TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#AddisAbaba

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ፥ በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወነ በሚገኘው የኮሪደር ፕሮጀክት እና ተያያዥ የልማት ሥራዎች ምክንያት በተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ መስመር የማዛወር ሥራዎች እየተሰራ መሆኑን ገልጿል።

በዚህም ሥራው ሲከናወን ተገቢውን ጥንቃቄ ለማድረግ እንዲሁም አደጋ እንዳይከስት ሲባል ሥራው በሚከናወንባቸው አካባቢዎች የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ሙሉ ለሙሉ ወይም አልፎ አልፎ ለተወሰኑ ሰዓታት #እየተቋረጠ እንደሚገኝ አመልክቷል።

" የመስመር ማዛወር ሥራዎቹ በጥንቃቄና በፍጥነት ለማከናወንና አገልግሎቱን ለማስቀጠል ከፍተኛ ጥረት እያደረግን ነው " ያለ ሲሆን ነዋሪዎች ይህን ተረድተው በትዕግስት እንዲጠባበቁ ጥሪ አቅርቧል።

በዚህ ምክንያት ለሚፈጠሩ ለአገልግሎት መስተጓጎሎችም #ይቅርታ ጠይቋል።

በሌላ በኩል፥ ከመጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ከ4 ኪሎ እስከ ፒያሳ ባለው መስመር የራስ መኮንን ድልድይ እየተሰራ በመሆኑ የመንገድ ግንባታው እስከሚጠናቀቅ በተለይ በስራ መግቢያ እና መውጪያ ሰዓት አሽከርካሪዎች ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክት አስተላልፏል።

በዚህም፦
ከ4 ኪሎ ወደ ራስ መኮንን ድልድይ
ከደጎል አደባባይ ትራፊክ መብራት ወደ 4 ኪሎ
ከቅ/ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ወደ ወደ ራስ መኮንን ድልድይ
ከደጃች ውቤ ወደ ራስ መኮንን ድልድይ
ከአፍንጮ በር ወደ ራስ መኮንን ድልድይ
ከባሻ ወልዴ ችሎት ወደ ራስ መኮንን ድልድይ እና ከቀበና ወደ ፒያሳ የሚመጡ አሽከርካሪዎች መንገዱ ግንባታ ላይ መሆኑን ተገንዝበው ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ተብሏል።

@tikvahethiopia