TIKVAH-ETHIOPIA
#ExitExam የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ፦ " የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና በሁሉም ዩኒቨርስቲዎች ለሚማሩ የቀን ፣ የማታ እና የርቀት መርሀ ግብር ተመራቂዎች ይሰጣል። ከዚህ ዓመት ጀምሮ በመንግስትና ግል ዩኒቨርስቲዎች ተግባራዊ የሚደረገውን የመውጫ ፈተና #በኦንላይን ለመስጠት ታቅዷል ። በመሆኑም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመሠረተ ልማት አቅሞቻቸውን ከወዲሁ በማረጋገጥ ለፈተናው…
#MoE
• መውጫ ፈተና በመጪው ሰኔ ወር በተመሳሳይ ጊዜ ይሰጣል።
• 200, 000 ተማሪዎች ፈተናውን ይወስዳሉ።
መውጫ ፈተና በሁሉም ዩኒቨርስቲዎች ለሚገኙ ተማሪዎች በአንድ ጊዜ እንደሚሰጥ የከፍተኛ ትምህርት የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ገልጸዋል።
መሪ ስራ አስፈጻሚው ኤባ ሚጀና ( ዶ/ር ) በጉዳዩ ዙሪያ በተዘጋጀ አውደጥናት ላይ እንደገለጹት መውጫ ፈተና በመጪው ሰኔ ወር ለሁሉም ቅድመ መደበኛ ተማሪዎች በአንድ ጊዜ ይሰጣል።
የመጀመሪያው ፈተና በሰኔ ወር ከተሰጠ በኋላ ቀጣዩ የመውጫ ፈተና ከ6 ወራት በኋላ እንደሚሰጥም ዶ/ር ኤባ አስረድተዋል።
የከፍተኛ ትምህርት ጥራትና ብቃት ዴስክ ኃላፊ አቶ ሰይድ መሀመድ በበኩላቸው ፈተናውን ለ200, 000 የመንግስትና የግል ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
ፈተናው ለሁሉም ተማሪዎች በኦንላይን እንደሚሰጥ የጠቀሱት አቶ ሰይድ " ይህ የፈተና ስርቆትን ለመከላከል የተሻለ አማራጭ በመሆኑ ነው " ብለዋል።
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱም ሆኑ ተፈታኝ ተማሪዎች ፈተናው በተመሳሳይ ጊዜ በኦንላይን እንደሚሰጥ አውቀው #ከወዲሁ_ዝግጅት እንዲያደርጉ አቶ ሰይድ አሳስበዋል።
በመውጫ ፈተና ብቃትና የፈተና ኮርሶች ልየታና የተገቢነት ማረጋገጥ ዙሪያ በተዘጋጀው አውደጥናት ከሁሉም ዩኒቨርስቲዎች የተውጣጡ ጉዳዩ የሚመለከታቸው መምህራን ተሳታፊ መሆናቸውም ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።
(ትምህርት ሚኒስቴር)
@tikvahethiopia