TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
214 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
🔈#የባለሙያዎቹድምጽ

“ የክረምት ስልጠና ሁሌም እኛን ያገለለ በመሆኑ ከፍተኛ ቅሬታ ፈጥሮብናል ” - የሳይኮሎጅና የልዩ ፍላጎት ባለሙያዎች

በተያዘው ክረምት ለመምህራን የክረምት ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል፡፡

የትምህርት ቤት ሳይኮሎጅስቶች እና የልዩ ፍላጎት ባለሙያዎች በዬጊዜው ከእንዲህ አይነት ስልጠና መገለላቸው ከፍተኛ ቅሬታ እንዳሳደረባቸው በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ቅሬታ አቅርበዋል።

ይህንን ስልጠና የሚሰጡ የዩኒቨርሲቲ መምህራንን በበኩላቸው፣ ይሄው ቅሬታ በስፋት እየተነሳ መሆኑን ገልጸዋል።

“ የአቅም ግንባታ ተብሎ በክረምት የሚሰጠው ስልጠና በተለመደው መልኩ ነው የሆነው፡፡ ማለት የሚሰጠው ለሱፐርናይዘሮች፣ ለዕርሳነ መምህራንና ለመምህራን ብቻ ነው ” የሚል ቃል ሰጥተዋል።

“ትምህርት ቤት ውስጥ ያለው Stakeholder የትምህርት ቤት Guidanace and counciling Professors, Psychologists, Special need ባሙያዎችን አላሳተፈም” ብለዋል።

አንድ የዩኒቨርሲቲ መምህር በበኩላቸው፣ “ከዚህ በፊት ያስተማርናቸው ባለሙያዎች 'ድምጽ ሁኑን እኛስ ሰዎች አይደለንምን? ስልጠናው እኛን ያገለለ ነው' የሚል ጥያቄ አላቸው እኛም ጥያቄ ፈጥሮብናል" ሲሉ ለቲክቫህ ተናግረዋል።

"በደርግ፣ በኢህአዴግ፣ በብልጽግና ጊዜም እነዚህ ባለሙያዎች የትምህርቱ አጋዥ እንዳይሆኑ ለምን እንደተፈለገ አልገባንም” ነው ያሉት።

“ግን ትምህርት ቤት ለስሙም ቢሆን አለ ‘Guidance and counciling officer’ ተብሎ፡፡ ይህም የመማር ማስተማሩን ሂደት ማገዝ በሚገባው መልኩ እንዲታገዝ ይገባል" ብለዋል።

"ክረምት ፕሮግራም ት/ቤት ላይ ሚሰሩ ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠናው የሚያስፈልጋቸው ሆኖ እያለ እንዳይሳተፉ ማድረጋቸው ከፍተኛ ቅሬታ ፈጥሮባቸዋል፡፡ እኛም እንደባለሙያ ቅሬታ ፈጥሮብናል” ሲሉ አክለዋል።

“እኔ አሁን እያሰለጠንኩ ነው፡፡ ማተሪያሉን ስናይ የሳይኮሎጅ ነው፡፡ ስናወያያቸው ለውይይት የሚቀርበው ‘የእነዚህ ባለሙያዎች አክቲቨሊ ትምህርት ቤቶቻችን ላይ አለመሳተፋቸው በመማር ማስተማር ላይ ክፍተት ፈጥሯል’” የሚል ቅሬታ እንደሚያቀርቡ ገልጸዋል።

ቅሬታ አቅራቢዎቹ፣ “ለወደፊት ምን ታስቧል? የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ለምንድን ነው የማይዘጋጅልን?” ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

ከትምህርት ሚኒስቴር ስለጉዳዩ ምላሽ የጠየቅናቸው አንድ  አካል እሳቸው የሚሰሩት ዩኒቨርሲቲዎችን የተመለከተውን እንደሆነ፣ አሁን የቀረበው ቅሬታ ግን የሚመለከተው ሌሎችን እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

ሆኖም ወደ ሌሎች አካላት ቲክቫህ ያደረገው ሙከራ ለጊዜው ያልተሳካ ሲሆን፣ ጉዳዩ እስከመጨረሻ በመከታተል የትምህርት ሚኒስቴርን ምላሽ በቀጣይ የምናቀርብ ይሆናል፡፡

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM