TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.7K photos
1.61K videos
216 files
4.36K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#የኢፌዴሪ_ትምህርት_ሚኒስቴር

"የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ ነው"- የትምህርት ሚኒስቴር
.
.
የግል ባለሀብት፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችንና ህብረተሰቡን በማሳተፍ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ እየሰራ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ ትምህርት ሚኒስቴር ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ትምህርት ቤቶች እንዲሰሩና መሳሪያዎች እንዲሟሉ እየተደረገ መሆኑን የሚኒስቴሩ የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር ወ/ሮ ሀረጓ ማሞ ተናግረዋል፡፡

መምህራንንና ተማሪዎችን ማብቃት፣ ለትምህርት ቤቶች ምቹ ሁኔታ መፍጠር፣ካሪኩለሞችን በተማሪው ልክ የመቅረጽ ስራዎችን በመስራት የትምህርት ጥራት ማረጋገጫ ፓኬጆች እየተተገበሩ ይገኛሉ ተብሏል፡፡

የመምህራንን አቅም በተለያዩ መርሃ ግብሮች የማሳደግ ስራ፣ በተለይም የክረምት መርሃ ግብርና አጫጭር ኮርሶችን በመስጠት የመምህራንን አቅም የማሳደግ ስራ እየተሰራ እንደሆነም ተገልጿል፡፡

ይህም የተማሪና መምህራንን ግንኙነት መልካም በማድረግ መምህሩ የተዘጋጀውን መጽሃፍ በተገቢው ሁኔታ አውቆ በማሳወቅ ለተማሪው እውቀት ለማስጨበጥ ይረዳል ነው የተባለው፡፡

የመምህራን ማህበር አደረጃጀት፣ የተማሪ ወላጅ ህብረት፣ በአገር አቀፍ ደረጃ እንዲቋቋም በማድረግ ለትምህርት ጥራት መምጣት ትኩረት መሰጠቱም ተገልጿል፡፡

የትምህርት ቤቶች መስፋፋትና ለትምህርት የሚያስፈልጉ መሳሪያዎች መሟላት ለትምህርት ጥራት የራሳቸውን አስተዋጽኦ ያበረክታሉ ያሉት ወ/ሮ ሀረጓ፣ ደረጃቸውን የጠበቁ ትምህርት ቤቶች እየተሰሩ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡

https://telegra.ph/FT-08-07

Via #ኢቲቪ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ📸የቀድሞው #የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝና የኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia