ባለሀብቶች #የቴሌኮም ባለቤት እንዲሆኑ የሚፈቅድ የህግ ረቂቅ ቀረበ‼️
የቴሌኮም አገልግሎት ረቂቅ አዋጅ በሚል ስያሜ የተዘጋጀው ሰነድ ኢትዮጵያን በቴሌኮም ዘርፍ ለመሰማራት ለፈለገ የሀገር ውስጥም ሆነ የውጭ ባለ ሀብት ክፍት የማድረግን የመንግስትን ፍላጎት ይፋ አድርጓል። ረቂቅ አዋጁ የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ባለፈው አመት በቴሌኮም ዘርፉ እንዲተገበር ከወሰነው ሰፋ ባለሁኔታ ዘርፉን ለገበያ ክፍት የሚያደርግ ነው። ቀድሞ ተነግሮ የነበረው መንግስት የኢትዮ ቴሌኮምን አብላጫ ድርሻ ይዞ ቀሪውን ለሀገር ውስጥና ለውጭ ባለሀብቶች ድርሻ የመሸጥ ነበር።
ዋዜማ ራዲዮ የተመለከተችው ረቂቅ አዋጅ እንደሚያሳየው ግን ሀገሪቱ የቴሌኮም ዘርፏን ሰፋ አድርጋ ለገበያ እንደምትከፍት የሚያሳይ ነው። በረቂቅ አዋጁም ላይ ፣ በሌላ ህግ የተደነገገ አዋጅ ወይንም ደንብ ቢኖርም ማንኛውም የሀገር ውስጥና የውጭ ባለሀብት የቴሌኮም አገልግሎት ፣ የቴሌ ኮሚኒኬሽን ኦፕሬሽን እና የቴሌ ኮሚኒኬሽን ኔትወርክ ባለቤትነት ፍቃድ የማግኘት መብት እንዳለው ተደንግጓል። እስካሁን ለቴሌኮም ዘርፉ ግልጋሎት ላይ የዋሉ የቴሌኮም አዋጅ፣ የብሮድካስት አገልግሎት አዋጅ፣ የቴሌኮም ማጭበርበር ወንጀል አዋጅ እና የፖስታ አገልግሎት ኢንተርፕራይዝ ህጎች እንዲሻሩም በረቂቅ አዋጁ ላይ ተቀምጧል።
#የቴሌኮም_ዘርፉን እንዲቆጣጠርም የኢትዮጵያ የኮሚኒኬሽን ተቆጣጣሪ ባለስልጣን እንዲቋቋም የሚያደርግ ሰፊ አንቀጾችም በረቂቅ ህጉ ተካቷል።
በረቂቅ ህጉ መሰረት በርካታ የቴሌኮም ኩባንያዎች ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ በመሆኑ ካልተገቡ የገበያ ውድድሮች ከመቆጣጠር አንስቶ፣ የቴሌኮም አገልግሎት ፍቃድን መስጠትና በርካታ ስልጣኖች ተሰጥተውታል። የቴሌ ኮም ዘርፍ ቢሊየን ዶላሮችን የሚያንቀሳቅሱ ኩባንያዎች ያሉበት በመሆኑ ባለስልጣኑ ጠንካራና ጥቅማ ጥቅሞቻቸው የተጠበቁላቸው ሰራተኞች ሊኖሩት እንደሚገባ ባለሙያዎች ይመክራሉ።
ረቂቅ አዋጁ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጸድቆ ተግባራዊ ከሆነ የኢትዮጵያን የቴሌ ኮሚኒኬሽን ዘርፍ በብዙ መልኩ የሚያሻሽልና ለሀገሪቱም የውጭ ምንዛሬን በስፋት እንደሚያስገኝ እንዲሁም ነገሩ በጥንቃቄ ከተያዘ ለሀገሪቱ ኢኮኖሚም መልካም መሆኑን መንግስት ያስረዳል።
አሁን በብቸኝነት አገልግሎት እየሰጠ ያለው ኢትዮ ቴሌኮምም ጠንካራ ውድድር ከፊቱ እንደሚመጣበት ይጠበቃል። ይህን የመንግስት ውሳኔ አስተዋይነት ይጎድለዋል ሲሉ የሚተቹ ባለሙያዎችም አሉ።
ምንጭ፦ ዋዜማ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia

❤1
የቴልኮም ማጭበርበር ወንጀል የፈፀመው ተከሳሽ በእስራትና በገንዘብ ተቀጣ፦
ተከሳሽ #ኤልያስ_አብዱርቃድር የቴሌኮም አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ሕጋዊ ፈቃድ ሳይኖረው በህገ-ወጥ መንገድ ዓለም አቀፍ ጥሪ በማስተላለፍ የኢትዮ ቴሌኮምን ከ518 ሺ ብር በላይ እንዲያጣ በማድረጉ በፈፀመው ወንጀል በእስራትና በገንዘብ ተቀጣ፡፡
ተከሳሽ #የቴሌኮም መሳሪያዎችን ወደ ሀገር ዉስጥ ለማስገባትና ለመጠቀም ብሎም የቴሌኮም አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ሕጋዊ ፈቃድ ሳይኖረው በኮልፌ ቀራኒዎ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ቤት በመከራየት የዲንስታር ጌትዌይ የስልክ መደወያና ቲፒ ሊንክ የሚባል የቴሌኮም መሳሪያዎችን በመጠቀም የቴሌኮም አገልግሎት በመስጠት ከሐምሌ 2010 እስከ ታህሳስ 12 ቀን 2011 ዓ.ም ባለው ጊዜ 95,378.73 ደቂቃ ከውጭ ሀገር ወደ ኢትዮጵያ አለም አቀፍ የስልክ ጥሪዎችን በማስተላለፍ ኢትዮ ቴሌኮም ያገኝ የነበረዉን 18,121.96 ዶላር ወይም 518,568.70 ብር እንዲያጣ በማድረጉ በቴሌኮም ማጭበርበር አዋጅ ቁጥር 761/2004 አንቀፅ 9 (1ለ) ስር የተመለከተውን የወንጀል ድርጊት በመተላለፍ የተከሰሰ መሆኑን የዐቃቤ ሕግ የክስ መዝገብ ያስረዳል፡፡ ዐቃቤ ሕግም የሰው ምስክሮች፣ የሰነድና የኢግዚቢት ማስረጃዎችን ለፍርድ ቤቱ በማቅረብ ተከራክሯል፡፡
የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 20ኛ የወንጀል ችሎት መዝገቡን መርምሮ፣ ተከሳሽን በፈፀመው ወንጀል ጥፋተኛ በማለት ሰኔ 28 ቀን 2011 ዓ.ም በዋለው ችሎት በ10 ዓመት ጽኑ እስራት እና በ500 ሺ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ሲል ወስኗል፡፡

👍1