Forwarded from BORN TO WIN
#update ልሳነ አማራ⬆️
ጋዜጠኛ እና አክቲቪስቱን #ሙሉቀን_ተስፋውን ጨምሮ የልሳነ ዐማራ አባላት የአማራ ብዙኃን
መገናኛ ድርጅትን ጎብኝተዋል፡፡ በጉብኝቱ የድርጅቱን #ዘመናዊ የሚዲያ ኮምፕሌክስ ያዩት ጎብኝዎቹ ዘመናዊ እና የተደራጀ ተቋም አይተናል ብለዋል። ድርጅቱ የአማራን ብሄርተኝነት ትኩረት አድርጎ ሊሰራ ይገባል ብለዋል፡፡ ‹‹የአማራ ብሄርተኝነት ለኢትዮጵያዊነት ዋስትና እንጅ የሚጣረስ አይሆንም፡፡›› ሲል ጋዜጠኛ እና አክቲቪስቱ ሙሉቀን ተስፋው ተናግሯል።
©አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia

አዳማ🔝
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #ዐቢይ_አሕመድ የ7ኛው የኢፌዲሪ ሀገር መከላከያ ሰራዊት ቀን ክብረ በዓል ወቅት በሰራዊቱ ያላቸውን ኩራት ገልፀዋል።
ጠ/ሚሩ በጦር ኃይሉ ውስጥ ግልጽነትና ሌሎች ክፍተቶችን ለመሙላት የተከናወኑ ዋና ዋና ለውጦችን በማንሳት የተመዝገበውንም ከፍተኛ ለውጥ አበረታች መሆኑን ገልጸዋል።
በዋናነትም ቁልፍ የሆነው የለውጡ መለያም ከፖለቲካ ወገንተኝነት የፀዳ ሙያዊ ብቃት ያለው ሰራዊት መገንባት ነው። መከላከያ ሰራዊቱን ከማዘመንና በሞያ ከማብቃት ጎን ለጎንም ጠ/ሚሩ የኢትዮጲያ ወጣቶች የጦር ሰራዊቱን #ዘመናዊ_ተቋማት_ግንባታና #የቴክኖሎጂ ልህቀት እርምጃ እንዲያግዙ ጥሪ አቅርበዋል።
ምንጭ፦ የጠ/ሚ ፅ/ቤት

#NewsAlert የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ከተሞች ምክር ቤቶች ተወካዮች እንዲሁም የአካባቢ ምርጫ ከቀጣዩ ሀገር አቀፍ ምርጫ ጋር እንዲካሄድ የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ አፀደቀ። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ አስቸኳይ ስብሰባውን በማካሄድ ላይ ይገኛል።
ምክር ቤቱ በ2011 ይካሄዳል ተብሎ የነበረውን የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ከተሞች ምክር ቤቶች አባለት ምርጫ እና የአካባቢ ምርጫ በተያዘው የጊዜ ሰሌዳ ማካሄድ ባለመቻሉ ከቀጣዩ አገር አቀፍ ምርጫ ጋር እንዲካሄድ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ያቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ ነው ያፀደቀው።
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድን #ዘመናዊ አሰራር ለማላበስ እና አዋጆችን ለማዘጋጀት እንዲሁም አዳዲስ የቦርዱን አመራር ለመምረጥ ጊዜ በመወስዱ ምርጫውን በጊዜ ሰሌዳው መሰረት ማካሄድ እንዳላስቻለ በውሳኔ ሀሳቡ ላይ ተጠቅሷል። በዚህም መሰረት ቦርዱ ለቀጣዩ ሀገር አቀፍ ምርጫ በሚያወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት የከተማዎቹ ምክር ቤቶች አባላት እና የአከባቢ ምርጫ አብሮ እንዲካሄድ ወስኗል።
Via #EPA