TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የሰራተኞቹ ጉዳይ ከምን ደረሰ ? " ... እንዴት ምላሽ ተከልክሎት ለሀገር የሚጠቅም ሰራተኛ ጎዳና ሲወጣ ዝም ይባላል " - ሰራተኞች የደቡብ ክልል መበቱኑን ተከትሎ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የተመደቡ የውሀ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ሰራተኞች " እስካሁን ደሞዝ ስላልተከፈለን ጎዳና ላይ ልንወጣ ነው " ማለታቸውን መረጃ ሰጥተናችሁ ነበር። በወቅቱ ይህን ችግር አስመልክተን ጥያቄ ያነሳንላቸዉ…
" ከግንቦት ወር ጀምሮ ደመወዝ መከልከላችን ተከትሎ ልጆቻችን ይዘን ጎዳና ወጥተናል " - የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ሰራተኞች
ላለፉት 6 ወራት " ስራ አልተገኘላችሁም " በሚል ወደስራ ገበታቸዉ መመለስ እንዳልቻሉ በቁጥር 206 የሚሆኑ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ሠራተኞች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ሠራተኞች እየተቆራረጠ ሲከፈላቸዉ የነበረዉ ደመወዝም " ከግንቦት ወር ጀምሮ በመቋረጡ ችግር ላይ ወድቀናል " ብለዋል።
ቅሬታቸዉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የገለጹት ሠራተኞች ምን አሉ ?
➡️ ወደ ማዕከላ ኢትዮጵያ ክልል ከተመደብን ጀምሮ በተደጋጋሚ ወደስራ እንዲመልሱንና ደሞዛችን በአግባቡ እንዲከፈለን ብንጠይቅም ምላሽ አላገኘንም።
➡️ የክልሉ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ቢሮ " ስራ አልተገኘም " የሚል ምላሽ ሲሰጠን ቢቆይም በቅርቡ ስራ መገኘቱን ተከትሎ እዚህ ግባ የማይባል ሰራተኛ ጠርቶ አብዛኛውን ሠራተኛ መተዉ አሳስቦናል።
➡️ በዚህ ህይወት በደመወዝ እንኳን ከባድ በሆነበት ወቅት ከግንቦት ወር ጀምሮ ደመወዝ መከልከላችን ልጆቻችን ለጎዳና ተዳዳሪነት እኛንም ለልመና ዳርጎናል።
➡️ ጥያቄያችንን ለክልሉ ርእሰ መስተዳድር እና ለሚመለከታቸዉ ሁሉ ካሁን በፊት ብናስገባም ምላሽ የሚባል አላገኘንም። አሁንም በድጋሜ ያለንበትን ሁኔታ ለማሳዉቅ እንቅስቃሴ ላይ ነን።
በቅርቡ የነዚህን ሠራተኞችን ጉዳይ አስመልክቶ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ጥያቄ የቀረበላቸው የክልሉ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ቢሮ ኃላፊ ኢንጅነር ሻምበል አብዬ ፥ የሠራተኛውን ችግር ለመፍታት የተለያዩ መንገዶች እንደሚጠቀሙ በመግለጽ " በቅርቡም በእጃችን ላይ የሚገቡ ስራዎች ስለሚኖሩ ወደስራ ይገባሉ የደመወዝ ችግራቸውም ይፈታል " ብለው ነበር።
#TikvahEthiopiaFmailyHW
@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
“ በ2500 ብር ደመወዝ ቤተሰብ ማስተዳደር፣ ምሳ እንኳ መመገብ አልቻልንም፡፡ በጣም ተጨቁነናል ” - የጥበቃ ሠራተኞች
የዩኒቨርሲቲ ምሩቅ ጭምር የባንክ ቤት ጥበቃ ሠራተኞች የሚከፈላቸው ደመወዛቸው እጅግ አነስተኛ በመሆኑ መመገብ እንኳ እንዳልቻሉ፣ ቀጣሪ ተቋማትም መፍትሄ እየሰጧቸው እንዳልሆነ በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል እሮሮ አሰምተዋል፡፡
ከሠራተኞቹ መካከል አንዱ፤ “ እኔ አሁን በፐብሊክ አድሚኒስትሬሽንና ዲቨሎፕመንት ማኔጅመነት ድግሪ አለኝ፡፡ 2015 ዓ/ም ነው የተመረኩት፡፡ የደረጃ እድገት አግኝቼ ወደ ባንክ ሥራ የምገባ መስሎኝ ነበር ጥበቃ የገባሁት፡፡ ግን ካለው ትንሽ ደመወዝ እንኳ ይቆርጡብናል ” ብሏል።
ቤተሰብ ጭምር የሚያስተዳድሩ የጥበቃ ሠራተኞች የሚከፈለው ደመወዝ እንኳን ቤተሰብ ለማስተዳደር ለአንድ ሰውም እንደማይበቃ ገልጸው፣ ወዴት ሂደን እንኑር ? ወደ ማንስ እንጩህ ? ሲሉ ጠይቀዋል።
ሠራተኞቹ በዝርዝር ምን አሉ ?
