TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" ... ዜጎች የሚፈልጉትን አገልግሎት ከመንግስት ተቋማት በተገቢው መንገድ እያገኙ ነው የሚል ግምገማ የለንም " - የኢትዮጵያ ህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም

የመልካም አስተዳደር ችግር ከመሻሻል ይልቅ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ እንደሆነ የኢትዮጵያ ህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም አሳውቋል።

ዜጎች ፤ የሚፈልጓቸውን አገልግሎቶችን ከመንግስት ተቋማት ማግኘት #ፈተና_እንደሆነባቸውም ተቋሙ ገልጿል።

የተቋሙ ዋና ዕንባ ጠባቂ የሆኑት ዶ/ር እንዳለ ኃይሌ ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጣቢያ በሠጡት ቃል ፤ " እንደ አጠቃላይ እንደ ሀገር የመልካም አስተዳደር ችግሩ እየሰፋ ተፈጥሮውም Complex (ውስብስብ) እየሆነ ነው የመጣው ዜጎች የሚፈልጉትን አገልግሎት ከመንግስት ተቋማት በተገቢው መንገድ እያገኙ ነው የሚል ግምገማ የለንም ፤ ይሄንን መንግስትም የሚያውቀው ጉዳይ ነው " ብለዋል።

" የመንግስት ተቋማት የተቋቋሙለት የሚቋቋሙበት ለህብረተሰቡ አገልግሎት ለመስጠት ነው " ያሉት ዶ/ር እንዳለ " ለህብረተሰቡ አገልግሎት ሲሰጡ ከዜጎች የሚሰበሰብ ታክስ አለ፣ ከዜጎች ከሚሰበሰብ ታክስ ነው እያንዳንዱ የመንግስት ተቋም የሚተዳደረው ፣ እያንዳንዱ የመንግስት ሰራተኛ ደመወዙ የሚከፈለው ፤ ነገር ግን #ከህብረተሰቡ_በሚሰበሰበው_ታክስ ፣ ህብረተሰቡ ከሚያወጣው ወጪ አንፃር አገልግሎት እየተሰጠነው የሚል አጠቃላይ ግምገማ የለንም " ሲሉ ገልፀዋል።

ይህ ችግር ለዜጎች ሰፋ ያለ አገልግሎቶችን መስጠት በሚጠበቅባቸው የመንግስት ተቋማት የሚብስ ሲሆን ከተማ አስተዳደር፣ ወረዳ እና ቀበሌ ዋና ዋና ተጠቃሽ ናቸው።

ዶ/ር እንዳለ " በተለይ የከተማ አስተደሮች አካባቢ ፤ በተለይ ማዘጋጃ ቤቶች አካባቢ፣ ሰፋፊ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት አካባቢ እንደ #ወረዳ#ቀበሌ#ከወሣኝ_ኩነት ጋር ተያይዞ መሰረታዊ የመልካም አስተዳደር ችግር እንዳለ መንግስትም ያምናል የኛም ግኝት ያን ያመለክታል " ሲሉ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ፥ " በፌዴራል መስሪያ ቤቶች የመልካም አስተዳደር ምን ሁኔታ ላይ ነው ያለው ? " የሚለውን ካሉት 22 ሚኒስትር መ/ቤቶች ሰፋፊ አገልግሎት በሚሰጡ 15 መ/ቤቶች በቅርብ ቀን ጥናት በማድረግ ለህዝብ እናሳውቃለን ሲል ለሬድዮ ጣቢያው አሳውቋል።

#credit_ሸገር_ኤፍ_ኤም

@tikvahethiopia