“ በአምስት ቀናት ውስጥ 7፣ ባለፉት ዓመታት ከ170 በላይ ሾፌሮች በሽፍቶች ተገድለዋል፡፡ ወደ 90 የፎቶ ማስረጃዎች አሉን ” - ጣና የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማኀበር
አሽከርካሪዎች በተለያዩ ቦታዎች ላይ በ " ሽፍቶች " መታገት እና መገደላቸው እንዳልቆመ፣ መንግስትም ሆነ የመንግስት ሚዲያዎች ለችግሩ ትኩረት እየሰጡ እንዳልሆነ ሾፌሮችና ጣና የከባድ መኪና አሽርካሪዎች ማኀበር ምሬታቸውን በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል አቤት ብለዋል፡፡
ለቲክቫህ ኢትዮጵካ ቃሉን የሰጠው ማኀበሩ ፣ ሰሞኑን እንኳ በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን 5 ሹፌርና ረዳት፣ አንድ ነጋዴ እንደተገደሉ፣ ሁለት ሰዎች ታፍነው እንደተወሰዱ ገልጿል፡፡
" መንገዱ የሱዳን ቦርደር (ድንበር) ነው፡፡ ሽንኩርት ኢምፖርት የሚደረግበት፣ ቡና፣ ባቄላ ኤክስፖርት፣ የሚደረግበት ዋና መንገድም ነው፡፡ ነገር ግን ሽፍታ ነው የሚፈነጭበት፡፡ በተደጋጋሚ ነው ይሄ ችግር የተከሰተው፡፡ ሰሚ አካላ የለም፡፡ በቃ አሽከርካሪውም ከመሄድ መቆጠብ አለበት " ብሏል፡፡
" በአምስት ቀናት ውስጥ ብቻ 7፣ ባለፉት ዓመታት ከ170 በላይ ሾፌሮች በሽፍቶች ተገድለዋል፡፡ ወደ 90 የፎቶ ማስረጃዎች አሉን፡፡ ከዛ ውጭ በማኀበራዊ ሚዲያ ያልወጣ፤ በየቦታው እተዳፈነ የቀረ ነፍስ አለ " ነው ያለው፡፡
" ችግሩ በየአካባቢው አለ " የሚለው ማኀበሩ ፣ " በኦሮሚያ ክልልም ከመተሐራና ወለጪቲ መካከል ከፍተኛ የስጋት ቀጠና ነው፡፡ ሾፌር ይዘረፋል፤ ይገደላል፤ ማንም ሳላልተቆጣጠረው ጥቃቱ አልቆመም " ሲል ወቅሷል፡፡
" በቅርቡ ደባርቅ ላይ የተገደለ ሾፌር አለ፡፡ ሁመራ መስመር ላይም የተገደለ ሹፌር አለ፡፡ በሁመራው መስመር የተገደለው ያውም የመከላከያዎችን ግዳጅ ጭኖ እየሄደ ነው፡፡ በአንድ ቀን 5 ሾፌርና ረዳት የሚገደልበት አሰቃቂ ሁኔታ ነው ያለው " ብሏል፡፡
" ትልቁ ክፍተት ፀጥታ የማስከበር ሂደቱ መላላት ነው፡፡ አግቶ ስልክ ተደደዋውሎ ገንዘብ የሚቀበልን ሽፍታን ስልክ በጂፒኤስ ጠልፎ ተከታትሎ እርምጃ መውሰድ ይቻላል፡፡ የተወሰነ ቦታ ላይ እንዲህ ቢደረግ ማንም ይህን ድርጊት አይሞክረውም " ሲል አስገንዝቧል፡፡
" ' ቴክኖሎጂውን ታጥቀናል ' እየተባለ ቴክኖሎጂው የዜጎችን ሕይወት ካልታደገ ምን ያደርጋል ? " ሲል ጠይቋል፡፡
አሽከርካሪዎችስ ምን አሉ ?
" መንግስት ሁሌ ህግ ያስከብር፤ ጥበቃ ያድርግልን ብለን ለፍልፈናል፡፡ በቃ ጉዳያችሁ አይመለከተኝም ብሎናል ማለት ነው፡፡
አሽከርካሪዎች ያላቸው አማራጭ ራሳቸውን በራሳቸው ማስከበር ነው፡፡
ችግር ወዳለበት ቦታ ባንሄድ እኮ ግብዓት ማቅረብ ሲቆም መንግስት መንገዱን ይጠብቀው ነበር፡፡
ስለዚህ አሁን የምንወቅሰው ራሳችንን ነው፡፡ ሾፌር የጫነውን ጤፍ የሚመገብ ሽፍታ ነው ሾፌርን የሚገድለው፡፡ ስለዚህ ሾፌሩም ጤፍ መጫን አቆሞ ያንበረክከዋል፡፡
ህዝብን የሚያገለግል ሾፌር ነው የሚገደለው፡፡ ስለዚህ ህዝብም አገልግሎት ሲቋረጥበት መንገዱን ወጥቶ ይጠብቃል፡፡ በቃ! መፍትሄው ይሄው ብቻ ነው፡፡
ለአመታት በተደጋጋሚ ሹፌር እየተገደለ፣ እየታገተ ስለጉዳዩ የሚዘግብ የመንግስት ሚዲያ የለም፡፡ ጎንደር ላይ ሰሞኑን እንኳ ለአገር ትልቅ አበርክቶ ያላቸው 6 ነፍሶች ወድቀው ቀርተዋል፡፡ ግን ማንም ጉዳይ አላለውም " ሲሉ በምሬት ተናግረዋል፡፡
ስለጉዳዩ ከዚህ ቀደም የጠየቅነው የትራንስፖርትና ሎጅስቲክ ሚኒስቴር ችግሩ እየቀነሰ እንደሆነ ነበር የገለጸው፣ አሽከርካሪዎች ግን እንዳውም ችግሩ እየባሰ ሂዷል ባይ ናቸው፡፡
የሚመለከታው አካላት ለጉዳዩ ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም፣ ከሆኑ በቀጣይ የምናቀርብ ይሆናል፡፡
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
😭792❤96😡38🙏33😱25😢19👏15🥰13🕊10