🔵 “ በጸጥታው ችግር ታካሚዎች በሰው ጫንቃ ታዝለው ነው ሆስፒታል የሚሄዱት፡፡ ተሂዶም መድኃኒት የማይገኝበት ጊዜ አለ ” - ነዋሪዎች
⚫️ “ አቅራቢዎች በቂ የመድኃኒት አቅርቦት እያመጡ አይደለም ” - የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል
በአማራ ክልል፣ ባሕር ዳር ከተማ የሚገኙ ነዋሪዎች ከሆስፒታል ውስጥ መድኃኒት ስለማይገኝ ከግል ፋርማሲዎች በከፍተኛ ዋጋ ለመግዛት እየተገደዱ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
ችግሩ የሚገጥማቸው በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ለህክምና ሲሄዱ መሆኑን ለአብነት ገልጸዋክ።
አንዳንዴም በጸጥታ ችግር መንገዶች ስለሚዘጋጉ ተመላላሽ ህክምና በወቅቱ መታከም እንዳልቻሉ አስረድተዋል፡፡
ከፍተኛ የሆነ ችግር ውስጥ ከገቡ ከዓመት በላይ እንዳስቆጠሩ ተናግረዋል።
በከተማዋ ተቋማት እንኳ ከሚከፈቱበት የሚዘጉበት ጊዜ እንደሚበዛ አስረድተዋል፡፡
በተለይ ደግሞ የጸጥታ ችግር በሚፋፋምበት ወቅት የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ሲለሚገደብ ታካሚዎች በሰው ጫንቃ ታዝለው ወደ ሆስፒታል እንደሚወሰዱ ጠቁመዋል።
በሸክም ተወስደው መድኃኒትና ሠራተኛ በሆስፒታሉ የማይገኝበት ወቅት እንዳል አስረድተዋል፡፡
በዚህም በተለይ ተመላላሽ ታካሚዎች መዳን እየቻሉ የመሞት እድላቸው እየሰፋ ነውና የሰላም ያለህ! ሲሉ ተማጽነዋል፡፡
ስማቸው እንዲነገር ያልፈቀዱ በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ውስጥ የሚሰሩ አንድ ሀኪም፣ ታካሚዎች ሆስፒታሉ ውስጥ ‘ግላቭ ብቻ ነው ያለው ሌላውን ውጪ ነው የምንገዘው’ እንዳሏቸው ገልጸዋል።
“Ampicillin፣ Gentamicin፣ Vancomicin፣ Cefepime፣ Tretionin” የሚባሉ መድኃኒቶች በሆስፒታሉ ውስጥ እንደሌሉ፣ የ“Laboratory፣ CBC፣ Serum electrolyte፣Liver function test፣ CSF analysis፣ Echo፣ CT scan” አገልግሎቶች በተሟላ ሁኔታ እየተሰጡ እንዳልሆነም ገልጸዋል፡፡
በተለይ ከሳምንታት በፊት ትራንስፖርት ተቋርጦ ስለነበር ሠራተኞቹ ሥራ ለመግባት ተቸግረው እንደነበር፣ በዚህም ታካሚዎቹ ሰርጀሪ የሚሰራላቸው ቀኑ እየተራዘመ መሆኑን አልደበቁም፡፡
ለጉዳዩን ምላሽ የጠየቅነው የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል፣ “አቅራቢዎች በቂ የመድኃኒት አቅርቦት እያመጡ አይደለም፡፡ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከጸጥታውም ይሁን ካለው የገበያ ሁኔታ ጋር ተያይዞ ማለት ነው” ብሏል፡፡
“ከዚያ በሻገር ግን ዛሬ ላይ መደበኛ ሥራችንን ለማስኬድ የሚያስችል ሰቶክም አለን፡፡ ችግሮችም ይኖራሉ ከአቅማችን በላይ በሆኑ ምክንያቶች” ነው ያለው፡፡
“በቂ ስቶኮች አንይዝም፡፡ ልናገኝ አንችልም፡፡ የ3፣ የ6 ወራት ብለን ልንገዛ አንችልም፡፡ እንገዛ ብንል በጀትም አይኖረንም አቅራቢም አናገኝም” ሲል አስረድቷል፡፡
ከጸጥታው ሁኔታ ጋር ተይይዞ ሠራተኞች አይገቡም ተብሎ ለቀረበው ቅሬታ ሆስፒታሉ ፥ “ ሠራተኞች ይገባሉ፡፡ መንገድ በተዘጋ ጊዜ በአምቡላንስ ነው የምናመጣቸው፡፡ ጦርነት በሚኖርበት ጊዜ ግን አስቸጋሪ ነው ” ሲል ገልጿል፡፡
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM