TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.7K photos
1.61K videos
216 files
4.36K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሰላም ለኢትዮጵያ!! ሰላም ለኢትዮጵያ!!
ሰላም ለኢትዮጵያ!! ሰላም ለኢትዮጵያ!!
ሰላም ለኢትዮጵያ!! ሰላም ለኢትዮጵያ!!
ሰላም ለኢትዮጵያ!! ሰላም ለኢትዮጵያ!!
ሰላም ለኢትዮጵያ!! ሰላም ለኢትዮጵያ!!
ሰላም ለኢትዮጵያ!! ሰላም ለኢትዮጵያ!!
ሰላም ለኢትዮጵያ!! ሰላም ለኢትዮጵያ!!
ሰላም ለኢትዮጵያ!! ሰላም ለኢትዮጵያ!!
ሰላም ለኢትዮጵያ!! ሰላም ለኢትዮጵያ!!
ሰላም ለኢትዮጵያ!! ሰላም ለኢትዮጵያ!!
ሰላም ለኢትዮጵያ!! ሰላም ለኢትዮጵያ!!
ሰላም ለኢትዮጵያ!! ሰላም ለኢትዮጵያ!!

#ከጥር_1_እስከ_ጥር_21
የሰላም፣ የፍቅር እና የአንድነት ሳምንታት!!
#TIKVAH_ETHIOPIA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ከፍተኛ ጫና እያሳደረብን ነው "

የ2013 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ተፈትነው ምደባ የሚጠባበቁ ተማሪዎች እና የተማሪ ወላጆች ምደባው እንዲፋጠንለቸው በድጋሚ ጠይቀዋል።

የመጀመሪያውን ዙር ፈተና ተፈትነው እና ውጤታቸውን አውቀው ቤታቸው የተቀመጡ ተማሪዎች 6ኛ ወራቸውን ሊደፍኑ እየተቃረቡ ይገኛሉ።

እስካሁን ምደባ ይፋ የሚሆንበት ቀን ይፋ ያልተደረገ ሲሆን ይህ ሁኔታ ተማሪዎችና ወላጆችን ጫና ውስጥ እየከተተ ነው።

መልዕክታቸውን የላኩ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል የሆኑ አንድ ወላጅ ልጃቸው ብሄራዊ ፈተና ወስዳ ወራት ቢቆጠሩም እስካሁን የምትማርበትን ተቋም ባለማወቋ ጫና እየደረሰባት፤ በግል እንኳን ለማስተማር ውሳኔ ላይ ለመድረስ እንደተቸገሩ፤ አመቱም እየተጠናቀቀ በመሆኑ ከእሷም አልፎ ቤተሰብ ላይ ጫናው እየበረታ መምጣቱን ገልፀዋል።

ከትምህርት እንዳትርቅ ጥረት እያደረጉ መሆኑ የገለፁት ወላጅ ፤ ነገር ግን ከመደበኛው ትምህርት ስርዓት ተማሪ መነጠሉ የሚያሳድረው ጫና ከባድ ነው ብለዋል።

መንግስት የሚስተካከሉ እና የቀረቡ ቅሬታዎች ካሉ በፍጥነት አስተካክሎ እና መፍትሄ ሰጥቶ ተማሪዎችን በፍጥነት ምደባቸውን እንዲያሳውቅ ጠይቀዋል።

ሌሎች መልዕክታቸውን የላኩ የቤተሰቡ አባላት ተማሪዎች ከመደበኛው ትምህርት ውጭ ሆነው የሚያሳልፉት ጊዜ ከፍተኛ የስነልቦና ጫና ውስጥ እየጣላቸው በመሆን መንግስት መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር ከጥቂት ቀናት በፊት ምደባን በተመለከተ ለቲክቫህ በላከው መልዕክት ትንሽ እንዲታገሱ መልዕክት ማስተላለፉ ይታወሳል።

የ2013 ዓ/ም ፈተና የመጀመሪያ ዙር #ከጥቅምት 28/2014 ጀምሮ ለ4 ተከታታይ ቀናት የ2ኛው ዙር ፈተና #ከጥር 24 ጀምሮ ለተከታታይ 4 ቀን መሰጠቱትና ውጤትን ጨምሮ መቁረጫ ነጥብ ይፋ መደረጉ ይታወሳል።

@tikvahethiopia
👍800👎223😢8214👏9🥰2
TIKVAH-ETHIOPIA
#የፀጥታ_ችግር ዘላቂ ሰላም ያልተገኘለት እና ዛሬም ድረስ የሰዎችን ህይወት እየቀጠፈ ያለው ቀጠና መፍትሄው ምንድነው ? • ከ2010 ዓ/ም አንስቶ የበርካታ ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ ንብረት ወድሟል። እርቅ ለመፈፀም ተሞክሮ ዘላቂ ሰላም አልመጣም። • ከሰሞኑ በተፈፀሙ ጥቃቶች የበርካታ ሰዎች ህይወት አልፏል፤ ንብረት ወድሟል ፤ እርቅ ለመፈፀም ጥረት እየተደረገ ነው። • ዛሬ ወደ ገበያ በሚያቀኑ ሰዎች…
#ማረቆ #መስቃን

- " እስከ 2,868 የቤተሰብ አባላቶች የተፈናቀሉበት ሁኔታ ነው ያለው " - የምሥራቅ መስቃን ወረዳ አስተዳደር

- " አንድ ቤተሰብ ላይ ተሰብስበው ቡና እየጠጡ ወደ ሰባት ሰው ተመትቷል። እናትና ልጅ ሞትዋል " - የማረቆ ልዩ ወረዳ አስተዳደር

- " ጉዳዩን በተመለከተ ግምገማ እየተደረገ ነው ሲጠናቀቅ እናሳውቃለን " - የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን

በመስቃንና ማረቆ ብሔረሰብ መካከል በተፈጠረው ግጭት " እስከ 2,868 የቤተሰብ አባላቶች የተፈናቀሉበት ሁኔታ ነው ያለው" ሲሉ የምሥራቅ መስቃን ወረዳ አስተዳደሪ አቶ ጀማል አወል ገለጹ።

ዋና አስተዳዳሪው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ " አሁን በቅርቡ ባለን መረጃ መሠረት ከማረቆ ልዩ ወረዳ ከተለያዩ ቀበሌዎች እስከ 2,868 የቤተሰብ አባላቶች የተፈናቀሉበት ሁኔታ ነው ያለው " ብለዋል።

ግን በሁለቱም ወረዳዎች ደግሞ የሁለቱ ም ብሄሮች ተሰባጥረው በሰላም የሚኖሩበት ሁኔታ ስላለ የብሄር ግጭት ነው ለማለት ያስቸግራል ያሉት አቶ ጀማል፣ "ችግር በተፈጠረባቸው አካቢባቢዎች ግን ተፈናቅለው ወደ ምሥራቅ መስቃንና ሌሎች አካባቢዎች የመጡ አሉ " ሲሉ አክለዋል።

" #ከጥር_7_ቀን_2014 ዓ.ም ወዲህ ( እርቀ ሰላሙ ከተፈጸመ በኋላም ) ከ34 ያላነሱ ግለሰቦች ላይ ከፍተኛ የሆነ ጥቃት ተፈጽሞ ለሞት የተዳረጉበት ሁኔታ አለ። በሁለቱም ወገን ሰው እየሞተ ነው " ብለዋል።

" መስቃንና ማረቆ አካባቢ ያለው ግጭት 4 ዓመታትና ከዚያ በላይ ያስቆጠረ ግጭት ነው " ያሉት አቶ ጀማል " በሕዝብና ሕዝብ መካከል የነበሩ አለመግባባቶች በአካባቢው ባህል መሠረት ጥር 7 ቀን 2014 ዓ.ም ግጭቱ የተፈታበት ሁኔታ ነበር። ከዚያ በኋላም በጣም የተሻሻሉ ሁኔታዎች ነበሩ። በሒደት ግን አንዳንድ እርቀ ሰላሙ እንዲጸና የማይፈልጉ አካላት በተለያዩ ጊዚያቶች ግለሰቦች፣ ተማሪዎች፣ ሴቶች፣ ሕጻናት፣ ፖለቲካውን በቅጡ የማያውቁ አርሶ አደሮች ላይ ጥቃቶች እያደረሱ ከመምጣታቸው ጋር ተያይዞ ግጭቱ እንደገና አገርሽቷል " ነው ያሉት።

ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጀማል የግጭቱን ዋነኛ ምክንያት እንዲያስረዱ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ማብራሪያ፣ " ከ2010 ዓ.ም ወዲህ ለውጡን ተከትሎ የመልካም አስተዳደር ችግርን አሳበው በሚነሱ ጥያቄዎችን ሽፋን አድርገው ሁለቱን ብሄረሰቦች ቅራኔ ውስጥ ያስገቡ አካላቶች አሉ " ብለዋል።

" በዚህ ምክንያት በተለይ ከእርቀ ሰላሙ በፊት ከሁለቱም ወገኖች ወደ 86 ሰዎች የሞቱበት ሁኔታዎች ናቸው ያሉት " ሲሉ አክለዋል።

" በማረቆ ወንድሞች ወገን ዘጠኝ / 9 ቀበሌዎች ወደ ምሥራቅ መስቃን ወረዳ ተከልለውብናል በሚል የሚነሱ ጉዳዮች አሉ" ያሉት አቶ ጀማል፣ "ዞሮ ዞሮ ዋነኛ መነሻው ግን እነዚህ ቀበሌዎችን መሠረት ያደረገ አይደለም በእኔ እምነት " ሲሉ ገልጸዋል።

የቀበሌ ጥያቄዎች ካሉ በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት በማድረስ ሳይሆን በሕግ አሰራር መቅረብ ይችል ነበር ብለው፣ ዋነኛው ምክንያቱ ግን ለራሳቸው ጥቅም ሲሉ ግጭቱ እንዲፈጠርና እንዳይቆም ይፈልጋሉ ያሏቸው የታጠቁ አካላትን ተወቃሽ አድርገዋል።

አክለውም ፣ " የፖለቲካ ቁማሮች በመሠረታዊነት አሉ። ከዚያ ባሻገር ጥቅማቸው ይቀርብናል ብለው የሚያስቡ የታጠቁ አካላቶች ይህ ግጭት እንዳይቆም የሚጥሩበት ሁኔታዎች አሉ " በማለት ተናግረዋል።

ችግሩን እንዲቆም ምን እየተሰራ እንደሆነ ሲጠየቁም፣ ግጭት ያለባቸው አካባቢዎችን በተመለከተ የክልሉ መንግሥት ተወያይቶ የመግባባት ደረጃ ላይ እንደተደረሰ፣ የተኩስ ልውውጥ በመሠረታዊነት እንዲቆም አቋም እንደተወሰደ፣ አዲሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጸጥታ መዋቅር ባደረገው ድጋፍ ግጭቱን በየቀኑ እንዲከታተል ሊደረግ መሆኑን አስረድተዋል።

" አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ የአካባቢው የጽጥታ ሁኔታ ጥሩ ስላልሆነ (ማታ ማታ ስለሚተኮስ) ተጨማሪ የመከላከያ ኃይል እንዲገባ የተደረገበት ሁኔታ አለ " ሲሉም አክለዋል።

በተጨማሪም፣ በመስቃን ወረዳ በሚኖሩ የማረቆ ብሄረሰብ ተወላጆች ሰሞኑን ተፈጸመ በተባለ ጥቃት ሁለት ሰዎች እንደሞቱና ሌሎች እንደቆሰሉ ተነግሯል።

የማረቆ ልዩ ወረዳ አስተዳደር አቶ ንጉሴ መኬ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ማብራሪያ ለመስጠት ፈቃደኛ ባይሆኑም፣ " አንድ ቤተሰብ ላይ ተሰብስበው ቡና እየጠጡ ወደ ሰባት ሰው ተመትቷል። እናትና ልጅ ሞትዋል። ህጻናት ሴት ናቸው። ተሰብስበው ቡና እየጠጡ ነው ጉዳት የደረሰባቸው " ሲሉ ለቪኦኤ አረጋግጠዋል።

#ሰሞኑን በተፈጸመ ጥቃት የሞት እና የአካል ጉዳት መድረሱን በተመለከተም የምሥራቅ መስቃን ወረዳ አስተዳደር አቶ ጀማል አወል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ " ባለፈው ሀሙስ ማረቆ ልዩ ወረዳና መስቃን ድንበር በቼ የሚባል ቀበሌ ላይ ማንነታቸው ባልታወቁ የታጠቁ ኃይሎች ቤት ላይ በተቀመጡ ሰዎች የመሳሪያ እሮምታ ከፍተው ጉዳት አድርሰዋል። አንድ ሕጻን ልጅና እናት የሞቱበት ሁኔታ ነው ያለው። ሌሎች ጉዳት የደረሰባቸው ግለሰቦች በሕክምና ላይ እንዳሉ ነው መረጃው ያለኝ " ብለዋል።

አክለውም፣ መስከረም 14 ቀን 2016 ዓ.ም በማረቆ ልዩ ወረዳ ዲዳ ሚደሬ በሚባል ቀበሌ በባጃጅ ላይ የነበሩ የማረቆ ብሄረሰብ ላይ ጉዳት እንደደረሰ፣ ይህን ተከትሎ በመስከረም 15 እና 16 ቀን 2016 ዓ.ም በመስቃንና ማረቆ ልዩ ወረዳዎች ድንበር ላይ ዲባ ሀዲቦ ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ እንደነበር አስረድተዋል።

አያይዘውም መስከረም 16 ቀን 2016 ዓ.ም በነበረው ግጭት ስድስት ሰዎች፣ መስከረም 14 ቀን 2016 ዓ.ም አምስት ሰዎች እንደተገደሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

ግጭቱን ለማስቆም ምን እየተሰራ እንደሆነ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ የቀረበላቸው የማዕከላዊ እትዮጵያ ክልል ፖሊስ አዛዥ ኮሚሽነር ሽመልስ በበኩላቸው " ጉዳዩን በተመለከተ ግምገማ እየተደረገ ነው ሲጠናቀቅ እናሳውቃለን " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

መረጃው በአዲስ አበባ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው።

@tikvahethiopia
😢26089😡33🕊14😱11🙏11🥰2