸዉን በመጠበቅ ከወር ባነሰ ጊዜ ቻይና ሀገር ከሚገኙ ጓደኞቸዉ አቶ አስቻለዉ በላይ ጋር በጋራ ቤቱን #ገዝተዉ አስረክበዋል፡፡

ትምህርቷንም ባቅራቢያዋ ካለ ሳዉዝ ዌስት የግል ትምህርት ቤት እንድትማር የአንድ አመት 16 ሺህ ብር ክፍያም ባለሀብቶቹ ፈጽመዋል፡፡

ያብስራ እና እናቷ ከሁለት ቀን በፊት ወደተረከቡት ቤት ሲገቡም ሙሉ የቤት ዕቃዉ ተሟልቶ የጠበቃቸዉ ሲሆን የተሰማቸዉን ስሜት በእምባ ደስታቸውን ገልፀዋል፡፡

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia