TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ደቡብ ክልል‼️

በደቡብ ክልል ኢትዮጵያን ከኬንያ ጋር የሚያዋስነውን ድንበር በህገ ወጥ መንገድ ሊሻገሩ ነበር የተባሉ 25 ኤርትራውያንን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የክልሉ ፖሊስ አስታወቀ። ወጣቶቹ በኬንያ አቋርጠው #ኡጋንዳ የመግባት እቅድ እንደነበራቸው ፖሊስ ገልጿል።

ኤርትራውያኑ ሐሙስ ዕለት የተያዙት በክልሉ በደቡብ ኦሞ ዞን፤ ሐመር ወረዳ ውስጥ ቱርሚ በተባለች አነስተኛ የጠረፍ ከተማ ላይ መሆኑን የዞኑ ፖሊስ ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር #ካሳ_ካውዛ ለDW ተናግረዋል፡፡ ኤርትራውያኑ በወጣትነት የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ
መሆናቸውን ኃላፊው ገልጸዋል።

“የተያዙበት ምክንያት ባልተለመደ ሁኔታ ወደዚያ በህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ከደረሱ በኋላ ከምሽቱ ሶስት ሰዓት ላይ ወደ ጭነት መኪና ተዛውረው ሊጓዙ ሲሉ በፖሊስ ጥርጣሬ ተይዘዋል። ሲታዩ ያው በኬንያ በኩል ወደ ኡጋንዳ ካምፓላ መድረስ እንፈልጋለን የሚሉ ወጣቶች
ነበሩ። ወጣቶቹ እነርሱ እንደሚሉት የኤርትራ ዜጎች ነን ነው። በእጃቸው ላይ የያዙት አንዳንድ መታወቂያዎችም ከኤርትራ ትምህርት ቤት የተነሱ መሆኑን የሚያሳዩ ናቸው። አሁን ወደ ዞናችን ፖሊስ መምሪያ አስመጥተን ወጣቶቹን በዚያው በዞናችን ፖሊስ መምሪያ ግቢ ውስጥ ይገኛሉ” ሲሉ የዞኑ የፖሊስ ኃላፊ ወጣቶቹ እንዴት ሊያዙ እንደቻሉ አስረድተዋል።

ዋና ኢንስፔክተር ካሳ ወጣቶቹን በተመለከተ በቀጣይነት ምን ማድረግ እንዳለባቸው ከክልሉ መንግስት ጋር እየተነጋገሩ መሆኑን ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ የኤርትራ ኤምባሲ እስከአሁን በፖሊስ እጅ በሚገኙት ኤርትራዊያን ጉዳይ ላይ ያለው ነገር አለመኖሩን ተዘግቧል።

ምንጭ፦ DW አማርኛው አገልግሎት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ📎

ዋሽንግተን ዩኒቨርሰቲ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር  ተባብረው ሊሰራ መሆኑ ተገለጸ፡፡

በአሜሪካ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ቋሚ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር #ካሳ_ተክለብርሃን ከዋሽንግተን ዩኒቨርስቲ የሚልጋርድ የቢዝነስ ትምህርት ቤት ኃላፊዎች ጋር ተባብረው በሚሰሩበት መንገዶች ላይ ምክክር ማድረጋቸውን  ተነግሯል፡፡

አምባሳደሩ  ከትምህርት ቤቱ ዲን ሃዋርድ ስሚዝ እና ሌሎች የተቋሙ ኃላፊዎች ጋር ነው በከፍተኛ የትምህርት መስክ ሊኖር በሚችል ትብብር ዙሪያ የተወያዩት፡፡

በውይይቱ ማጠናቀቂ በዋሽንግተን ዮኒቨርስቲ እና ሌሎች የአገራችን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መሀከል ትስስር ለመፍጠር ከመግባባት መደረሱ ተጠቁሟል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለኢዜአ በላከው መግለጫ ላይ እንደተጠቀሰው የሚልጋርድ የቢሰኮስ ትምህርት ቤት በአንደኛና በሁለተኛ ዲግሪ ደረጃ የተለያዩ ትምህርቶችን የሚሰጥ ሲሆን የተመሰረተው እ.ኤ.አ. 1994 ነበር፡፡

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ለገናሌ ዳዋ የውኃ ኃይል ማመንጫ ግንባታ ተነሺዎች የ3 ቢሊየን ብር #ካሳ መከፈሉን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ። የገናሌ ዳዋ የውኃ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት በኦሮሚያ ክልል በባሌና ጉጂ ዞኖች አዋሳኝ ላይ እየተገነባ ይገኛል።

Via fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia