TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ቤንሻንጉል ጉምዝ⬇️

በአሶሳ ከተማ የእርዳታ እህል የተጫኑ 9 ከባድ መኪኖች መንቀሳቀስ አልቻሉም ተባለ፡፡ መኪኖቹ ወደ #ካማሺ ዞን የእርዳታ እህል ለማድረስ ታስቦ የተላኩ ነበሩ፡፡

የብሔራዊ አደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኮሚሽን የአቅርቦትና ሎጅስቲክስ ዳይክቶሬት ዳይሬክተሩ አቶ #ሃይድሮስ_ሀሰን ዛሬ ለሸገር 102.1 እንደተናገሩት፣ 9ኙ ተሽከርካሪዎች 2358 ኩንታል ስንዴ፣ በቆሎና የተለያዩ አልሚ ምግቦችን ተጭነው ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በፀጥታ ችግር ስጋት ከከተማው አልተንቀሳቀሱም ብለዋል፡፡

ብሔራዊ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል አደጋ መከላከል ቢሮ ጋር በመተባበር ዛሬ #በመከላከያና በፖሊስ አባላት መኪኖቹን በማጀብ የእርዳታ እህሉን ወደ ካማሺ ዞን ለማድረስ በዝግጅት ላይ እንደሆነ አቶ ሃይድሮስ ተናግረዋል፡፡

ቀያቸውን ለቀው በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ መጠለያዎች የሚገኙ ተፈናቃዮች ግን ያለ እክል #ድጋፍ እየቀረበላቸው እንደሆነ አቶ ሃይድሮስ
ነግረውናል፡፡

ምንጭ፦ ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" በተኩስ ልውውጡ 19 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል " - ፖሊስ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሺ ዞን ምዥጋ ወረዳ በክልሉ ልዩ ኃይሎችና በመጋቢት ወር ዕርቅ ፈጽመው ከጫካ በተመለሱ የጉሙዝ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ታጣቂዎች መካከል በተደረገ የተኩስ ልውውጥ የ19 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አሳውቋል። ግንቦት 24/2014 በተደረገው የተኩስ ልውውጥ ከተገደሉት መካከል የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ…
#ካማሺ

በካማሺ ዞን የተፈጠረውን ውጥረት ተከትሎ የዞኑ ፀጥታ ምክር ቤት ዓርብ ግንቦት 26 ቀን 2014 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ በካማሺ ከተማ የሰዓት ገደብ ጥሏል።

የፀጥታ ም/ቤቱ " በየአቅጣጫዎች ለማኅበረሰቡ ደኅንነት ሥጋት የሚሆኑ እንቅስቃሴዎች ስላሉ " በሚል በጣለው የሰዓት ገደብ ከምሽቱ 2:00 ሰዓት በኋላ እንቅስቃሴ እንዳይደረግ አግዷል፡፡

የመንግሥትም ሆነ የግል ሞተር ብስክሌቶች በከተማ ውስጥም ሆነ ውጪ እንቅስቃሴ ማድረግ እንደማይችሉ የተገለፀም ሲሆን ይህንን ተላልፈው በተገኙ አካላት ላይ የፀጥታ ኃይሉ ለሚወስደው ዕርምጃ መንግሥት ኃፊነቱን እንደማይወስድ ማስጠንቀቁን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።

@tikvahethiopia