TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.8K photos
1.61K videos
216 files
4.36K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
'በአማራና ደቡብ ክልል የታዩ ስጋትን የሚፈጥሩ ሁኔታዎች'

የፖለቲካ ፓርቲዎች በየምርጫ ጣቢያው ታዛቢ ወኪሎቻቸውን አስቀምጠው ጉዳዩን የመታዘብ እና የማየት ፣ችግር ካላቸው ያን አስመዝግበው ወደፍርድ ቤት የሚሄዱ ከሆነም ያን አስመዝግበው ሰነዶቻቸውም ይዘው ክርክራቸውን የመቀጠል መሰረታዊ መብት አላቸው።

በዚህ ረገድ አብዛኛው ክልል ጥሩ የሚባል ሁኔታ አለ፤ ነገር ግን በሁለት ክልሎች (አማራ እና ደቡብ) በጣም አሳሰቢ በሆነ ደረጃ፣ በአንዱ (አፋር ክልል) በመለስተኛ ደረጀ ከፍተኛ ስጋት የሚፈጥር ሁኔታ መመልከቱን ምርጫ ቦርድ አሳውቋል።

አማራ እና ደቡብ ክልሎች ላይ የፖለቲካ ፓርቲ እጩ ወኪሎች ከቦታ ቦታ በፈለጉበት አግባብ መንቀሳቀስ እየቻሉ እንዳልሆነ፣ ድብደባ እየተፈፀመባቸው እንደሆነ፣ ባጅ እየተቀሙ እንደሆነ ፣ ወደ ጣቢያ ሊጠጉ የማይችሉበት ሁኔታ እየተፈጠረ እንደሆነ እጅግ በጣም ብዙ አቤቱታ ለቦርዱ ቀርቧል።

አቤቱታው #ከገዢው_ፓርቲ በስተቀር ከሁሉም ፓርቲዎች ነው ለቦርዱ የቀረበው።

የክልሎቹ አስተዳዳሪዎች ይህን ችግር እንዲያስተካክሉ እና እንዲፈቱ ቦርዱ አሳስቧል።

ቦርዱ፥ ችግሩ ካልተፈታ የምርጫ ሂደቱን እና የውጤቱን ታማኝነት ችግር ላይ እንደሚጥለው ሊታወቅ ይገባል ብሏል።

ምርጫ ቦርድ ክልሎቹ በአፋጣኝ ማስተካከያ እንዲያደርጉ የታችኛው የአስተዳደር ክፍል በተጨማሪ አንዳንድ ጊዜ የህግ አስፈፃሚዎች በፖለቲካ ፓርቲ ወኪሎች ላይ ፣ በእጩ ወኪሎች ላይ የሚፈፅሙት ከህግ ውጪ የሆኑ ድርጊቶችን #አሁንኑ እንዲያቆሙ ሲል በጥብቅ አስገንዝቧል።

@tikvahethiopia