TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በ2 ቀን ውስጥ በጎሳ ግጭት 400 ሰዎች ሞቱ‼️

በዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ኮንጎ በታህሳስ ወር ላይ ተከስቶ በነበረ #የጎሳ_ግጭት የ400 ሰዎች ህይዎት ማለፉ ተገለፀ።

በሀገሪቱ ሰሜን ምስራቅ አካባቢ ባለፈው ታህሳስ ወር ላይ ተከስቶ በነበረው የጎሳ ግጭት በሁለት ቀናት ውስጥ ብቻ 400 የሚሆኑ ዜጎች ህይዎት አልፏል።

ግጭቱ የተፈጠረውም በዩምቢ ከተማና አካባቢው በሚገኙት #ባቴንድ እና #ባኑን በተሰኙ ጎሳዎች መካከል መሆኑ ነው የተገለፀው።

የግጭቱ ምክንያትም በአካባቢው ለመካሄድ ዝግጅት ላይ በነበረው ሀገራዊ ምርጫ ላይ በተፈጠረ አለመግባባት ነው ተብሏል።

የባቴንድ ጎሳዎች የገዢውን መንግስት መመረጥ #የሚደግፉ ሲሆን ፥ባኑኖች ደግሞ በአካባቢው እነሱን ወክሎ የሚወዳደረውን #የተቃዋሚ ፓርቲ ደጋፊዎች ነበሩ።

በተፈጠረው ግጭትም ከሞቱት ሰዎች በተጨማሪም በርካቶች ከባድና ቀላል የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል፡፡

እንዲሁም በግጭቱ ብዛት ያላቸው ሰዎች ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ መሆኑ በዘገባው ተመላክቷል።

ግጭቱን ተከትሎ የሀገሪቱ መንግስት ታህሳስ 30 ላይ በአካባቢው ሊካሄድ የነበረውን ምርጫ መሰረዙ ይታወሳል።

ምንጭ፦ fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#SUDAN

በሱዳን የዳቦ ዋጋ መናርን ተከትሎ በተቀሰቀሰው የፖለቲካ ቀውስ ምክንያት የቀድሞውን ፕሬዘዳንት ኦማር ሃሰን አልበሽርን ከስልጣን በማውረድ ብቻ አልተጠናቀቀም ነበር።

ተቃውሞን ተከትሎም የአገሪቱ ወታደራዊ ጦር ስልጣን መቆጣጠሩን ተከትሎ በሱዳን ድጋሚ የፖለቲካ ቀውስ ተከስቶ ነበር። በዚህ ምክንያት ነበር የአፍሪካ ህብረት በወቅቱ የአገሪቱን ስልጣን ተቆጣጥሮ የነበረው ወታደራዊ የሽግግር መንግስት ስልጣኑን ለሲቪል እንዲያስረክብ ያዘዋል። ይሁንና የሽግግር መንግስቱ ስልጣኑን በተባለው ጊዜ ባለማስረከቡ ምክንያት ህብረቱ ሱዳንን በጊዜያዊነት አገደ።

አሁን ላይ የሽግግር መንግስቱና #የተቃዋሚ ሃይሎች በመስማማታቸው የፕሬዘዳንትነቱን ስልጣን ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤት የጠቅላይ ሚኒስትርነትና የተወሰኑ የሚኒስትርነት ቦታዎችን ከተቃዋሚዎች በሚመረጡ ሹመኞች እንዲያዝ ተስማምተዋል።

የቀድሞው የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ምክትል ሃላፊ የነበሩት ኢኮኖሚስቱ ዶክተር አብደላ ሃምዶክ የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር ተደርገው የተሾሙ ሲሆን ካቢኔያቸውን ከትናንት በስቲያ አዋቅረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሱዳን የፖለቲካ ታሪክ የመጀመሪያዋን ሴት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርም ሾመዋል። በሱዳን የነበረው የፖለቲካ ቀውስ እየረገበ በመምጣቱና ወታደራዊ ጦሩ ስልጣኑን በከፊል በማስረከቡ የአፍሪካ ህብረት በሱዳን ላይ ጥሎት የነበረውን እገዳ ማንሳቱን አስታውቋል።

Via #ETHIO_FM
@tsegabwolde @tikvahethiopia