#የልብሕሙማን
የኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ህፃናት መርጃ ማዕከል ፤ በዓመት እስከ 1,500 ሰርጀሪዎች መሥራት የሚያስችል አቅም ቢኖረውም አሁን ላይ እየሰራ ያለው አንድ ሶስተኛውን መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
የማዕከሉ ሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ ምህረተዓብ ኤርሚያስ (ዶ/ር) ፤ " ማዕከሉ ባለው ሙሉ አቅም ሕክምና እንዳይሰጥ የሕክምና ግብዓቶች እጥረትና ሌሎች መሠል ምክንያቶች ፈተና ሆነዋል " ሲሉ ተናግረዋል።
" በዓመት እስከ 1,500 ሰርጀሪዎች መሥራት እንችላለን ግን አሁን እየሰራን ያለነው ግን አንድ ሦርተኛውን ነው " ብለዋል።
ወደ ማዕከሉ የሚያቀኑ ታካሚዎች " በወረፋቸው አገልግሎት አላገኘንም " የሚል ቅሬታ ሲያነሱ ይደመጣል፤ ለዚህ ችግር ምክንያቱ ምን እንደሆነ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ የቀረበላቸው ምህረተዓብ (ዶ/ር)፣ " በሕመማቸው አይነትና ከወቅቱ ካለን ዕቃ አንፃር ውጪ ወረፋ የምናስቀድምበት ምንም ምክንያት የለም " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
አክለውም ፤ አንዳንድ የሕክምና ዕቃዎች ከ10 እስከ 20፣ ከ20 እስከ 40 ኪሎ ላሉ ሕፃናት ክብደት ተብለው እንደሚወሰኑ አስረድተው፣ ታካሚዎቹ ለሕክምና በሚሄዱበት ወቅት የሚገኙት የሕክምና ዕቃዎች በዛ ክብደት ሬንጅ ውስጥ ሳይሆን ሲቀር በኋላ የተመዘገበ ሰው ሊታከም ይችላል ብለዋል።
እንዲሁም፣ አምና በነበረው ቁጥር መሠረት ከ7,500 በላይ ህፃናት ታካሚዎች ወረፋ በመጠበቅ እንደሚገኙ፣ ነገር ግን ገና የታከሙትን ሲቀናንሱበት ቁጥሩ ከፍ ወይም ዝቅ ሊል እንደሚችል ምህረተዓብ (ዶ/ር) ገጸዋል።
የልብ ሕሙማን ቁጥር እየጨመረ ነው ወይስ እየቀነሰ ?
ዶክተር ምህረተዓብ ኤርሚያስ ፦
" የታካሚዎች ቁጥር መጨመሩ አይቀርም። ምክንያቱም የሚመጡ ታካሚዎች የታመሙ ብቻ አይደሉም። የታመሙና እዚህ አገልግሎቱ እንዳለ የሚያውቁ ናቸው። ታመው አገልግሎቱ እንዳለ የማያውቁ ሰዎች አሉ። ስለዚህ እነርሱ አይመጡም።
የታካሚ ቁጥር እንዳይጨምር ማድረግ አይቻልም። የሚቻለው እዚህ ላሉ ታካሚዎች የምንሰራበትን ፍጥነት መጨመር ነው።
በእኛ ተቋም በዓመት እስከ 1,500 ሰርጀሪዎችን መስራት እንችላለን በተለያዩ ችግሮች ግን አሁን እየሰራን ያለነው አንድ ሦስተኛውን ነው። እንዲህ አይነት ተመሳሳይ ነፃ አገልግሎት የሚሰጡ የሕክምና ማዕከላት ካልተከፈቱ የሕሙማኑን ቁጥር መቀነስ ያስቸግራል። "
* የልብ ህክምና ታካሚዎች በሌሎች ተቋማት ለአንድ ቀዶ ሕክምና እስከ 500,000 ብር የሚጠየቁ ሲሆን ከፍተኛ የግብዓት እጥረትም አለ። የኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ህፃናት መርጃ ማዕከል በቅርቡ ባስጀመረ ' ተስፋ ' በሚለው የድጋፍ ሲስተም ሰዎች የሕፃናትን የልብ ህክምና ወጪ በመሸፈን እንዲያግዙ ጥሪ ቀርቧል።
ድጋፍ ማድረጊያ ፦ 6710 ላይ OK ብለው ያላኩ።
መረጃው በአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው።
@tikvahethiopia