“ ደማታአ ጥበቃና ንግድ ሥራዎች ኃ/የተ/የግ/ማ በሚባለው ኤጀንሲ አማካኝነት ነው ወደ ባንክ ቤት ጥበቃ ሥራ የገባነው፡፡
በደብዳቤ ፣ በውል ነው የገባነው ግን የሆነ ሰበብ ፈልገው ውጣ ነው እያሉን ነው፡፡ ሲፈልጉ ' ግቡ ' ይላሉ ሲፈልጉ ደግሞ ' ውጡ ' ይላሉ፡፡
ሰዎች ነን የሆነ ችግር ሊገጥመን ይችላል፡፡ የጥበቃ መሳሪያ፣ መጸዳጃ ቤት የለንም፡፡ አሁን ደግሞ ከባንክ ቤት ቅጥር ግቢ ውጪ አስወጡን፡፡ በፊት ቅጥር ግቢ ውስጥ ነበር የምናድረው አሁን ውጪ አደረጉት፡፡
የጥበቃ መሳሪያ እንዲሰጠን ደብዳቤ ብንጽፍ 'እናንተ ደብዳቤ መጻፍ አትችሉም ' አሉና ጭራሽ የፅሑፍ ማስጠንቀቂያ ጻፉልን፡፡ በዚሁ ሳቢያ ሁለት ጓደኞቻችን ተባረዋል፡፡
በ2,500 ብር ደመወዝ ቤተሰብ ማስተዳደር፣ ምሳ እንኳ መመገብ አልቻልንም፡፡ በጣም ተጨቁነናል፡፡ ቢሮ ስንሄድ ጉዳያችንን አጣጥለው ይወነጅሉናል፡፡
በተለይ ደብዳቤ ከጻፍንላቸው ወዲህ እንደሰው አይደለም የሚቆጥሩንም፡፡ ለማን እንደሚጮህም ግራ ገባን፡፡
በውስጥ ሂደን ስናመለክት እኛኑ ነው የሚወነጅሉንና የሚያባርሩን፡፡ ይቺ 2,500 ብር ደመወዝ ለቤት ኪራይ እንኳ መሆን አትችልም።
አንድ ሰው ባንክ ቤት ጥበቃ ሲሰራ 24 በ 48 የሚባል አለ፡፡
5,000 ብር ተከፍሎን አንድ ባንክ ላይ በጥበቃ እንደምንሰራ ነው ባንኮች የሚውቁት (ዋናዎቹ ማለትነው)፡፡ ከታች ያሉት ግን በ2,500፣ በ2500 ከፋፍለው ሁለት ቅርንጫፍ ላይ ነው የሚያሰሩን፡፡
የባንክ ቤት ማናጀሮችን ስናናግር ' እኛ ምን እናድረግ የቀጠራችሁን ኤጀንሲ ጠይቁ ' እያሉ ዝም አሉን፡፡ የሚያስቡን መረጃ አጠያየቅ /አካሄድ አይችሉም ብለው ነው " ብለዋል።
ሠራተኞቹ የቀጠራቸው ኤጀንሲ ከባንክ ቤት ጋር ተነጋግሮ ችግራቸውን እንዲፈታላቸው በአንክሮ ጠይቀዋል፡፡
ለቅሬታው ምላሽ ለማግኘት ወደ ድርጅቱ ያደረግነው ሙከራ ስልክ ለማንሳት ፈቃደኛ ባለመሆኑ ለጊዜው አልተሳካም፡፡
በድጋሚ የምንጠይቃቸው ይሆናል፡፡
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
" 3 ወር ደሞዝ አልተከፈለንም " ያሉ የፐርፐዝ ብላክ ሠራተኞች የከፋ ችግር ላይ እንደሚገኙ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
ያሉበት የከፋ ችግር ታይቶ መፍትሄ እንዲፈለግላቸው ጥሪ አቅርበዋል።
ሠራተኞቹ ምን አሉ ?
