• " ቤንዝል ሙሉ በሙሉ ከጠፋ 4 ቀናት መሆኑን ተከትሎ ከስራ ውጭ ሆነናል " - በሀዋሳ ከተማና አካባቢዉ የሚገኙ አሽከርካሪዎች
• " ከጅቡቲ የተነሱ ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎች እስኪደርሱ በትእግስት ጠብቁ " - የሀዋሳ ከተማ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ
ከሰሞኑ በነዳጅ እጥረት ምክኒያት አልፎ አልፎ የነዳጅ ፕሮግራም ሲወጣ ቢቆይም ካለፉት አራት ቀናት ጀምሮ ግን ሙሉ በሙሉ ድልድል ባለመውጣቱና በከተማው ውስጥ ያሉ ሁሉም ማደያዎች " ቤንዝል የለም " በማለታቸው በከፍተኛ ሁኔታ ችግር ውስጥ ገብተናል ያሉ የሀዋሳና አካባቢው አሽከርካሪዎች ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
አሁን ላይ በህዝብ ትራንስፖርት ዘርፍ የተሰማሩ አሽከርካሪዎች ስራ መፍታታቸዉን ሲገልጹ አንዳንዶች ደግሞ እጅን አጣጥፎ ላለመቀመጥ ከህገወጥ ቤንዝል ሻጮች አንድን ሊትር እስከ ከመቶ ሀምሳ ብር በላይ እየገዙ መሆኑን ይናገራሉ።
በዚህ ደረጃ ቤንዝል መጥፋቱ ግራ አጋብቶናል የሚሉት ቅሬታ አቅራቢዎቹ አሁን ላይ አሽከርካሪዉም ማህበረሰቡም ችግር ላይ ነው ብለዋል።
የአሽከርካሪዎቹን ቅሬታ ይዘን ያነጋገርናቸው የሀዋሳ ከተማ ንግድና ገበያ ልማት ኃላፊዉ አቶ ተመስገን ችሎት " ላለፉት ሶስት ቀናት ድልድል ያልነበረው ከተማ ውስጥ የሚገኙ ማደያዎች ቤንዝል በመጨረሳቸዉ ነው " ብለዋል።
በዚህ ሰአት መንገድ የጀመሩ ነዳጅ ጫኝ ቦቴዎች ከጅቡቲ መነሳታቸውን የሚገልጽ መረጃ አለን የሚሉት ኃላፊዉ እነዚህ ቦቴዎች እስኪደርሱ ሁለት ሶስት ቀናት መታገስ ይኖርብናል ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyHW
@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM