#ትግራይ
በሚቀጥለው ሳምንት በመላ ትግራይ ክልል #የሃዘን ቀን ይታወጃል።
ይህንን ያስታወቁት የግዚያዊ አስተዳደሩ ፕረዚደንት አቶ ጌታቸው ረዳ ዛሬ የመስቀል በዓል በማስመልከት በመቐለ ከተማ ለህዝብ ባስተላለፉት መልእክት ነው።
የዘንድሮ የመስቀል በዓል ከቄየው ተፈናቅሎ በስደት በረሃብና ጥማት ከሚሰቃይ ህዝባችን በመሆን የምናከብረው መሆናችን መዘንጋት የለብንም ያሉት ፕረዚደንት ጌታቸው ረዳ " ይህንን አንፃራዊ ሰላም እንዲገኝ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰማእታት መክፈላችን መዘንጋት የለብንም " ብለዋል።
" ለህዝብ ህልውና የተሰውና አካላቸው የጎደሉ እንዲሁም ቤተሰቦቻቸው ሁሌም ሊዘከሩና ሊከበሩ ይገባል የመሰቀል በዓል ስናከብርም ብሄራዊ የሃዘን ቀን ለማዋጅ በተዘጋጀንበት ወቅት መሆኑ በማወቅ ከሰማእታት ቤተሰቦችና ለኛ ሲሉ አካላቸው የጎደሉ በቀጣይነት ለማከበር ቃል በመግባት ሊሆን ይገባዋል " ብለዋል አቶ ጌታቸው።
" ሰማእታት ስናስታውስና አካላቸው የጎደሉና ቤተሰቦቻቸው ስናከብር መስዋእት የከፈሉባቸውና አካላቸው የጎደሉባቸው ሜዳና ተራራ እንዲሁም የወደሙ መሰረተ ልማቶች በተደራጀና በተናበበ መልኩ በእልህና በቁጭት በማልማት ሊሆን ይገባል " ያሉት ፕረዚደንቱ " ግዚያዊ አስተዳደሩ በተገቢ የመምራት ሚናው ይወጣል " ብለዋል።
የተጀመረው የሰላም ስምምነት ከማፅናት ጎን ለጎን ተፈናቃዮች ወደ ቁያቸው እንዲመለሱ ፣ በሃይል የተያዙ መሬቶች ወደ ባለቤታቸው እንዲመለሱ የምናደርገው ሰላማዊና ፓለቲካዊ ትግል በመደገፍ በኩል ህዝቡ የበኩሉ እንዲወጣ አቶ ጌታቸው ረዳ ጥሪ ማቅረባቸው የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ የትግራይ ቴሌቪዥን በዋቢነት በመጥቀስ ዘግቧል።
@tikvahethiopia