" እኛ በፐርፐዝ ብላክ ኢታኤች የምንሰራ ሠረተኞች ደሞዝ ስላልተከፈለን ለከፋ ችግር ተዳርገናል።
በፐርፐዝ ብላክ ኢቲኤች የምንሰራ ሰራተኞች ደሞዝ ለ3 ወር ባለመከፈሉ ምክንያት ካለው የኑሮ ውድነት ጋር ተደማምሮ ከፍተኛ ችግር ላይ ወድቀናል።
ከዛሬ ነገ ይከፈለናል በሚል ተስፋ የቆየን ቢሆንም እስካሁን በህግ ተይዟል ከሚል ጥቅል ምላሽ ውጪ ይህ ነው የሚባል መረጃ እንኳን ማግኘት አልቻልንም።
ከእለት ወደእለት ወዳለመኖር እየተሸጋገርን ነው ፤ አልፎ ለከፍተኛ ማሕበራዊ ቀውሶች እየተዳረግን ነው።
አብዛኛው ሠራተኛ ቤት ተከራይቶ ስለሆነ የሚኖረው የቤት ኪራይ መክፈል አቅቶታል ቤተሰብ እየተበተነ ነው፤ ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት መላክ አልቻሉም።
እነዚ የጠቀስናቸው ችግሮች ከብዙ በጥቂቶቹ ናቸው የሚመለከተው አካል ያለንበትን ችግር አይቶ አፋጣኝ ምላሽ ቢሰጠን " ብለዋል።
@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔊 #የሠራተኞችድምጽ
" ቋሚ ሠራተኞች ሆነን ሳለ በደሞዝ ማሻሻያው አልተካተትንም " - የሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ መንግስት ሠራተኞች
የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ሪፎርሙን ተከትሎ የሚከሰቱ የኑሮ ዉድነትና ተያያዥ ጉዳዮችን ታሳቢ በማድረግ የመንግስት ሠራተኞች ደሞዝ ማሻሻያ ተደርጎ ከጥቅምት ወር 2017 ዓ/ም ጀምሮ ተግባራዊ የተደረገ መሆኑ ይታወቃል።
በሲዳማ ክልል፤ ሰሜናዊ ሲዳማ ዞን፤ ሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ በተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች የሚሰሩ የመንግስት ሠራተኞች ግን " ከ2012 ዓ/ም ጀምሮ በቋሚነት ተቀጥረን እየሰራን ያለን ቢሆንም በአዲሱ የመንግስት ሠራተኞች የደመወዝ ማሻሻያ አልተካተትንም " ሲሉ ቅሬታቸዉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስገብተዋል።
ቅሬታቸዉን ካደረሱን መካከል ፦
- በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን፣
- ማዘጋጃ ቤቶች፣
- በትምህርት ዘርፍ ፣
- በሴቶችና ሕፃናት እንዲሁም በሕብረት ስራ ጽ/ቤቶች የሚሰሩ ሠራተኞች ናቸው።
" በወቅቱ በአግባቡ ማስታወቂያ ወጥቶ ተመዝግበንና ተወዳድረን ማለፋችን ተረጋግጦ የቋሚነት ደብዳቤ ተሰጥቶን ላለፉት አምስትና ስድስት ዓመታት ደሞዝ ሲከፈለን በቆየንባቸው መደቦች ላይ እየሰራን ባለንበት በአዲሱ የደሞዝ ማሻሻያ አለመካተታችን ለዘርፈ ብዙ ችግሮች ዳርጎናል " ብለዋል።
" ለወረዳዉ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰዉ ሃብት ልማት ጽ/ቤት እና ለክልሉ ፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ ቅሬታችንን በአካልና በፅሁፍ ብናቀርብም ተገቢዉ ምላሽ አልተሰጠንም ጉዳዩን ለኢትዮጵያ እምባ ጠባቂ ተቋም ለማቅረብ መረጃ እያደራጀን ነው " ሲሉ ተናግረዋል።
ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡት ፤ የሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰዉ ሃብት ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሃይሉ አቢኖ ፥ " በወረዳዉ በ2012 ዓ/ም የነበረው አግባብነት በሌለው ቅጥር በአንድ መደብ ሶስትና አራት ሰዎችን በተደራራቢነት የመቅጠር ሁኔታዎች አሁን ለተፈጠረው ችግር ዋነኛ ምክንያት ሆኗል " ሲሉ ገልጸዋል።
ከዞኑና የክልሉ ፐብልክ ሰርቪስ ጋር በመናበብ መፍትሔ እያፈላለጉ ስለመሆኑም ጠቁመዋል።
በወቅቱ ይህን ተግባር የፈፀሙ አመራሮች እና የሰዉ ሃብት ልማት ኃላፊዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን የሚናገሩት ኃላፊዉ በወረዳዉ በዚህ መልክ ተጠቀጥረዉ በአዲሱ የደመወዝ ማሻሻያ ያልካተቱና በቀጣይ መፍትሔ የሚፈለግላቸዉ 470 በተለያዩ መስሪያ ቤቶች ዉስጥ የተለዩ ሰራተኞች ስለመኖራቸዉ አክለዋል።
የሰሜናዊ ሲዳማ ዞን ፐብልክ ሰርቪስና የሰዉ ሃይል ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ በዛብህ ባርሶ በበኩላቸው በ2011 እና 2012 በአከባቢው ሕገወጥ ቅጥሮች መፈፀማቸውን ገልጸዋል።
በወረዳዉ አጣሪ ቡድን ተቋቁሞ በአዲሱ ደሞዝ ያልተካተቱንና በወረዳው ቅጥር ያልተፈፀመባቸዉ ክፍት መደቦችን የመለየት ስራ መከናወኑን አንስተዉ በሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ ብቻ 407 ክፍት መደቦች መኖራቸዉን ለማወቅ መቻሉን ገልፀዋል።
የክልሉ የበላይ አመራሮች በሚያስቀምጡት አቅጣጫ መሰረት እነዚህን ሠራተኞች በነዚህ ክፍት መደቦች የመደልደልና ሌሎችም ሕጋዊ አመራጮች በመፈለግ በአጭር ጊዜ ዉስጥ እልባት ለመስጠት እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጉዳዩን እስከመጨረሻ ተከታትሎ መረጃውን ይልካል።
#TikvahEthiopiaFamilyHW