TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አሜሪካ ዜጎቿን ከካቡል ማስወጣቷን ቀጥላለች።

የአሜሪካ ፕሬዜዳንይ ጆ ባይደን በሰጡት መግለጫ አሜሪካ እስካሁን ድረስ 13,000 ሰዎችን ከአፍጋኒስታን ማስወጣቷን፤ ይህ በታሪክ ትልቁ እንዲሁም አስቸጋሪው እንደሆነ ተናግረዋል።

ፕሬዜዳንቱ አሜሪካ እያካሄደችው ያለው ዜጎቿን በአየር የማስወጣት ዘመቻ በታሊባን እንቅፋት እየገጠመው አይደለም ሲሉ ተደምጠዋል።

ይህም ከመከላከያ ኃላፊያቸው ጋር የተቃረነ ንግግር መሆኑ ጥያቄ አስነስቷል።

የመከላከያ ሚኒስትሩ ሎይድ ኦስቲን አርብ ዕለት ለህግ አውጪዎች እንደተናገሩት ፤ አሜሪካውያን አፍጋኒስታንን ለመልቀቅ በሚሞክሩበት ወቅት በታሊባን ታጣቂዎች እንደተደበደቡ ነው ብለው ነበር።

የእረፍት ጊዜያቸውን አቋርጠው ወደ ሥራ የተመለሱት ጆ ባይደን ትላንት በሰጡት መግለጫ ፥ "ወደ አገራችሁ መመለስ የሚፈልጉ የአሜሪካ ዜጎች ወደ ቤታችሁ እንመልሳችኋለን" ብለዋል።

ከአሜሪካዊያን በተጨማሪ ከ50 እስከ 65 ሺ የሚደርሱ ከአሜሪካ ጋር ሲሰሩ የነበሩ አፍጋኒስታናውያንንም ለማስወጣት ተመሳሳይ ቁርጠኝነት እንዳለ ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል።

ባይደን በትላንቱ መግለጫቸው ፥ ታሊባን #የአሜሪካን_ፓስፖርት የያዘ ማንኛውም ሰው ወደ አውሮፕላን ማረፊያው እንዲገባ እየፈቀደ መሆኑን ጠቅሰው የአሜሪካ ወታደሮችን ወደ ካቡል መላክ አስፈላጊ አይሆንም ብለዋል።

#ቢቢሲ በካቡል የአሜሪካ ዜጎች ወደ አውሮፕላን ማረፊያው ለመግባት እንቅፋቶች እየገጠማቸው እንደሆነ በርካታ ከካቡል የሚወጡ ዘገባዎች ያመላክታሉ ብሏል።

@tikvahethiopia