አሊባባ በኢትዮጵያ የኢንተርኔት ግብይት ሥርዓት ሊገነባ መሆኑ ተገለጸ!
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከቻይናው #አሊባባ ኩባንያ ጋር የኢንተርኔት ግብይት ስርዓት ግንባታ በትብብር ለመሥራትመስማማቱን አስታወቀ። የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር መረጃ መሰረት፤ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጅነር ጌታሁን መኩሪያ የቻይናው ግዙፉ የቴክኖሎጂ ኩባንያ አሊባባን በጎበኙበት ወቅት ከኩባንያው መስራች ጃክ ማ ጋር ባደረጉት ውይይት የኢንተርኔት ግብይት ስርዓት በኢትዮጵያ ለመዘርጋት ስምምነት ላይመደረሱን በማህበራዊ ሚዲያ ጠቁመዋል።
ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው ኢትዮጵያ #የዲጅታል ትራንስፎርሜሽን ማካሄዷ ለኢንቨስትመንት ጥሩ ዕድል እንደሚፈጥርና አሠራርን በማዘመን ረገድ ትልቅ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ እንዳለው ጠቁመዋል። በከፍተኛ አመራሮች ደረጃ የተደረገው የአሊባባን ግዙፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ጉብኝት በዘርፉ በፍጥነት ለመሰማራት እንደሚያስችልም ጠቁመዋል።
በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ የተመራው የልዑካን ቡድን የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከጥቂት ወራት በፊት ካደረጉት የግዙፉ የቴክኖሎጂው ኩባንያ አሊባባ ጎብኝት በኋላ መሆኑም ተገልጽዋል። በወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአሊባባ መስራች ከሆኑት ጃክ ማ ጋር ውይይት ማድረጋቸውና ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂው ዘርፍ ከአሊባባ ጋር በተለያዩ ዘርፎች የመሥራት ፍላጎት እንዳላት ገልጸው እንደነበርምጠቁመዋል። አያይዘውም፤ በአሊባባ የሚመራ የቴክኖሎጂ ከተማ ለመመስረትም መታሰቡን መግለጻቸው ይታወሳል።
በወቅቱ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ባደረጉት ውይይት መደሰታቸውን የተናገሩት የኩባንያው መስራች ጃክ፤ ኢትዮጵያን የኩባንያው ቁልፍ አጋር የማድረግና ከሀገሪቱ ጋር አብሮ የመሥራት ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸው ጠቁመው እንደነበር ተገልጸዋል።
Via #EPA
@tikvahethiopia