TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.7K photos
1.61K videos
216 files
4.36K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሰበር ዜና‼️

አዋሽ ባንክ ጃክሮስ ቅርንጫፍ ዝርፊያ ተፈጸመበት። "ዘራፊዎቹ አምስት ናቸው። መሳሪያ የታጠቁ እና በሞተር ሳይክል የመጡ ናቸው" ብለዋል የባንኩ ተረኛ ጥበቃ ብርሃኑ ሁንዴ።

የቦሌ ወረዳ የCMC ፖሊስ ጣቢያ መርማሪ #ሚኪያስ_ደረሰ ወንጀሉ መፈፀሙን አረጋግጠዋል። ዝርዝር መረጃ ለመስጠት ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።

በስፍራው የነበረ አንድ የአይን እማኝ ደግሞ ይህን ብሏል "ተጯጩኸን ... በሕዝቡ ርብርብ አንዱን ሞተረኛ ይዘናል! ...ሌሎቹ አምልጠውናል "

የባንኩ ጥበቃ ነኝ ያሉት አቶ ብርሀኑ ሁንዴ ይህን ብለዋል፦ "የባንኩ ጥበቃ ነኝ። #መሳሪያ የያዝኩት እኔ ነበርኩ። ሽጉጥ #ደቅነው እኔንም ጓደኛዬን ወደ ውስጥ አስገቡን። ከዚያም ወደ ላይ #ተኮሱ። በያዙት ቦርሳ መጠኑ ያልታወቀ ገንዘብ #ዘርፈው አምልጠዋል። ጩኸት አሰማን። ከኅብረተሰቡ ጋር በመተባበር አንዱ ተይዟል"

ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ጌጡ ተመስገን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
1