TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ታማኝ በየነ⬇️

ለአርቲስት #ታማኝ_በየነ የሚደረገው አቀባበል በሰላም እንዲጠናቀቅ ሁሉም ህብረተሰብ ራሱንና አካባቢውን እንዲጠብቅ የዝግጅቱ አስተባባሪ ኮሚቴ ጠየቀ።

አርቲስት፣ አክቲቪስትና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ታማኝ በየነ ቅዳሜ #ነሐሴ 26 ቀን 2010 ዓ.ም ጠዋት 1 ሰዓት ላይ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት፣ ፖለቲከኞች፣ አክቲቪስቶችና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች፣ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎችና የኃይማኖት አባቶች አቀባበል ያደርጉለታል።

የኮሚቴው አባል አቶ #የሺዋስ_አሰፋ እንደተናገሩት በአቀባበል ስነስርዓቱ ላይ ከመንግሥት የፀጥታ አካላት በተጨማሪ ኀብረተሰቡ ራሱንና አካባቢውን በመጠበቅ የአቀባበል ሥነ ስርዓቱ ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ የዜግነት ግዴታ ሊወጣ ይገባል ብለዋል።

የኮሚቴው ፀሐፊ አቶ ይድነቃቸው ከበደ በበኩላቸው የተለያዩ ዝግጅቶች የሚካሄዱ ሲሆን በዕለቱ ትያትር ቤቶች የባህል ሙዚቃና ውዝዋዜ ያቀርባሉ፤ በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ባለው ልዩ የእንግዳ ማረፊያም ታማኝ በየነ መግለጫ እንደሚሰጥ ገልጸዋል።

ከቦሌ ዓለም አቀፍ አየረ ማረፊያ እስከ ብሄራዊ ትያትር ቤት ድረስ አድናቂና ደጋፊዎቹ የአዲስ አበባና የተለያዩ አካባቢ ሰዎች በሰላማዊ ህዝባዊ ትዕይንት አቀባበል ያደርጉለታል ተብሎም ይጠበቃል ብለዋል።

በብሄራዊ ትያትር ቤት ጥሪ የተደረገላቸው ከ1 ሺህ በላይ እንግዶች በተገኙበት የተለያዩ የኪነ ጥበብ ሥራዎች እንደሚቀርቡም ገልጸዋል።

እሁድ ነሐሴ 27 ቀን 2010 ዓ.ም. ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ በሚሊኒየም አዳራሽ ከተለያዩ ዘርፎች የተመረጡ ሰዎች ንግግር ያደርጋሉ፤ አርቲስት ታማኝ በየነም የምስጋናና አጠቃላይ መልዕክት ያስተላልፋል ተብሎ ይጠበቃል።

በሚሊኒየም አዳራሽ በሚኖረው ዝግጅት 25 ሺህ ሰዎች ይሳተፋሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን የአርቲስቶችን ፍቅር፣ ተስፋ እንዲሁም አንድነትን የሚያበስሩ የጥበብ ሥራዎች ይቀርባሉ ተብሎም ይጠበቃል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ ወደ አሜሪካ ‘ግንቡን እናፍርስ ድልድዩን እንገንባ’ በሚል መርህ ተጉዘው እንደነበር የሚታወስ ሲሆን የአርቲስት ታማኝ በየነ ወደ አገር ውስጥ መግባት የድልድዩን መጠናከር የሚያሳይ ተደርጎ ተወስዷል።

©ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
«"የእገሌ ብሔር ነፃ አውጪ ነኝ!" ብሎ የሚመሰረት የብሔር ፓርቲ ያንን ማህበረሰብ ከቱርክ ወይም ከጣልያን ወይም ከእንግሊዝ አይደለም ነፃ የሚያወጣው፣ ከጎረቤቱና ከገዛ ወንድሙ እንጂ። ለዚህ ነው የብሔር ድርጅት ስሜታዊ ደጋፊ የማያጣው! "እገሌ ጨቁኖሃል እገሌ ገድሎሃል እገሌ ዘርፎሃል" እያለ ቁስሉን እየነገረ ሆ በል ከማስባል በዘለለ በዚህ በዚህ ፖሊሲ #ከርሃብ አላቅቅሃለሁ፣ በዚህ ፖሊሲ #ጤናህን እጠብቅልሃለሁ በዚህ ፖሊሲ #ኑሮህን አሻሽላለሁ ብሎ የራሱን ፕሮግራሞች ወደ ሕዝቡ አውርዶ ተፎካካሪ የሚሆን ሃሳብ አቅርቦ ሲንቀሳቀስ የማይታየው።» አቶ #የሺዋስ_አሰፋ

@tsegabwolde @tikvahethiopia